ከዛሬ ጀምሮ መንገደኞች የጉዞ ትኬታቸውን በቴሌብር አማካኝነት ብቻ መቁረጥ ይጠበቅባቸዋል
👉 ደንበኞች የብሔራዊ መታወቂያ ከሌላቸው የተቋሙ አገልግሎት ማግኘት አይችሉም፣
****
(ኢ ፕ ድ)
የኢትዮ ጅቡቲ የባቡር መንገድ አክስዮን ማህበር ከዛሬ የካቲት 24 ጀምሮ መንገደኞች የጉዞ ትኬታቸውን በቴሌብር አማካኝነት ብቻ መቁረጥ እንደሚጠበቅባቸው አስታወቀ።
የኢትዮጵያ ጅቡቲ ባቡር አክስዮን ማህበር ከፍተኛ የኮሙኒኬሽን ባለሞያ ወይዘሮ እስራኤል ወልደመስቀል ለኢፕድ እንደገለፁት፤ የመንገደኞችን እንግልት ለመቀነስና ለጋራ ደህንነት መንገደኞች የጉዞ ትኬታቸውን በቴሌብር አማካኝነት በመቁረጥ አገልግሎቱን ማግኘት እንዲችሉ ተደርጓል።
ማህበሩ የአገልግሎት አሰጣጥ ስርዓቱን ዲጂታላይዝድ ማድረጉን የገለፁት ወይዘሮ እስራኤል፤ ከዛሬ የካቲት 24 ጀምሮ መንገደኞች የጉዞ ትኬታቸውን በቴሌብር አማካኝነት ብቻ መቁረጥ እንደሚጠበቅባቸው ተናግረዋል።
ደንበኞች የብሔራዊ መታወቂያ ከሌላቸው የተቋሙ አገልግሎት ማግኘት አይችሉም። ይህንንም ለደንበኞች የማሳወቅ ስራው ከአንድ ወር በፊት ጀምሮ ሲሰራ እንደነበርና ከብሄራዊ መታወቂያ ፕሮግራም ጋር በመተባበር መታወቂያውን እንዲያገኙት እየተደረገ እንደነበር አስታውሰዋል።
የብሔራዊ መታወቂያ ተግባራዊነቱ ለሃገር ውስጥ ተጠቃሚዎች ብቻ ሲሆን፤ ኢትዮጵያዊ ላልሆኑ ተጠቃሚዎች ፓስፖርታቸውን በመጠቀም ትኬት ማግኘት እንደሚችሉ ወይዘሮ እስራኤል ገልጸዋል።
በኦንላይን ትኬት የመቁረጥ አገልግሎት ተግባራዊ መደረግ መጀመሩ ይታወሳል።
በቃልኪዳን አሳዬ
የካቲት 24 ቀን 2017 ዓም