እውቀት knowledge


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic
Category: not specified


እውቀት ለፍጥረታት።Knowledge for all.

Related channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Category
not specified
Statistics
Posts filter


Forward from: Ethiopia Check
#EthiopiaCheck ምስሎችን ለማጣራት ልንጠቀምባቸው የምንችላቸውን ሁለት መተግበሪያዎች እናስተዋውቃችሁ

መረጃዎችን እንዲሁም ምስሎችን ለማጣራት የሚረዱ የተለያዩ የቴክኖሎጂ መተግበሪያዎች ይገኛሉ። ከድረ- ገጾች እስከ ሞባይል መተግበሪያዎች ድረስ አይነታቸው ብዙ የሆኑ የመረጃ ማጣራትን ስራ የሚያቀሉ እና እውነተኝነታቸውን የሚያረጋግጡ መሳሪያዎች አሉ። ከእነሱም መካከል:

1.  ቲንአይ(TinEye):
ይህ መተግበሪያ ምስሎችን በኢንተርኔት አማካኝነት ለማጣራት የሚጠቅመን ድረ-ገጽ ነው። የምንፈልገው ምስል ከዚህ በፊት ጥቅም ላይ ውሎ ከነበረ መቼ እና የት እንዲሁም በምን መልኩ ጥቅም ላይ እንደዋለ ያሳውቀናል። በዚህ መተግበርያ በፎቶሾፕ የተነካኩ ምስሎችንም ፈልጎ ማግኘት ይቻላል። ድረ-ገፁ www.tineye.com ሲሆን አጠቃቀሙ ደግሞ ድረ-ገጹ ላይ የምንፈልገውን ምስል ከኮምፒተር ወይም ከስልካችን ላይ መርጠን በማስገባት መፈለግ ነው። ያስገባነውን ምስል አርቴፊሻል ኢንተለጀንስን በመጠቀም ቲንአይ ከኢንተርኔ ላይ ከወሰዳቸው 45 ቢሊዮን ምስሎች ውስጥ ይፈለግለናል። ምስሉን እና ምስሉን የሚመስሉ በርካታ ውጤቶችን ያወጣል፣ ከወጡት ምስሎች ውስጥም የምንፈልገውን መርጠን ስንመለከት ከዚህ በፊት ይህ ምስል የት ጥቅም ላይ እንደዋለ ማየት እንችላለን። ምንም ውጤት ካልመጣ ደግሞ ምስሉ ከዚህ በፊት ጥቅም ላይ አልዋለም ማለት ነው፣ ወይም ምስሉ የቲንአይ ክምችት ውስጥ የለም ማለት ነው። ይህን መሳሪያ በነጻ መጠቀም መቻሉ አንዱ ጥሩ ጎኑ ነው።

2.  ፎቶ ፎሬንዚክስ (Photo Forensics):
ይህ መተግበርያ የሚጠቅመን የአንድን ፎቶ በፎቶሾፕም ሆነ በሌላ መተግበሪያ አለመነካካቱን እና ከዋናው ፎቶ አለመቀየሩን ነው። አጠቃቀሙ ደግሞ ወደ www.fotoforensics.com ከገባን በሁዋላ በመጀመሪያው ገጽ ማረጋገጥ የምንፈለገውን ፎቶ የምናስገባበት ገጽ እናገኛለን። የምንፈልገውን ፎቶ ከኮምፒተራችን ወይም ከስልካችን መርጠን ካስገባን በሗላ ፈልጎ ሲጨርስ ፎቶው ተነካክቶ ከሆነ ምኑ ጋር እንደተነካካ ወይም እንደተቀየረ የሚያሳየን ፎቶ ይመጣል። ያስገባነው ፎቶ ላይ ወጥ የሆነ ቀለም ብቻ የምናይ ከሆነ ፎቶ እውነተኛ ፎቶ መሆኑን ማረጋገጥ እንችላለን፣ አለበለዚያ ደሞ አንድ ቦታ ላይ በብዛት ለየት ያለ ቀለም ወይም ነጣ ያለ ቀለም አንድ ቦታ ላይ ተከማችቶ ካገኘን ያ ፎቶ መነካካቱን መረጋገጥ እንችላለን። ፎቶውም ከየት እንደመጣ(ከካሜራ ወይስ ከፎቶ ሾፕ) ማየት እንችላለን።

ኢትዮጵያ ቼክ

@EthiopiaCheck


ጠቃሚ ቦቶች ናቸው ‼️

@xD0RMuleBot ቶረንት files ለማውረድ
@Tech_GPT_Bot ai ለመጠቀም
@PigeonDocumentBot ዶክመንት ማኔጅ ለማድረግ
@WeatherAppRobot የአየር ንብረት መረጃ
@BitgetOfficialBot ቢትጌት እዚሁ ለመጠቀም
@voicetomp3_bot የተቀረጽነው ድምጽ ወደ mp3 ቀይሮ ለመላክ


አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አዲስ የተማሪዎች ቅበላ አሰራርን ከ2017 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ጀምሮ ተግባራዊ ያደርጋል፡፡

አሰራሩ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲን  የላቀ ውጤት ያስመዘገቡ እና ልዩ ብቃት ያላቸው ተማሪዎች ማስተማሪያ ተቋም ያደርገዋል፡፡

ይህን አስመልክቶ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተ/ፕሬዝዳንት ሳሙኤል ክፍሌ (ዶ/ር) ለመገናኛ ብዙሃን ጋዜጣዊ መግለጫ እየሰጡ ይገኛሉ።
***

ከ2017 ዓ.ም የትመህርት ዘመን ጀምሮ ስለሚተገበረው የተማሪዎች ቅበላ አሰራር ዋና ዋና ጉዳዮች የሚከተሉት ናቸው፣

👉 አዲሱ የተማሪዎች ቅበላ አሰራር አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ወደ ሙሉ ራስ-ገዝነት በሚያደርገው የሽግግር ሂደት አንድ አካል ነው

👉 አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲን  የላቀ ውጤት ያስመዘገቡ እና ልዩ ብቃት ያላቸው ተማሪዎች ማስተማሪያ ተቋም ያደርገዋል

👉 አሰራሩ የሚተገበረው በመጪው የትምህርት ዘመን በዩኒቨርሲቲው አዲስ  የቅድመ ምረቃ እና ድህረ ምረቃ ተማሪዎች ጀምሮ ነው

👉 ከፍተኛ ብቃት ያላቸው ተማሪዎች  የተዘጋጀውን የመወዳደሪያ ነጥብ ፣ የመግቢያ ፈተና እንዲሁም ሌሎች መስፈርቶችን ሲያሟሉ ብቻ ወደ ዩኒቨርሲቲው የሚገቡ ይሆናል

👉 የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ፣ ፍትሐዊ የትምህርት ተደራሽነትን ለማስፋት ፣ ኢትዮጵያ በመጪው ዘመን የምትፈልገውን ብቁ ምሩቃንን ለማፍራት እንዲሁም በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ የሆኑ ተማሪዎችን  ለማዘጋጀት የሚያስችል ነው

👉 አሰራሩ በመንግስት ወጪ የሚሸፈን የትምህርት ዕድል (ስኮላርሺፕ) እና በግል ወጪን በመሸፈን የተማሪዎችን ስብጥር በጠበቀ መልኩ ማስተናገድ እንዲያስችል ተደርጎ የተቀረጸ ነው

👉  አዲሱ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ቅበላ ስርዓት ለቅድመ ምረቃና ድህረ ምረቃ ተማሪዎች በፖሊሲው እና በመመሪያው መሰረት የሚተገበር ሆኖ፣

1.  ለሴቶች፣ ለአካል ጉዳተኞች እና ከታዳጊ ክልል ለሚመጡ ተማሪዎች ልዩ ትኩረት በመስጠት ፍትሓዊነቱ ይረጋገጣል፡፡
2. መንግስት ከፍተኛ ብቃት ያላቸውና ተወዳዳሪ የሆኑ ተማሪዎችን ለሀገር በሚፈለጉ የስልጠና መስኮች ወጪን ጭምር በመሸፈን የሚያስተናግድበት ስርዓት ይኖራል፡፡
3.  በገበያው እጅግ ተፈላጊ በሆኑ የትምህርት መስኮች ጥራት፣ ፍትሐዊነት እና ብዝሀነት ሳይዘነጋ በራሳቸው የትምህርት እና ሌሎች ወጪያቸውን ሸፍነው ለሚማሩ ተማሪዎች እድል ተመቻችቷል፡፡

በ2014፣ 2015 እና 2016 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ የመልቀቂያ ፈተና ወስደው የማለፊያ ነጥብ ያገኙ ተማሪዎች የሚወጣውን መስፈርት ታሳቢ አድርገው በዩኒቨርሲቲው ፖርታል https://portal.aau.edu.et መመዝገብ ይችላሉ።
@t.me/etknowledge




Google.com በየቀቡ 4.5 ቢሊየን የሚጠጉ ሰዎች 'በመጎልጎል' (መረጃ ለማፈላለግ) ይጠቀሙበታል ሆኖም ግን በትክክል አጠቃቀሙን የሚችሉት ብዙ አይደሉም። እርስዎስ?
ትክክለኛ እና ብዙ መረጃ በተወሰነ ጉዳይ ላይ ለማግኘት ይሄ ሊጠቅም ይችላል

1 የሚፈልጉትን ቃላት ወይም ሐረግ (quotation) ወይም እንደ ጥቅስ መጠቀም ለምሳሌ "Football News" የእግር ኳስ ዜና ብቻ ያሳያል።

2 ሁለተኛው የማይፈለገውን ቃል ማስቀረት ወይም exclude ማድረግ ነው። ይሄንን ለማድረግ ሰረዝ (-) መጠቀም ያስፈልጋል። ለምሳሌ Manchester የአንድ ከተማ ስም ነው። ለማየወቅ የተፈለገው ከተማው ላይ ስላለው ማንቼስተር ዮኒቨርሲቲ ነው እንበል። Google ላይ Manchester ብትጽፉ ወዲያውኑ Manchester Football Club የሚሉ ብዙ መረጃዎችን ያግበሰብሳል እንጂ የዩኒቨርሲቲውን መረጃ አይመጣም ስለዚህ Google ላይ ሰረዝ (-) መጠቀም ያስፈልጋል Manchester - University (ይሄ ሲጻፍ The University of Manchester የሚሉ መረጃዎች ብቻ ይመጣሉ።

3 ተያያዥ ቃላቶችን synonymous ሲፈልጉ ይቺን Tilde (~) ምልክት ይጠቀሙ። ለምሳሌ Football~training #training ከሚለው ጋር ተያያዥ ቃላቶችን Instruction, coaching, exercising ወዘተ ሌሎችም ቃላት ያገኛሉ

4 በአመታት ገደብ ተደርጎ መረጃ ሲፈለግ ሁለት ነጥቦች (. .) መጠቅም ወሳኝ ነው።
ምሳሌ Ethiopian history (1974..1991) ተብሎ መረጃ ሲፈለግ Google በዚህ አመታት ብቻ ያለውን መረጃ ያስነብባል። አለማወቅ ብዙዎች መረጃ ሲፈልጉ የሚያደርጉት ግን (From 1974 to 1991 ወይም between 1974 and 1991) ብለው ነው። በዚህ አቀራረብ Google ስለማይረዳው የሚያቀርበው መረጃ ዝብርቅረቅ ያለ ይሆናል። ስለዚህ ሁለቱን ነጥቦች በሚፈለገው አመታት፣ ወራት፣ ሳምንት መካከል መጠቀም በጣም ወሳኝ ነው።

5 Filetype የሚባለው ነው። ብዙውን ጊዜ በሚፈለገው ጉዳይ ብቻ Pdf የተሰራ እውነተኛ ፋይል ያቀርባል። ለምሳሌ Berbera Filetype:pdf ብሎ Google ላይ በመጻፍ ስለ ወደቡ እንቅስቃሴ ማንበብ ይቻላል።

https://t.me/etknowledge


ኮምፒውተራቸው ላይ የጫናችሁት antivirus በትክክል መስራቱን ለማረጋገጥ በሚከተለው መንገድ virus ፈጥራችሁ መሞከር ትችላላችሁ።
ቫይረሱ ምንም አይነት ጉዳት ኮምፒውተራችሁ ላይ አያስከትልም።

1. Notepad ክፈቱና የሚከተለውን code paste አድርጉ።

"X5O!P%@AP[4\PZX54(P^)7CC)7}$EICAR-STANDARD-ANTIVIRUS-TEST-FILE!$H+H*"

⚠️የquotation ምልክቱን አታስገቡም።

2. የsave ምልክቱን ንኩና save አድርጉት። save ስታደርጉ ስሙን virus.com ወይም eicar.com ብላችሁ መሆን አለበት።

3. የሚሰራ antivirus ካላችሁ ልክ ፋይሉን ስትከፍቱት አንቲቫይረሱ ፋይሉን ያጠፋዋል።
ካላጠፋው አንቲቫይረሱ አይሰራም ወይም disable አድርጋችሁታል ማለት ነው።

ምንጭ ፦ big habesha

https://t.me/etknowledge


ከአንድ ምስል ጀርባ ብዙ የግል መረጃዎች እንዳሉ ያውቃሉ?

✍🏿 ሜታ ዳታ (meta data) የምንለው በዲጅታል ፋይሎች ላይ ማለትም በምስል፤ በቪድዮ እና በዶክመንቶች ላይ ተያይዞ የሚገኝ መረጃ ነው። ይህ መረጃ ስለ ፋይሉ ጥልቅ የሆኑ መረጃዎችን ማለትም ምስሉ የተነሳበት ቀን ፣  ሰዓት፣ ምስሉን ለማንሳት ጥቅም ላይ የዋለው የካሜራው አይነት፣ የካሜራውን ሴቲንግ ፤ ምስሉ የተነሳበትን  ቦታ፣  ምስሉን ኤዲት ለማድረግ ጥቅም ላይ የዋለውን ሶፍትዌር እና ሌሎችንም መረጃዎች የሚያሳይ የአንድ ዲጂታል ፋይል መለያ ነዉ ።

✍🏿 ስለዚህ አንድ ምስል በኦንላየን ወይም በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ሲያጋጥመን የፋይሉን ሜታ ዳታ በመመልከት ምስሉ ከተጋራበት አዉድ ጋር በማመሳከር እዉነት መሆን አለመሆኑን መለየት እንችላለን፡፡

✍🏿 ሜታ ዳታ ጥቅም እንዳለዉ ሁሉ የግላዊ ሚስጥር እና ደህንነትን ስጋት ላይ የማጋለጥ አሉታዊ ጎን አለው ለምሳሌ አንድ ምስል በኢንተርኔት  ላይ ሲለቀቅ ሚስጥራዊ የሆኑ መረጃዎችን ማለትም ፎቶውን ያጋራው ሰው ያለበትን ቦታ እና ሰዓቱን የሚያሳይ ከሆነ ለጥቃት ሊጋለጥ ይችላል። ከዚያ ባለፈ እነዚህ መረጃዎች  ግለሰቡን ለስለላ ሊያጋልጡት  ይችላሉ፡፡

✍🏿 ሌላው ደግሞ አሁን አሁን አንዳንድ ጥናቶች እንደሚያሳዩት አንዳንድ ማህበራዊ ሚድያዎች ላይ ምስል እንዳጋራን ወዲያዉኑ የምስሉን ሜታ ዳታ እንደሚያጠፉት ያሳያሉ

✍🏿 የአንድን ምስል ሜታ ዳታ ለማየት የሚጠቅሙ ብዙ መሳሪያዎች ያሉ ሲሆን ከነዚህ መካክል verexif.com አንዱ ነው፡፡
ምንጭ : haqcheck

https://t.me/etknowledge


አዲስአበባ ዩኒቨርሲቲ በቀን መርሐግብር መማር ለምትፈልጉ!...

ለ2016 ዓ.ም. ለመጀመሪያ ዲግሪ በቀን በመደበኛ መርሃ-ግብር የትምህርት ክፍያ በመክፈል መማር ለሚፈልጉ አመልካቾች በሙሉ ዩንቨርሲቲው በተወሰኑ የትምህርት መስኮች የግል አመልካቾችን ለመቀበል ዝግጅት አድርጓል በመሆኑም ዩኒቨርሲቲዉ የመግቢያ ፈተና የሚሰጥበት ጊዜ ከህዳር 27 እስከ ህዳር 28 2016 ዓ.ም ሲሆን የማመልከቻ ቀናት ከህዳር 20 እስከ ህዳር 25 ቀን 2016 ዓ.ም ብቻ በመሆኑ ለመመዝገብ በዩኒቨርስቲውን ፖርታል https://portal.aau.edu.et/ >>>> Apply for Admission በሚለው በመግባት መመዝገብና ለፈተና መክፈል የምትችሉ ሲሆን የፈተና የመፈተኛ ቦታ በቴሌግራም ቻናል>>> https://t.me/aau_official ስለምናሳውቅ እንድትከታተሉ እናሳስባለን።

ለተጨማሪ መረጃ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ሬጅስትራር ቢሮ ማግኘት ትችላላችሁ፡፡

#ማስታወሻ:- ሼር ቢያደርጉት ቢያንስ አንድ ወገን ይጠቅማሉ።

https://t.me/etknowledge


Microsoft office አክቲቬት ለማድረግ






አንዴ ኮኔክት ያደረጋችሁትን ፓስወርድ ከረሳችሁ‼️






window activation




ኮምፒውተራችሁ ለሚንቀራፈፍባችሁ☝️




በ online ተምረው certified ለመሆን☝️



20 last posts shown.