#ከሰሞኑ እየበዛ ያለው ጥያቄ 'ልጄን ወይም የልጅ ልጄን ትምህርት ቤት ለማስመዝገብ የልደት ካርድ አቅርቢ ተባልኩኝ እሱን ለማውጣት ደግሞ ሌላኛው ወላጅ ከሌለ ወይም የሞግዚትነት ውሳኔ ከሌለሽ አይቻልም ተባልኩኝ' ምን ይሻለኛል? የሚል ነው። እነሆ ምላሹ!
#ልጅዎን ወይም የልጅ ልጅዎን ለብቻዎ እያሳደጉ ከሆነ በሚኖሩበት ክፍለ ከተማ ሥር በሚገኘው የአዲስ አበባ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመቅረብ ልጅዎትን ወይም የልጅ ልጅዎን ለብቻዎ እያሳደጉ መሆኑንና ለልጅዎ ወይም ለልጅ ልጅዎ ሞግዚትና አሳዳሪ ተደርገው ለመሾም ያመልክቱ።
#ሲያመለክቱ እንደማስረጃነት የክትባት ወረቀት፣ የሀኪም ቤት የተወለደበት ማስረጃ እና የእምነት ተቋም ማስረጃዎችን ማያያዝዎትን አይርሱ።
#በማመልከቻው ላይ በምን ምክንያት ልጅዎን ወይም የልጅ ልጅዎን ለብቻዎ እያሳደጉ እንዳለ ሚያቀርቡት ምክንያት ማስረጃ ካለው እሱን ይጥቀሱ፤
ለምሳሌ ባለቤቴ ሞቷል ካሉ የሞት ሠርተፍኬት ወይም የፍርድ ቤት ውሳኔ፣ በሕጋዊ መልኩ ተለያይተው ከሆነ የፍቺ ውሳኔ፣ ወላጆቹ በሕይወት ወይም በሥራ ምክንያት በአካባቢው ከሌሉ ምክንያቶችን ይጥቀሱ።
#ፍርድ ቤቱ ያለዎትን ማስረጃ እና ምስክሮች ከመረመረ በኋላ ለልጅዎ ሞግዚትና አሳዳሪ እንደሆኑ አረጋግጥዎ ማስረጃውን ይሰጥዎታል።
#ይህን ውሳኔ ይዘው በሚኖሩበት ወረዳ ለልጅዎ የልደት ሠርተፍኬት በማውጣት ለሚፈልጉት አገልግሎት ሊጠቀሙበት ይችላሉ።
የሞግዚትነት ሥልጣን ቅደም ተከተል
1. የልጁ ወላጅ አባትና እናት
2. የልጁ ወደላይ ሚቆጠሩ ወላጆች (አያቶች)
3. አካለ መጠን የደረሱ የልጁ ወንድሞች እና እህቶች
4. የአጎት ወይም የአክስት ልጆች
#አቤቱታውን ለማጻፍ አቅም ከሌለዎት በቴሌግራም በኩል ያናግሩኝ።
⚖️ይግባኝ መብት ነው!!!
©️ጠበቃ ቴዎድሮስ አብዲሳ
☎️ 09 10 61 69 50