መርህ
በወንጀል ጉዳይ የተጠረጠረ ግለሰብ ጉዳዩን በዋስትና ከእስር ውጪ በመሆን እንዲከታተል ሊፈቀድለት ይችላል።
ዋስትና የተፈቀደለት ሰው ጥፋተኛ ወይም ነፃ እስኪባል ፍርድ ቤት በሚሰጣቸው ቀጠሮዎች ሁሉ የመቅረብ ግዴታ አለበት።
ይህ የመቅረብ ግዴታው ተጠርጣሪው የሕግ ባለሙያ ቢኖረውም ባይኖረውም የማይቀር ነው።
በተሰጠው ቀጠሮ ባይቀርብ ውጤቱ ምን ይሆናል?
ፍርድ ቤቱ በወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 79 መሠረት በዋስትና የተያዘው ገንዘብ ሊወረስ የማይችልበትን ምክንያት ተጠርጣሪው በቀጣይ ቀጠሮ በመቅረብ ካላስረዳ በስተቀር ለዋስትና ያስያዘውን ገንዘብ ለመንግሥት ገቢ በማድረግ ተጠርጣሪው ጉዳዩን በእስር ቤት በመሆን እንዲከታተል ትዕዛዝ ይሰጣል።
ከአቅም በላይ የሆነ ምክንያት ማለት፦
በአካል ፍርድ ቤት ላለመቅረብ የሚያስችል ጽኑ የሆነ የጤና እክል፤
ሊገመት በማይችል ድንገተኛ የጉዞ ሂደት ላይ ለመድረስ አለመቻል፤
ሌሎች በቂና አሳማኝ የሆኑ በሰነድ ማስረጃ ሊረጋገጡ የሚችሉ ምክንያቶች ናቸው።
በቀጣይ ቀጠሮ ሲቀርቡ
ፍርድ ቤቱ ሰጥቶት በነበረው ቀጠሮ ሊቀርቡ ያልቻሉበትን ከአቅም በላይ የሆነውን ምክንያት ከሚያስረዱ የሰነድ ማስረጃዎች ጋር /መተርጎም ያለባቸውን በማስተርጎም/ የዋስትና ገንዘቡ ለመንግሥት ገቢ የማይሆንበትና መታሰር የሌለብዎት መሆኑን ማስረዳት ይጠበቅብዎታል።
ይግባኝ መብት ነው
©️ጠበቃ ቴዎድሮስ አብዲሳ
☎️ 09 10 61 69 50
በማንኛውም የፌዴራል ፍርድ ቤት
ጠበቃና የሕግ አማካሪ