👉 ስላሴ ክፍል_፩(አንድ)
""ሥላሴን አውቄ እጨርሳለው የምትል ከሆነ አዕምሮህን #ታጣዋለህ ፣ ሥላሴ የለም የምትል ከሆነ ደግሞ ሕይወትህን ታጣዋለህ""
በዚህ አባባል ውስጥ የምንረዳው ሥላሴን ማመን እና አለማመን የሕይወት እና የሞት ጉዳይ እንደሆነ ነው በአለም ላይ በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ሃይማኖቶች ቢኖሩም ሶስት አካላት ያሉት አንድ አምላክ (ሥላሴ) ያለው ግን የክርስትና እምነት ውስጥ ብቻ መሆኑ ለየት ያደርገዋል።
👉##ሥላሴ ማለት ምን ማለት ነው? ከየትስ መጣ?
ሥላሴ የሚለው ቃል የተገኘው ከግዕዝ ቃል ሲሆን፤ ይኸውም "ሠለሰ" ከሚል ግስ ትርጓሜውም "ሦስት አደረገ" ማለት ነው። ["ሠለሰ" - "ሦስት አደረገ"]፤ በኢንግሊዘኛውም [Tri-Unity] ከሚለው ሁለት ቃላቶች ተቆራኝተው የተገኘ ሲሆን "የሶስትነትን አንድነት ይገልፃል። [Tri-unity - Trinity];
ሥላሴ የሚለው ቃል በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በየትኛውም ክፍል ተፅፎ በፍፅም አይገኝም! ነገር ግን የአምላክ አንድነት እና በአካል ሶስትነት የሚለውን ትምህርት ለማብራራት የምንጠቀምበት ቃል ነው፤ይህንን የአምላክ አንድ መሆን እና በአካል ሶስት መሆን Trinity የተጠቀመው የመጀመሪያው ሰው ተርቱሊያን የተባለ የቤተክርስቲያን መሪ ነበር 160-220 ዓ.ም።
የሥላሴ ትምህርት እጅግ፣ ጥልቅ እንዲሁም ተመርምሮ የማይደረስበት እና የእግዚአብዚሔር ጥበብ ከሰው ልጅ ጥበብ እጅግ የላቀና የማይመረመር መሆኑን የሚያሳይ ነው። ሮሜ 11፡33-36
አለም ከመፍጠሩ በፊት የነበረ፣ መጀመሪያ እና መጨረሻ የሌለው ዘላለማዊ የሆነ በሰው የማይመረመር አንድ አምላክ እግዚአብሔር አለ። ይህም አምላክ አንድ ሲሆን ነገር ግን ሶስት በግብር (በሥራ ድርሻ) የተከፋፈሉ አካሎች አሉት። እነዚህም ሶስቱ አካላት አብ(አባት)፣ ወልድ(ልጅ) እና መንፈስ ቅዱስ እንደሆኑ ቅዱሱ መጽሐፍ በግልፅ ይናገራል።
##የሥራ ድርሻን በተመለከተ
#አባት (God the Father) == እቅድ አውጭ (the planner, Designer ሲሆን
#ልጅ (God the Son) == እቅድ አስፈፃሚ (Agent)
#ቅዱሱ መንፈስ (God the Holy Spirit) == ገላጭ, አካል አልባሽ (the Revealer) ነው።
ለምሳሌ
1==በፍጥረት ታሪክ መጀመሪያ ሶስቱም አካላት በስራ ድርሻቸው ሲሰሩ እናያለን
# አባት === አለማትን መፍጠር ፈለገ =ዕብ 1፡2
# ልጅ ==== ይሁን እያለ ይናገር ጀመር =ቆላስ 1:15-17, ዮሐ 1፡3
# መንፈስ ቅዱስ == የሚነገረውን ቃል አካል ያለብሰው ጀመር ...ዘፍ 1፡2
2==በማዳን ስራ የሶስቱም አካላት የስራ ድርሻ....
#አባት = የሰው ልጆችን ለማዳን ወደደ =ዮሐ 3፡16
#ልጅ = የሰው ልጆችን ለማዳን ሰው ሆነ=ዮሐ 1፡14
#መንፈስ ቅዱስ = የአዳኙን ስጋ በድንግሊቱ በማርያም ማህፀን አዘጋጀ = ማቴ 1፡18, ሉቃ 1፡35
የሥላሴን አስተምህሮ የምናጠናበት ምክንያቶች
1==የምናመልከውን እንድናውቅ (በመረዳት ማምለክ እንዲሆንልን ሳያውቁ ከማምለክ ራስን ለመጠበቅ ። ዮሐ 4፡22
2== ስለ ክርስቶስ ለማወቅ እና ራስን ከተቃዋሚው መንፈስ ለመጠበቅ። 1ዮሐ 4፡1-4
3== ስለ መንፈስ ቅዱስ አካል ያለው መለኮት ሊከበር እና ሊሰገድለት እንደሚገባ እና ለክርስትና ሕይወታችን ከእርሱ ጋር ያለንን ግንኙነት ለማጠናከር ነው።
የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ የእግዚአብሔርም ፍቅር የመንፈስ ቅዱስም ኅብረት ከሁላችሁ ጋር ይሁን። አሜን። 2 ቆሮንቶስ 13 14
👉ይቀጥላል 👇👇
@christiandoctrine