በሌ/ጄ ይልማ መርዳሳ የተመራ ልዑክ በአፍሪካ የመጀመሪያ የሆነውን ኤር ባስ ኤ350-1000 አውሮፕላን ለመረከብ ፈረንሳይ ገባ
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 24፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢፌዲሪ አየር ኃይል ዋና አዛዥና የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቦርድ ሰብሳቢ ሌተናል ጄኔራል ይልማ መርዳሳ የተመራ ልዑክ ኤር ባስ ኤ350-1000 የመንገደኞች አውሮፕላንን ለመረከብ ፈረንሳይ ገብቷል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በቅርቡ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት በሰጡት ማብራሪያ አየር መንገዱ 124 አውሮፕላኖችን ለመግዛት ማዘዙን መናገራቸው ይታወቃል።
በተጨማሪም አየር መንገዱ በዓመት እስከ 130 ሚሊየን መንገደኞችን ማስተናገድ የሚችል ግዙፍ የአውሮፕላን ማረፊያ ለመገንባት እንቅስቃሴ መጀመሩም አንስተዋል።
ይህም የኢትዮጵያ አየር መንገድን በአፍሪካ ትልቁ የአውሮፕላን ባለቤት ብቻ ሳይሆን ግዙፍ የአውሮፕላን ማረፊያ ያለው ተቋም ያደርገዋል፡፡
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአፍሪካ የመጀመሪያ የሆነውን ኤ350-1000 "Ethiopia land of origins" የተሰኘ የመንገደኞች አውሮፕላን ከኤር ባስ ኩባንያ በቅርቡ እንደሚረከብ መግለጹ ይታወሳል።
በዛሬው ዕለትም ሌ/ጄ ይልማ መርዳሳ፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈጻሚ መስፍን ጣሰው እና ሌሎች የአየር መንገዱ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች አውሮፕላኑን ከኤር ባስ ኩባንያ ለመረከብ ፈረንሳይ ገብተዋል።
የኤር ባስ ኩባንያ ዋና መስሪያ ቤት የሚገኝበት ቱሉስ ከተማ ሲደርሱም የኤር ባስ ኩባንያ አመራሮች አቀባበል አድርገውላቸዋል።