የኢትዮጵያና የሶማሊያ ድርድር በስኬት ተጠናቀቀ
አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 2/ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) - -በቱርኪዬ ፕሬዚዳንት ረሲፕ ጣይብ ኤርዶሃን አደራዳሪነት በአንካራ የተካሄደው የኢትዮጵያ እና የሶማሊያ ድርድር ተጠናቀቀ፡፡
ጠቅላይ ሚኒትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በዚህ ወቅት እንዳሉት የኢትዮጵያና የሶማሊያ ህዝቦች በቋንቋ በባህል እና በደም የተሳሰሩ መሆናቸውን አንስተው አገራቸው ለጋራ ሰላምና ልማት ከሶማሊያ ጋር ለመስራት ቁርጠኛ መሆኗን ተናግረዋል፡፡
ኢትዮጵያ የባህር በር በሰላማዊ መንገድ ለማግኘት የምታደርገውን ጥረት ለቀጣናው ምጣኔ ሃብታዊ እና ማህበራዊ ትስስር የጎላ ሚና እንደሚጫወት አንስተዋል
የሶማሊያው ፕሬዚዳንት ሃሰን ሼክ ሞሃሙድ በበኩላቸው ለሁለቱ ሃገራት ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ሰላም ቁልፍ ጉዳይ መሆኑን አንስተው ከኢትዮጵያ መንግስት እና ህዝብ ጋር በጋራ ጉዳዮች ላይ በትብብር ለመስራት ቁርጠኛ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡
መንግስታቸው የኢትዮጵያ ወታደሮች ለሶማሊያ ሰላም መጠበቅ የከፈሉትን መስዋዕትነት እንደማይዘነጋው እና በቀጣይም ሰላምን ለማፅናት ለሚረገው ጥረት ቁርጠኛ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡
ፕሬዚዳንት ረሲፕ ጣይብ ኤርዶሃን:- ሁለቱ ሃገራት የፈረሙት የስምምነት ሰነድ ትብብርን፣ ምጣኔ ሃብታዊ ልማትን እና ብልጽግናን የሚያረጋግጥ መሆኑን ተናግረዋል፡፡