ኢትዮጵያ የቡድን-20 የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ፎረም ላይ እየተሳተፈች ነው
አዲስ አበባ፣ የካቲት 13፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በደቡብ አፍሪካ ጆሃንስበርግ ዛሬ በተጀመረው የቡድን-20 የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ፎረም ላይ በውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) የተመራ የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን እየተሳተፈ ነው።
“አንድነት፣ እኩልነት እና ዘላቂነት” በሚል ቀጥታ ፍቺ ባለው መሪ ሃሳብ እየተካሄደ ያለው የውይይት መድረክ በደቡብ አፍሪካ ፕሬዚዳንት ሲሪል ራማፎሳ በይፋ ተጀምሯል።
ጌዲዮን (ዶ/ር) በንግግራቸው፥ ዓለም በጂኦፖለቲካል ውጥረቶች፣ ግጭቶች እና የአየር ንብረት ለውጥ የተለያዩ ፈተናዎች ውስጥ እየገባች ነው ብለዋል።
በትብብር ትክክለኛ ሚዛን ማምጣት አስፈላጊ መሆኑን ጠቁመው፥ የቡድን-20 አባል ሀገራትን ጨምሮ በዓለም አቀፍ ማህበረሰብ መካከል የጋራ ትብብር እንደሚያስፈልግ ገልፀዋል፡፡
በፎረሙ በፈረንጆቹ 2025 በደቡብ አፍሪካ ፕሬዚዳንት በተዘረዘሩት የቡድን-20 የትኩረት አቅጣጫዎች ላይም ይወያያል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
ይህም ሁሉን አቀፍ የኢኮኖሚ ልማት፣ የምግብ ዋስትና፣ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ እና የኢነርጂ ሽግግርን እንደሚያጠቃልልም ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
በአፍሪካ ለመጀመሪያ ጊዜ እየተካሄደ የሚገኘው ፎረሙ፥ ሁለት ቀናት ይቆያል ተብሏል፡፡