ፀሐይ-2 አውሮፕላን የመጀመሪያ የሙከራ በረራዋን በስኬት አከናወነች
አዲስ አበባ፣ የካቲት 14፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በአየር ኃይል የተሰራችው ፀሐይ - 2 የስልጠና አውሮፕላን የመጀመሪያ የሙከራ በረራዋን በስኬት ማከናወኗ ተገልጿል፡፡
ፀሐይ -2 አውሮፕላን ለበረራ ማሰልጠኛ እና ለሌሎች አገልግሎት መዋል የምትችል ሲሆን÷ የተሰጣትን ግዳጅ በብቃት መፈፀም የሚያስችላትን የዘመኑን የአቪዬሽን ቴክኖሎጂ ታጥቃለች ተብሏል፡፡
የአውሮፕላኗ ስኬታማ የሙከራ በረራ አየር ኃይሉ የደረሰበትን የከፍታ ጉዞ እንደሚያሳይ ነው የተመላከተው፡፡
በቀጣይነት ወደ ምርት ሂደት ለመሸጋገር ፋብሪካውን የማደራጀት፣ የመፈተሻ እቃዎችን የማሟላትና የሞያተኞችን አቅም የማጎልበት ሥራ በመከናወን ላይ መሆኑ ን የመከላከያ ሠራዊት ማህበራዊ ትስስር ገጽ መረጃ ያመላክታል፡፡
የትራንስፖርት አውሮፕላን ስኳድሮን አዛዥና አብራሪ እንዲሁም የፀሃይ -2 የሙከራ በረራን በስኬት ያካሄዱት ሻለቃ ፍቃዱ ደምሴ ÷ አውሮፕላኗ የበረራ አቅሟ አስተማማኝና ተቋሙ ለያዘው የወደፊት ራዕይ ጉልህ አስተዋፅኦ የምታበረክት መሆኗን ገልፀዋል፡፡