የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለመቄዶንያ የ30 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 30፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለመቄዶንያ የአረጋውያን እና አዕምሮ ሕሙማን መርጃ ማዕከል 30 ሚሊየን ብር አበርክቷል።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ፕሬዚዳንት አቶ አቤ ሳኖ 30ኛ ቀኑን በያዘው የመቄዶንያ የእርዳታ ማሰባሰቢያ ዝግጅት ላይ በመገኘት የባንኩን ድጋፍ አስረክበዋል።
አቶ አቤ በዚህ ወቅት እንዳሉት፥ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሠራተኞች እና ማኔጅመንት አባላት የተሰበሰበ 18 ሚሊየን ብር እንዲሁም ባንኩ 12 ሚሊየን ብር ወጪ በማድረግ ድጋፍ ተደርጓል።
መቄዶንያ እያከናወነ የሚገኘው የበጎ አድራጎት ሥራ የሚደነቅ እና የሚበረታታ መሆኑን ተናግረዋል።
አቶ አቤ ሁሉም ዜጋ እንደየአቅሙ ለማዕከሉ ድጋፍ እንዲያደርግ ጥሪ ማቅረባቸውንም የባንኩ መረጃ ያመላክታል።
የመቄዶንያ መስራችና የበላይ ጠበቂ ቢኒያም በለጠ በበኩላቸው ፥የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የመቄዶንያ ቋሚ ደጋፊ መሆኑን ገልጸው፤በየጊዜው ለማዕከሉ ለሚያደርገው ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል።