ቼልሲ ማንቼስተር ዩናይትድን አሸነፈ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 8፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በ37ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ቼልሲ ማንቼስተር ዩናይትድን 1 ለ ዐ አሸንፏል።
የምዕራብ ለንደኑን ክለብ ቼልሲ ብቸኛ የማሸነፊያ ግብ ማርክ ኩኩሬያ በሁለተኛው አጋማሽ ከመረብ አሳርፏል።
ቼልሲ የምሽቱን ድል ተከትሎ ነጥቡን 66 በማድረስ በኒውካስል ዩናይትድ በግብ ክፍያ ተበልጦ 4ኛ ደረጃ ላይ መቀመጥ ችሏል።
በውድድር አመቱ በፕሪሚየር ሊጉ ብቻ 18ኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ማንቼስተር ዩናይትድ 16ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።
ቀደም ብሎ ምሽት 3:30 በተደረገው ጨዋታ አስቶን ቪላ ቶተንሃም ሆትስፐርን 2 ለ 0 በማሸነፍ ለሻምፒየንስ ሊግ ተሳትፎ ወሳኝ 3 ነጥብ አሳክቷል።
የአስቶንቪላን ግቦች ኮንሳ እና ካማራ በሁለተኛው አጋማሽ ከመረብ አሳርፈዋል።
ቪላ ነጥቡን 66 በማድረስ በኒውካስል ዩናይትድና ቼልሲ በግብ ክፍያ ተበልጦ 5ኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ፥ ሽንፈት ያስተናገደው ቶተንሃም በነበረበት 17ኛ ደረጃ ላይ ለመቆየት ተገዷል።