#ከቅጣት ለማምለጥ ሲል ጎኑን በጦር ወጋው፣ ዓይኑንም....
ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተሰቀለበት ስፍራ ቀራንዮ-ጎልጎታ አባታችን አዳም የተቀበረበት እንደሆነ የቅድስት ቤተ ክርስቲያን አባቶችና በርካታ ዓለም አቀፍ የታሪክ ጸሐፍያን ይገልጻሉ።
ጲላጦስ አይሁድ እንዲሰቅሉት አሳልፎ የሰጣቸው ጠዋት 3:00 ላይ ነው። በፍርድ ሒደቱ ላይ ተጽእኖ ለማሳረፍ አይሁድ ሕዝቡን ሁሉ ሲያስተባብሩ፣ የሀሰት ምስክርም አቁመው ነበር። መስቀል አሽክምው እየገረፉ ወስደው በእርጥብ እንጨት ሰቀሉት። ሰውን ሊያድን ሰው የሆነው ጌታ፣ በሰው ልጅ ይሙት በቃ ተፈረደበት።
በዚህ ሁሉ ክፋታቸው ወስጥ ያልተስማሙ፣ ኢየሱስ ንጹህና ጻድቅ ሲሆን በግፍ እንደተገደለ የሚያምኑ ድርጊቱንም ያልደገፉ የራሳቸው የአይሁድ ወገኖች ነበሩ። በበጎ ምግባር መሳተፍና ከክፉ ምግባር መራቅ የየትኛውም ቅን ልብ ያለው ሰው መገለጫ ነው።
ከእነዚህ አንዱ ለንጊኖስ የተባለው አንድ ዐይና ወታደር ነው። ይህ ፈረሰኛ በዚያች ዕለተ አርብ በጌታ ላይ የሚፈጸመውን ግፍ ላለማየት ከከተማ ወጥቶ በጫካ ውስጥ ዋለ። ነገሮች አብቅተዋል ብሎ አመሻሹ ላይ ወደ ከተማ ሲግባ፣ የአይሁድ አለቆች ከቀራንዮ ሲመለሱ ከመንገድ አገኘቱ፤ ስለምን ከመሢሑ ሞት አልተባበርክም አሉት? እርሱም ምንም ስላላገኘሁበት አላቸው፡፡ ከዚያም በኋላ እንደሕጋቸው እንደሚቀጡት ቢነግሩት እየሮጠ ሔዶ የጌታችንን ጎን ሲወጋው ደሙ በዐይኑ ላይ ሲፈናጠቅ ወዲያው ዐይኑ በራለት።
ከጌታችን ጎንም ትኩስ ደምና ውሃ ፈሰሰ፣ መላእክትም ደሙን በጽዋ ቀድተው በዓለም ላይ ረጩት፤ ውሃውም ለጥምቀታችን ሆነ። ይህ መሠረት ሆኖ ዛሬ ቤተ ክርስቲያን የሚታነጸው የጌታችን ደም የነጠበበት ነው፡፡ ለዚህም ነው ቅዱስ ጳውሎስ "አሁንም በገዛ ደሙ የዋጃትን የእግዚአብሔር ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ትጠብቁ ዘንድ መንፈስ ቅዱስ እናንተን ጳጳሳት አድርጎ ለሾመባት ለመንጋው ሁሉና ለራሳችሁ ተጠንቀቁ" ያለው (ሐዋ 20÷28)፡፡
ለንጊኖስ የልቡናው ቅንነት ነው የታየለት፤ ጎኑን መውጋቱ ዓይኑን ሲያበራለት ለኛ ደግሞ ለጥምቀታችን የሚሆነንን ማየ ገቦና በዓለም የተረጨ ደሙን አስገኘልን። የእኛስ የልቡና ቅንነት እንዴት ይገለጻል? በዘመናችን ዐይነ ልቡናችንን የሚያበራ በጎ ምግባር የምናደርግበት እድል አለና የቤተ ክርስቲያንን ጥሪ እንስማ።
ድጋፍ ለማድረግ:-ሙትአንሳ ማር ቅዱሰ ሚካኤል አድነት ገዳም
ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391
ወይም
አቢሲኒያ ባንክ
141029444
የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444