2 ወጣት ሴቶች በቡድን ሲደፈሩ የሚያሳይ ቪዲዮ በቴሌግራም እየተዘዋወረ ነው፣ ድርጊቱን የፈፀሙት እየተፈለጉ ነው።
በኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ ወላጋ ዞን ነቀምቴ ውስጥ ሁለት ታዳጊ ልጆችን በቡድን በመሆን የደፈሩ ወጣቶች እስካሁን ድረስ በፖሊስ ቁጥጥር ስር አለመዋላቸውን ፖሊስ እና የአካባቢው ባለሥልጣን ለቢቢሲ ተናገሩ።
የነቀምቴ ከተማ ፖሊስ አዛዥ የሆኑት ኮሚሽነር ሻሎ ገለታ ወንጀሉ የተፈጸመው ነቀምቴ ከተማ ውስጥ ባለፈው መስከረም ወር ላይ መሆኑን ለቢቢሲ አረጋግጠዋል።
ነገር ግን ወንጀሉን ከፈጸሙት መካከል “እስካሁን ድረስ በቁጥጥር ስር የዋለ የለም። ነገር ግን ሁለት ተጠርጣሪዎችን እየፈለግን ነው” ሲሉ ኮሚሽነሩ ተናግረዋል።
ሁለቱ ታዳጊ ልጆች በቡድን ሲደፈሩ የሚያሳየው ተንቀሳቃሽ ምሥል ባለፉት ቀናት በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ በስፋት ከተሠራጨ በኋላ በርካቶች ቁጣቸውን እየገለፁ ነው።
ማኅበራዊ ሚዲያ ላይ የተጋራው ተንቀሳቃሽ ምሥል ላይ ወንጀሉ የተፈጸመው ጊምቢ ከተማ ነው ቢባልም ነቀምቴ ከተማ መፈጸሙን ጥቃቱ ከደረሰባት ታዳጊ መካከል አንዷ ማረጋገጧን የፖሊስ ኃላፊው ተናግረዋል።
የከተማው የሴቶች እና ሕጻናት ጉዳይ ቢሮ በበኩሉ ወንጀሉ መፈጸሙን እንሚያውቅና ተጠርጣሪዎቹን ለፍርድ እንዲቀርቡ ጉዳዩን በቅርበት እየተከታተለ መሆኑን ለቢቢሲ ገልጿል።
የቢሮው ኃላፊ የሆኑት መብራቴ ባጫ በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ የተጋራውን ቪድዮ እንደተመለከቱ እና ምርመራ መጀመራቸውን ተናግረዋል።
“መረጃው እንደደረሰን ማጣራት ጀምረናል። መጀመሪያ ወንጀሉ ጊምቢ ውስጥ መፈጸሙ ቢነገርም አሁን ግን እዚሁ ነቀምቴ ከተማ ውስጥ መፈፀሙን አረጋግጠናል” ብለዋል።
በቪድዮው ላይ በቡድን ሲደፈሩ የሚታዩት ሁለቱ ታዳጊ ሴቶች ተማሪዎች መሆናቸውን እና ከታዳጊ ሴቶቹ በዕድሜ ተለቅ የሚሉ መሆናቸው የተነገረው ወንጀሉን የፈጸሙት ወንዶች ማንነት አልታወቀም።
ከዚህ የወንጀል ድርጊት ጋር በተያያዘ ምንም አንኳ ፖሊስ ሁለት ተጠርጣሪዎችን ለይቶ ለመያዝ ጥረት እያደረገ እንደሆነ ቢገልጽም፣ የነቀምቴ ከተማ የሴቶች እና ሕጻናት ጉዳይ ኃላፊዋ ግን አራት ተጠርጣሪዎችን መለየታቸውን ይናገራሉ።
“በቪድዮው ላይ የሚታዩ አራት ጥቃት አድራሾችን ለይተናል። የባጃጅ ሹፌሮች መሆናቸውንም ደርሰንበታል። አንዱ ባጃጁን ጥሎ የጠፋ ሲሆን የፀጥታ አካላት ክትትል አድርገው በቁጥጥር ስር እንዲውሉ ተነጋግረናል” ብለዋል።
አክለውም ጥቃቱ የደረሰባቸውን ታዳጊዎች ቤተሰቦች ለማግኘት ጥረት ማድረጋቸውን እና አንዷ የሕክምና ድጋፍ እንድታገኝ መደረጉን ተናግረዋል።
እንዲህ ዓይነት ወንጀሎች ሲፈጸሙ ተከታትሎ ጥቃት አድራሾችን ለፍትህ ማቅረብ አስፈላጊ መሆኑን የተናገሩት የቢሮ ኃላፊዋ ሴቶች በነጻነት ወጥተው እንዲገቡ የሕግ የበላይነት መረጋገጡን እንከታተላለን ብለዋል።
አክለውም ይህ ዓይነት ከማኅበረሰቡ ሞራል ያፈነገጠ ተግባር እንዳይደገም ቢሯቸው የበኩሉን እንደሚሠራም ተናግረዋል።
የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን የኦሮሚያ ቅርንጫፍ ባልደረባ በዳሳ ለሜሳ በበኩላቸው መረጃው እንደደረሳቸው እና እየተከታተሉ መሆኑን ለቢቢሲ ገልጸዋል።
ይህ በታዳጊ ሕጻናቱ ላይ በደቦ የተፈጸመውን ወንጀል የሚያሳየው ቪዲዮ ላይ የጥቃቱ ሰለባዎች ገጽታ የሚታይ ሲሆን፣ የወንጀሉ ፈጻሚዎች ፊት ግን ለመለየት በሚያስችል ሁኔታ አይታይም።
ድርጊቱ ቁጥቋጦ በሆነ ስፍራ ላይ ሲፈጸም የወንጀሉ ፈጻሚዎች እንዲሁም ቪዲዮውን የሚቀርጸው ሰው ሲነጋገሩ ይሰማል።
ባለፈው ሳምንት ማብቂያ ቀናት በማኅበራዊ ሚዲያ የትስስር መድረኮች ላይ በስፋት ሲዘዋወር የነበረው ይህ የወንጀል ድርጊት ቪዲዮን የተመለከቱ ሰዎች የተፈጠረባቸውን ድንጋጤ እና ቁጣ እየገለጹ ነው።
ይህ በሴቶች በተለይም በሕጻናት ላይ የሚፈጸመው የመድፈር ወንጀል ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እየተደጋገመ መሆኑን ባለፉት ዓመታት የወጡ ሪፖርቶች ያመለክታሉ።
በዚህም ሳቢያ ወላጆች የልጆቻቸው ደኅንነት በእጅጉ እንደሚያሳስባቸው በተለያዩ መንገዶች እየገለጹ ነው።
ዘገባው የቢቢሲ አማርኛ ነው።