"አጋቾቹ ከጠየቁት 2 ሚሊዮን ብር 1.4 ሚሊዮን ብር ከፍለን ሌላውን እየፈለግን ነበር ግን ቀድመው ጀናዛቸውን ላኩልን"
በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ደራ ወረዳ ገንዳ አረቦ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በታጣቂዎች ታግተው የነበሩት የሀጂ አህመድ መስጅድ ኢማም ሼይኽ ሙሀመድ መኪን ሸይኽ ሙሀመድ አሪፍ አብረዋቸው ታግተው ከነበሩት 12 የሚሆኑ የቅርብ ቤተሰቦቻቸው ጋር መገደላቸው ተሰምቷል።
የዛሬ ወር ገደማ ሸይኹ የሱብኺ ሶላት አሰግደው በሚመለሱበት ወቅት ነበር እሳቸውንና ቤተሰቦቻቸውን ጨምሮ ከ30 በላይ የአንድ አካባቢ ሰዎች በታጣቂዎች መታገታቸው የተገለጸው።
በወቅቱ ከታገቱት ሰዎች በተጨማሪ ከ80 በላይ የሚሆኑ የቀንድ ከብቶች መዘረፋቸውም ተገልጿል። በተደረገው የገንዘብ ድርድር ከታገቱት ሰዎች መካከል የሸይኹ እናትና ባለቤታቸው ጨምሮ ጥቂት ሰዎች የተለቀቁ ቢሆንም ሼይኽ ሙሀመድ መኪንን ጨምሮ 12 የሚሆኑ የቅርብ ቤተሰቦቻቸው ተገድለዋል።
አጋቾቹ ከጠየቁት 2 ሚሊዮን ብር 1.4 የሚሆነው ከፍለው ቀሪውን እየፈለጉ እንደነበር የተገለፁት ቤተሰቦች ነገር ግን ቀድመው ጀናዛ ላኩልን የተፈፀመብንን ከባድ ግፍ ነው ያጣነው ታላቅ አሊም፣ አስታራቂ ሽማግሌ የነበሩ ሰው ነበር ያለምንም ምክንያት ነው በግፍ የተገደሉት" ሲሉ ቤተሰቦቻቸው ገልጸዋል።
ዘገባው የሀሩን ሚዲያ ነው።