“በቆባቸው ግድግዳውን ቢመቱት ለሁለት ተሰነጠቀ”
ታላቁ ጻድቅ አባት አባ ሣሉሲ ዜና ሕይወታቸው እጅግ ከሚያስገርሙ ገዳማውያን አንዱ ናቸው። መጽሐፈ ስንክሳር እንደሚገልጸው የዘመነ ከዋክብት ፍሬ ከሚባሉት ጻድቃን አንዱ ሲሆኑ በነበሩበት ገዳም የሚታወቁት ግን 'የማይጾመው፣ የማይጸልየው፣ ሥራ ፈቱ መነኩሴ' በሚል ነበር።
ገዳሙ ውስጥ ከሚኖሩ መነኮሳት መካከል አንድም ቀን ቢሆን አባ ሣሉሲ ሲጸልዩና ሲሰግዱ ያያቸው የለም። ሁሌ ብቻ እንደ ሞኝ ቁጭ ብለው ያኝካሉ። በዚህ ምክንያትም ሥጋ ወደሙን ወስደው አያውቁም።
አንድ ቀን ግን በገዳሙ በዓል ላይ አበምኔቱና መነኮሳቱ መከሩ። "አባ ሣሉሲን አሥረን አውለን ቢያንስ ለቁርባን እናብቃቸው።" ሲሉ ወሰኑ። በውሳኔው መሠረትም በጧት ሒደው ጻድቁን አሠሯቸው።
አባ ሣሉሲም "ፍቱኝ ቁርሴን ልብላበት?" ሲሉ ተቆጡ። መነኮሳቱ ግን "ሳትቆርብ አንለቅህም።" አሏቸው። በዚህ ጊዜ ጻድቁ ቆባቸውን አውልቀው "እመቤቴ የሰው ልጅስ ጨካኝ ነው። አንቺ ግን ርኅርኅት ነሽ።" ብለው በቆባቸው ግድግዳውን ቢመቱት ለሁለት ተሰነጠቀ።
እርሳቸውም ሁለት ክንፍ አውጥተው በረው ተሰወሩ። ባዩት ነገር የደነገጡ መነኮሳት እያለቀሱ ሦስት መቶ ጊዜ "እግዚኦ....." አሉ። በዚህ ጊዜ የጻድቁን ቆብ አገኙ። በዚህች ቆብም አጋንንትን አሳደዱ ተአምራትንም ሠሩ።
አባ ሣሉሲ ግን ሃያ አራት ሰዓት ሙሉ በተመስጦ በልባቸው ስለሚጸልዩና ይህ ቅድስናቸው እንዳይታወቅ ነበር የሚጥሩት፡፡ በጧት ተነስተው የሚያኝኩትም ደረቅ ሣር እንጂ ምግብ አልነበረም። ከውዳሴ ከንቱ መራቅ ማለት ይሔው ነው።
ስንቶቻችን ጥቂቷን በጎነታችን ሰው ሁሉ እንዲያውቅልን ስንጥር ገዳማውያን አባቶቻችን ግን ጤዛ ልሰው፣ ድንጋይ ተንተርሰው፣ ግርማ ሌሊቱን ጸብአ አራዊቱን ታግሰው ሀገርንና ሕዝብን ሌት ተቀን በጸሎት ሊያስምሩ እየተጉ መንፈሳዊ ጸጋና ክብር ሲያገኙ ትሕትናቸው ይበልጥ ከፍ ይላል፡፡
የጸሎታቸው ረድኤት አብሮን እንዲሆን ገዳማትን ማገዝ ደግሞ የእኛ ድርሻ ነው፡፡ የገዳማውያኑን በረከትና ጸሎት አይለየን፡፡
ድጋፍ ለማድረግ :-ሙትአንሳ ማር ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት ገዳም
ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391
አቢሲኒያ ባንክ
141029444
ለተጨማሪ መረጃ:-
የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957
ወይም 0938644444