#ሙት ያስነሳው ታላቅ ምስጋና
ለእመቤታችን ትልቅ ፍቅር ነበረው አባታችን አባ ሕርያቆስ ቅዳሴ ማርያን በመንፈስ ቅዱስ ተቃኝቶ ሲደርስ እንደ ውሃ ሙላት፣ እንደ ኃያል ሞገድ በተገለጸለት ወቅት ቆሞ እየቀደሰ ነበር፡፡ በአበምኔትነት በሚያስተዳድረው ገዳመ ብሕነሳ በቀለም ትምህርቱ ያልገፋ በመሆኑ የሚንቁት “እውቀት የለህም ብለው ሊሽሩት በማሰብ ቀድሰህ አቁርበን ብለውት ቅዳሴውን እያካሔደ ከፍሬ ቅዳሴው ሲደርስ ነው ድንቁ መገለጥ የሆነለት፡፡ የልቡ ደርሶ እመቤታችንን ያመሰገናት፡፡
በእውቀታቸው ማነስ፣ በልብሳቸው መቆሸሽ፣ በአካላቸው መንኳሰስ ባንንቃቸው እንኳን ብዙም ክብር የማንሰጣቸው ባሕታውያን አባቶች ጸሎታቸው ምን ያህል ድንቅ ተአምር እንደሚሰራ ልንረዳው ይገባል፡፡ በአባ ሕርያቆስ የቅዳሴ ማርያም ድርሰትም የተከሰተው ተአምር ይህን ያሳያል፡፡
እርሱ መንፈስ ቅዱስ በገለጸለት ጥበብ የማርያምን ምስጋና ሲናገር የሚጠሉት፣ ሊሽሩት ፈልገው ቀድሰህ አቁርበን ያሉት “የሚያውቀውን ቀለም እንኳን አከናውኖ መናገር ሳይችል አዲስ ድርሰት እደርሳለሁ ብሎ ይቀባጥራል” አሉት፡፡ የሚወዱት ግን “እንዲህ ያለ ነገር ከመንፈስ ቅዱስ እንጂ ከስጋዊ ሰው አይፈልቅምና ጽፈን ደጉሰን እንያዘው” አሉ፡፡
በሀገራቸው አዲስ ድርሰት ሲኖር የመንፈስ ቅዱስ ስራ መሆኑን የሚያዩበት ስርዓት አለና በዚያው መሰረት፤ ጽፈው ደጉሰው ወደ ውሃ ውስጥ ከተቱት ምንም ሳይሆን ወጣ፣ እሳት ውስጥ ከተቱት ሳይቃጠል ወጣ፣ በህሙም ላይ ጣሉት ፈወሰው፡፡ ይህ በቀደመ ስርዓታቸው በቂ ሒደት ቢሆንም የአባ ሕርያቆስ የቅዳሴ ማርያምን ድርሰት ግን በሙት ላይ ቢጥሉት ሙት አስነስቷል፡፡ ከዚያ ጊዜ ጀምሮም በቤተ ክርስቲያናችን ካሉት ከ14ቱ ቅዳሴያት አንዱ ሆኖ በሊቃውንቱ ተይዟል፡፡
ገዳማውያን አባቶቻችን ንዒ ባሉበት ጸሎታቸው፣ ሰዓሊ ለነ ቅድስት ባሉበት በረከታቸው እንድናተርፍ ገዳማቱን እና፦ጠናክር፣ ለሀገርና ለወገን ሲጸልዩ እኛ ደግሞ ካለን ላይ አካፍለን በዓታቸውን እናጽና፡፡
ድጋፍ ለማድረግ፦ሙትአንሳ ማር ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት ገዳም
ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391
ወይም
አቢሲኒያ ባንክ
141029444
የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444