#የእግዚአብሔር ሰራዊት አለቃ ሆኜ ወዳንተ መጥቻለሁ
“በጎዳናህ ሁሉ ይጠብቁህ ዘንድ መላዕክትን ስላንተ ያዝዛቸዋል በእጃቸውም ይደግፉሃል፡፡” ይላል ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት፡፡ ይልቁንም የመላእክት ሁሉ አለቃቸው የሚሆን ቅዱስ ሚካኤል ከእግዚአብሔር ተልኮ በርካቶችን ሲጠብቅ በቅዱስ መጽሐፍ ተመልክተናል፡፡ በየዓመቱ በህዳር በ12 ቀን በዓለ ሲመቱ የሚከበረው ቅዱስ ሚካኤል የዋህ፣ ርህሩህ፣ አዛኝ፣ ለወዳጆቹ ቅርብ፣ የሰው ሁሉ ልጆችን ጠላት በእሳት ሰይፍ መትቶ የጣለው በክንፎቹ ረድኤት የሚጠብቀንም ነው፡፡ “በሰማይ ብርቱ ሰልፍ ሆነ ሚካኤልና መላአክቱም ዘንዶውን ተዋጉት ዘንዶውም አልቻላቸውም። ከዚያም በኃላ በስማይ ቦታ አልተገኘለትም” ተብሎ በራዕይ 12÷7 እንደተጻፈ ዲያብሎስ በትዕቢቱ ከወደቀ በኋላ የመላዕክት ሁሉ አለቃ የሆነው ቅዱስ ሚካኤል ነው፡፡
አምላካቻን እግዚአብሔር ወደር የማይገኝለት ኃያል፣ የሚመስለው የሌለ ብርቱ፣ ዘመን የማይቆጠርለት ዘለዓለማዊ ነው፡፡ መላዕክቱን መንፈስ የሚላኩትን የእሳት ነበልባል የሚያደርጋቸው ተብሎ እንደተጻፈ የኃይሉ መገለጫ ከሆኑት አንዱ ናቸው ቅዱሳን መላዕክት፡፡ ይልቁንም የስሙ ትርጓሜ “ማን እንደ አምላክ ማለት የሆነው ታላቁ አለቃ ቅዱስ ሚካኤል በርካታ ድንቅ ስራ ሰርቷል፡፡ በበዓለ ሲመቱም በየዓመቱ ከሕዳር 12 እስከ የአእላፍ መላእ በዓል እስከሚከበርበት ሕዳር 13 ለሰው ልጆች ሁሉ ከአምላካችን ምሕረት ይለምናል፡፡ ስፍር ቁጥር የሌላቸው ነፍሳትንም ከሲዖል ያወጣል፡፡
ሕዳር 12 እስራኤላውያንን ከግብጽ ባርነት መርቶ ያወጣበትም ቀን ነው፡፡ 430 ዘመን በባርነት ከቆዩባት ምድረ ግብጽ በሙሴ መሪነት ሲጓዙ፣ ግርማ ሌሊቱን በብርሃን አምድ፣ የቀኑን ሐሩር ደግሞ በደመና ጋርዶ ወደ ተስፋይቱ ምድር ያገባቸው እርሱ ቅዱስ ሚካኤል ነው፡፡ ከሙሴ በኋላ እስራኤልን የመራው ነቢዩ ኢያሱም ኢያሪኮን ለመያዝ ሲሰናዳ የመላእክት ሁሉ አለቃቸው የሚሆን የከበረ ገናና መልአክ ቅዱስ ሚካኤል የተመዘዘ ሰይፍ በእጁ ይዞ ተገለጸለት፡፡ እርሱም በምድር ላይ በግንባሩ ተደፍቶ ሰገደለት፡፡ ወደ እርሱ ቀርቦም “አንተ ከእኛ ወገን ነህ ወይስ ከጠላቶቻችን?” ሲል ጠየቀው፡፡ እርሱም “አይደለሁም ነገር ግን የእግዚአብሔር ሠራዊት አለቃ ሆኜ አሁንም ወደ አንተ መጥቻአለው አለው፡፡ ኢያሱ 5÷13፡፡ የኢያሪኮ ግምብን አፍርሶም ድልን አጎናጽፎታል፡፡
ለሚጠሩት ሰዎች ሁሉ ቅርብ የሆነው ቅዱስ ሚካኤል ዛሬም በዙሪያችን ከቦ ይጠብቀናል፣ ያድነንማል፡፡ ነብዩ ቅዱስ ዳንኤልም “በዚያም ዘመን ለሕዝብ ልጆች የሚቆመው ታለቁ አለቃ ሚካኤል ይነሳል።” እንዲል ሁሌም ጥበቃው ከኛ ጋር ነው፡፡ ከእግዚአብሔር በተሰጠው ቃል ኪዳን ልጆቹን ለመርዳት ቸል አይልም፡፡ ይልቁንም በዱር በገደል ጤዛ ልሰው፣ ድንጋይ ተንተርሰው፣ ዳዋ ለብሰው የሚኖሩትን ገዳማዊያን ዘወትር ይጠብቃቸዋል ጸሎታቸውንም ያሳርጋል፡፡ የእግዚአብሔር ሰራዊት አለቃ ሆኖ ወደ እነርሱ ይመጣል፡፡ ለእነዚህ ገዳማዊያንና ለገዳማቸው እገዛ በማድረግ የመልአኩ ጥበቃና የጸሎታቸው በረከት ተካፋይ እንሁን፡፡
ድጋፍ ለማድረግ:-ሙትአንሳ ማር ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት ገዳም
ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391
ወይም
አቢሲኒያ ባንክ
141029444
የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444