ከአዲስ አበባ ነዋሪዎች 75 በመቶዎቹ የቫይታሚን ዲ እጥረት እንዳለባቸው ጥናት አሳይቷል፡፡
ዓመቱን ሙሉ ፀሐይ በማያጣት ኢትዮጵያ በሽታ የመከላከል አቅምን ያዳክማል፣ ድብርትንም ያስከትላል ለተባለው የቫይታሚን ዲ እጥረት አብዝቶ የመከሰቱ ችግር የአኗኗር ዘይቤ ለውጥ እንደ ምክንያት ተጠቅሷል፡፡
ጥናቱ እንደ ሀገርም ከ50 በመቶ በላዩ ኢትዮጵያዊ የቫይታሚን ዲ እጥረት አለበት ይላል፡፡
የአጥንት መሳሳትን ጨምሮ የቫይታሚን ዲ እጥረት የሚያስከትላቸውን የጤና እክሎች ለመከላከል ቢያንስ በሳምንት አንድ ቀን ገላን በፀሀይ በማጋለጥ ለተወሰነ ደቂቃ መሞቅ እንደሚያስፈልግ ተመክሯል ሲል ሸገር ሬዲዮ ነው ያስነበበው።