#ቀድሞ በመንፈስ የሚያውቀውን ከሠላሳ ዓመታት በኋላ በአካል አየው
የስድሰት ወር ጽንስ አምላኩን አወቀውና ሰገደለት፤ እናቱ ቅድስት ኤልሳቤጥ ልትጠይቃ የመጣችውን፣ የዘመዷን፣ የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያምን ድምጽ በሰማች ጊዜ መንፈስ ቅዱስ ሞልቶባት “የጌታዬ እናት ወደኔ ትመጣ ዘንድ እንዴት ይሆንልኛል” እንዳለች ከሠላሳ ዘመን በኋላ ልጇ መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ “እኔ ባንተ እጅ ልጠመቅ ይገባኛል እንጂ አንተ በኔ እጅ ትጠመቃለሕን?” ብሎ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስን አምላክነት መሰከረ፡፡ በነቢዩ ቅዱስ ኢሳይያስ እንደተነገረው የጌታን መንገድ አዘጋጁ፤ ጥርጊያውንም አቅኑ፤ እያለ በምድረ በዳ የሚጮኽ ሰው ድምፅ እርሱ ነበር፡፡ በቅዱስ ሉቃስ ወንጌል 3÷3-6 እንደተነገረውም ቅዱስ ዮሐንስ *መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ!* እያለ እየሰበከ በዮርዳኖስ ዙሪያ ወዳለው አገር ኹሉ ወጣ፡፡
ዮሐንስ ማለት “እግዚአብሔር ጸጋ ነው” ማለት ነው፡፡ ትርጓሜ ወንጌልም መጥምቀ መለኮት ዮሐንስን ፍሥሐ ወሐሴት ተድላና ደስታ ይለዋል፤ ወላጆቹ በእርሱ መወለድ ተደስተዋልና፡፡ በዮርዳኖስ ወንዝ የንስሐ ጥምቀት ሲጢምቅም የይሁዳ አገር ሰዎች ሁሉ ኃጢአታቸውን እየተናዘዙ ከእርሱ ይጠመቁ ነበር፡፡ በጥፋታቸው ሲገስጻቸውም ምን ማድረግ እንዳለባቸው ጠየቁት እርሱም በመልካም ምግባርና በልግስና በእውነትና በርትዕ እንዲኖሩ ይነግራቸው ነበር፡፡ በዋናነት ግን ስለጌታችን ይነግራቸው ነበር፡፡ “እኔ ለንስሐ በውኃ አጠምቃችኋለሁ፤ ነገር ግን የጫማውን ጠፍር እንኳን መፍታት የማይገባኝ ከእኔ በኋላ የሚመጣው ከእኔ ይልቅ የሚበረታ እርሱ በመንፈስ ቅዱስና በውኃ ያጠምቃችኋል” አላቸው፡፡
ከዚህ ምስክርነት በኋላ ዮሐንስ ጌታ ሊጠመቅ ወደ እርሱ ሲመጣ ቢመለከት “የዓለምን ሁሉ ኃጢአት የሚያርቅ የእግዚአብሔር ልጅ” ብሎ መስክሮለታል፡፡ ጌታችንንም “እኔ በአንተ ልጠመቅ ያስፈልገኛል፣ አንተ ወደ እኔ ትመጣለህን? ባሪያ ወደ ጌታው ይሔዳል እንጂ እንዴት ጌታ ወደ ባሪያው ይመጣል?” የቤተ ክርስቲያናችን አባቶች የጌታችን ወደ ዮሐንስ መሔድ እረኛ ለበጎቹ ክብር እንደመስጠት ነው ይላሉ፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ የተባለው ቅዱስ አባትም ጌታችን አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከራሷ ከጥምቀት ይልቅ እንኳ ንጹህ ነውና ሊጠመቅ ወደ ዮሐንስ መሔዱ፣ ወደ ዮርዳኖስ መውረዱ የሚደንቅ ትህትና ነው ይላል፡፡ ለስም አጠራሩ ክብር ይግባውና ኢየሱስም በዮርዳኖስ ወንዝ በዮሐንስ ሲጠመቅ ሰማያት ተከፈቱ፣ አብ በደመና መሰከረ፣ ምንፈስ ቅዱስም በርግብ አምሳል ወረደ፡፡
የመጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ክብሩ እጅግ ከፍ ያለ እንደሆነ ጌታችን ከሴቶች ከተወለዱት መካከል ከመጥምቁ ዮሐንስ የሚበልጥ አልተነሣም፤ ሲል በቅዱስ ማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ 11÷9-11 መስክሮለታል፡፡ ራሱን ከዓለም የለየው ፍጹም ባሕታዊ፣ የመናንያን፣ ፈቃደ ስጋን የተዉ ሁሉ ድንቅ ምሣሌ ነው፡፡ በረከቱ ትደርብንና መናንያንን፣ ገዳማውያንንና ገዳማቸውን ማሰብ በረከታቸው እድናገኝ ያደርገናል፡፡ ገዳማትን እናግዝ፣ ዓአታቸውን እናጽና፡፡
ድጋፍ ለማድረግ:- ሙትአንሳ ማር ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት ገዳም
ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391
ወይም
አቢሲኒያ ባንክ
141029444
የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444