ወደ ማረሚያ ቤት እንዳይገቡ የተከለከሉ ነገሮች እና መዘዛቸው
1. በማረሚያ ፖሊስ አባላት ዘንድ፣
በፌዴራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን የፖሊስ አባላት የዲስፕሊን አፈፃፀም መመሪያ ቁጥር 3/2003 አንቀጽ 31 ቁጥር 24 በሕገ ወጥ መንገድ አባልና ሰራተኛ ከታራሚ ጋር ወይም አባል እርስ በርስ በመመሳጠር ወደ ማረሚያ ቤት እንዳይገቡ የተከለከሉ ነገሮችን ማስገባት፤ ለሌሎች መተባባር፣ ድርጊቱ ሲፈፀም እያዩ ለአስተዳደር አለማሳወቅ፣ ከፍተኛ ጥፋት መሆኑ በግልጽ ተመላክቷል፡፡
ወደ ማረሚያ ቤት እንዳይገቡ የተከለከሉ ነገሮች
ሀሽሽ፣
የሞባይል ቀፎ፣
ሲም ካርድ፣
ሲጋራ፣
አልኮል መጠጥ፣
ፈንጅ ፣
የጦር መሳርያ፣
ተቀጣጣይ ነገሮች፣
ስለታም ነገሮች …ወዘተ ማስገባት ወይም አስገብቶ መገኜት ሲሆን፣ ይህ ጥፋት በፈፀመ የማረሚያ ፖሊስ አባል ላይ የሚወሰድ እርምጃ፡- በፌዴራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን በከፍተኛ ዲስፕሊን የሚያስጠይቅ፣ጥፋት ነው፤ ጥፋቱም ከስራ ማሰናበት እስከ ፍርድ ቤት ድረስ የሚሄድ ጥፋት ይሆናል፡፡
2. በሕግ ታራሚዎችና በቀጠሮ እስረኞች ዘንድ፣
በፌዴራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን የሕግ ታራሚዎችና የቀጠሮ እስረኞች የተሻሻለ የሥነ ስርዓት ጥፋት ቅጣት አፈፃፀም መመሪያ ቁጥር 5/2009 በክፍል 02 አንቀጽ 11 ቁጥር 35 የተከለከሉ ነገሮችን (ጫት፣ ተቀጣይ ነገር፣ ስልክ፣ ሲም ካርድ ፣ሲጋራ፣ ጋንጃ፣ ቡሪ፣ አንጋዳ፣ አልኮል መጠጥና …ወዘተ) ወደ ማረሚያ ቤትና ማረፊያ ማዕከል ለማስገባት መሞከር ወይም የገባውን መጠቀም የሚያስከትለው የቅጣት አይነት
ለ4 ወር እንዳይጎበኝ መከልከል ወይም
ለ3 ወር ለብቻ ለይቶ ማሰር ወይም
ከ5 ወር ከ1 ቀን አስከ 6 ወር ለሚደርስ ጊዜ ከሚያገኘው ገቢ 1/3ኛውን በመቀነስ ሥራ ማሰራት ወይም ማግኘት ከሚገባው የአመክሮ እስራት 3/4ኛውን መከልከል፡፡
ቁጥር 36 የተከለከሉ ነገሮች (አደንዛዥ እጽ፣ ጦር መሳሪያ እና ተቀጣጣይ ነገሮች ወደ ማረሚያ ቤት እና ማረፊያ ማዕከል ለማስገባት መሞከር ወይም አስገብቶ መገኘት ወይም ሌሎች እንዲያስገቡ መተባበር፣ ጉዳት ማድረስ (በወንጀል ያለው ተጠያቂነት እንደተጠበቀ ሆኖ የሚያስከትለው የቅጣት አይነት
ለ4 ወር እንዳይጎበኝ መከልከል ወይም
ለ3 ወር ለብቻ ለይቶ ማሰር ወይም
ከ5 ወር ከ1 ቀን እስከ 6 ወር ለሚደርስ ጊዜ ከሚያገኘው ገቢ 1/3ኛውን በመቀነስ ሥራ ማሰራት ወይም ማግኘት ከሚገባው የአመክሮ እስራት 3/4ኛውን መከልከል፡፡
ቁጥር 37 የተከለከሉ ነገሮች (ሀሺሽ፣ ፈንጂ፣ እና ተቀጣጣይ ነገሮች…ወዘተ) ወደ ማረሚያ ቤት እና ማረፊያ ማዕከል ለማስገባት መሞከር ወይም ማስገባት ወይም የገባውን መጠቀም የወንጀል ተጠያቂነት እንደተጠበቀ ሆኖ የሚያስከትለው የቅጣት አይነት
ለ4 ወር እንዳይጎበኝ መከልከል ወይም
ለ3 ወር ለብቻ ለይቶ ማሰር ወይም
ከ5 ወር ከ1 ቀን እስከ 6 ወር ለሚደርስ ጊዜ ከሚያገኘው ገቢ
1/3ኛውን በመቀነስ ሥራ ማሰራት ወይም ማግኘት ከሚገባው የአመክሮ እስራት 3/4ኛውን መከልከል፡፡ የሚሉት ይገኙበታል፡፡
በመሆኑም አባላት እና ሰራተኞችም ሆኑ የህግ ታራሚዎች፣የቀጠሮ እስረኞች፣ ጠያቂ ቤተሰቦች ወይም ማናቸውም በዚህ ጸያፍ ስራ ላይ የሚሰማራ ሁሉ አባላትና ሰራተኞችን ከስራ ከማፈናቀል ጀምሮ እስከ ማሰሳር ሊያደርስ የሚችል ጥፋት ሲሆን ለታራሚዎች እና ለቀጠሮ እስረኞች ደግሞ በፍርድ ቤት ከተወሰነባቸው ውሳኔ ወይም ከተጠረጠሩበት ወንጀል ተጨማሪ ጥፋት የሚሆን በመሆኑ ለተጨማሪ ቅጣት እንዲዳርጉ የሚያድርግ ስህተት መሆኑ ታውቆ አስፈጊላው ሁሉ ጥንቃቄ ሊደረግ ይገባል፡፡
የፌዴራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን
ጥር 27/2017 ዓ.ም