# በ4ኛው መቶ ክ/ዘመን...
በ4ኛው መቶ ክ/ዘመን የነበሩት ጻድቃን እንድራኒቆስና ሚስቱ አትናስያ በዘመናቸው ከልጅነት ጀምረው ቃለ እግዚአብሔርን የሚሰሙ ለወላጆቻቸው የሚታዘዙ ነበሩ፡፡
ዘመኑ ደርሶ በሚገባው የተክሊል ሥርዓት ጋብቻቸውን ፈጽመው 40 ቀን ከተጠናቀቀ በኋላ ከምንም ነገር በፊት 2ቱ ቁጭ ብለው ተወያዩ፡፡ የውይይታቸው ርዕስ ደግሞ "ፈጣሪያችን በምን እናስደስተው" የሚል ነበር፡፡ በመጨረሻም ሁልጊዜም እንግዳ በመቀበል፣ ነዳያን በቤታቸው በማስተናገድ፣ ጸሎት፣ ጾምና ስግደት ሳያቋርጡና ለሩካቤ ስጋ ሳይቻኮሉ ለመኖር ተስማሙ፡፡ መልካም ነገር አስበዋልና አምላክ የሰጣቸውን ሃብት ሲመጸውቱ ኖሩ፡፡ ከዘመናት የቅድስና ጉዞ በሁዋላ በፈቃደ እግዚአብሔር 2 ልጆች አከታትለው ወለዱ፡፡ ወንዱን ዮሐንስ ሴቷን ደግሞ ማርያም አሏቸው::
ልጆች ከወለዱ በኋላ ይህንን ላደረገላቸው ጌታ ክብር አልጋ ለመለየት ሌላ ወስነው ለ12 ዓመታት በጾምና በጸሎት ኖሩ፡፡ ልጆቻቸው ዮሐንስና ማርያም በቅንነት አድገው እድሜአቸው 12 ሲሆን 2ቱም በአንድ ቀን ታመው ሞቱ፡፡ እንድራኒቆስና ሚስቱ አትናስያ ታቅፈው ወስደው ቀበሯቸው:: ይህ እጅግ አሰቃቂ ፈተና እንድራኒቆስ ከቀብር በሁዋላ ወደ ቤተ ክርስቲያን ገብቶ ምርር ብሎ እንዲያለቅስ ቢያደርገውም “አምላከ ኢዮብ! አንተ ሰጠኸኝ፣ አንተም ነሳኸኝ፤ ስምህ ለዘለዓለም ይባረክ" ብሎ ሔደ፡፡ አትናስያ ግን ከሐዘኗ ብዛት የልጆቿ መቃብር ላይ ተደፍታ ስታለቅስ ቅዱስ መልአክ ልቡናዋን ወደ ሰማይ አሳረገው፡፡ ልጆቿ ዮሐንስና ማርያም በገነት ውስጥ ከቅዱሳን ጋር ሐሴትን ሲያደርጉም ተመለከተች፡፡ ወዲያው ወደ ቤቷ ተመልሳ ለባሏ እንድራኒቆስ ያየችውን ነገረችውና ተደሰቱ፡፡
ለዚህ የእግዚአብሔር ውለታም በምናኔ ሊኖሩ ተስማሙ፡፡ እጅግ ሃብታሞች ነበሩና ያላቸውን ሁሉ ለነዳያን አካፍለው ወደ ገዳመ አስቄጥስ ሔደው እርሷ ከሴቶች፣ እርሱ ደግሞ ከወንዶቹ ገዳም ገቡ፡፡ ለ12 ዓመታት በፍጹም ተጋድሎ ለፈጣሪያቸው ተገዙ፡፡ በእነዚህ ዘመናት አንዳቸው ስለ ሌላው ሰምተው ባያውቁም በጸሎት ግን ያለማቁዋረጥ ይተሣሠቡ ነበር፡፡ ከ12 ዓመታት በሁዋላ የፍቅር አምላክ በልቡና ተመሳሳይ ሐሳብን አመጣ፡፡ እርሱ ከአበ ምኔቱ ታላቁ_አባ_ዳንኤል እርሷም ከእመ ምኔቷ አስፈቅደው ከኢየሩሳሌም ከቅዱሳት መካናት ለመባረክ ጉዞ ጀመሩ፡፡ በጉዞ ላይ ሲተያዩ እርሷ ለየችው፡፡ እርሱ ግን በጥበበ እግዚአብሔር አካሏ በገድል ከመለወጡ ባሻገር የለበሰችው እንደ ወንድ መነኮሳት ለብሳ ነበርና ሊለያት አልቻለም፡፡
2ቱም እየተጫወቱ፣ እየጸለዩ በሰላም ተባርከው ወደ ግብጽ እስኪመለሱ ቅድስት አትናስያን የለያት አልነበረም፡፡ ወደ ገዳመ አስቄጥስ ሲደርሱ ግን አባ ዳንኤል በጸጋ እግዚአብሔር ባልና ሚስት መሆናቸውን አውቆ “ለምን አብራችሁ አትኖሩም?” አላቸው፡፡ በደስታ ተቀብለውት እርሷ እያወቀችው እርሱ ሳያውቃት ለ12 ዓመታት አብረው በቅድስና ኖሩ፡፡ ከእነዚህ ዘመናት በሁዋላ ግን ሐምሌ 28 ቀን ቅድስት አትናስያ ታመመችና አባ ዳንኤል ሥጋውን ደሙን አቀብሏት ዐረፈች፡፡ ሊገንዟት ሲቀርቡ ቅዱስ እንድራኒቆስ ሚስቱን አወቃት፡፡ በአንድ ጊዜ ሚስቱንና የሚወደውን ባልንጀራ በማጣቱ አለቀሰ፡፡ ከቀብር መልስ "ጌታ ሆይ! ውሰደኝ?" ብሎ ጸልዮ እርሱም ተከትሏት ዐረፈ:: አባ ዳንኤል እርሱንም ቀብሮ ዜና ቅድስናቸውን ጻፈ፡፡
የቅዱሳን በረከት እንዲያድርብን ገዳማትን እንርዳ፡፡
ገዳማዊያን በዓለም ላለነው ለኛና ለቅድስት ቤተክርስቲያን ለሀገራችንም ይጸልያሉ፡፡ ገዳማቸውን በመርዳት፣ በዓታቸውን በማጽናት ከበረከታቸው እንሳተፍ፡፡
ድጋፍ ለማድረግ:- ሙትአንሳ ማር ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት ገዳም
ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391
ወይም
አቢሲኒያ ባንክ
141029444
የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444