#ምኩራብ፣ የቤትህ ቅናት በላኝ
በቅድስት ቤተክርስቲያናችን የዐቢይ ጾም ሶስተኛ ሣምንት ምኩራብ ተብሎ ይጠራል፡፡ ጌታችን አምላካችን መድኅኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ምኩራብ የገባበትና ያስተማረበት ነው፡፡ ምኩራብ ማለትም ቀጥተኛ ፍቺው ኮረብታ፣ ተራራ የሚያህል ታላቅ ሕንጻ ማለት ነው። የዮሐንስ ወንጌል 2÷12-ፍጻሜው ይነበባል፡፡ “የአይሁድም የፋሲካቸው በዓል ቀርቦ ነበር፤ ጌታችን ኢየሱስም ወደ ኢየሩሳሌም ወጣ፡፡ በቤተ መቅደስም በሬዎችንና በጎችን÷ ርግቦችንም የሚሸጡትን፣ ገንዘብ ለዋጮችንም ተቀምጠው አገኘ፡፡ የገመድም ጅራፍ አበጀ፤ በጎችንና በሬዎችን፣ ሁሉንም ከቤተ መቅደስ አስወጣ፤ የለዋጮችንም ገንዘብ በተነ፤ ገበታዎቻቸውንም ገለበጠ፡፡ ርግብ ሻጮችንም÷ “ይህን ከዚህ አውጡ፤ የአባቴን ቤት የንግድ ቤት አታድርጉ” አላቸው፡፡ ደቀ መዛሙርቱም÷ “የቤትህ ቅናት በላኝ” የሚል ቃል በመዝ. 68÷9 ተጽፎ እንዳለ ዐሰቡ፡፡”
ጌታችን ከጥምቀቱ በፊት ወደ ቤተመቅደስ የመጣባቸው በርካታ አጋጣሚዎች ቢኖሩም ሁለቱ ግን ተለይተው ይታወቃሉ፡፡ የመጀመሪያው ሉቃስ 2÷22-40 በሥርዓተ ኦሪት መሰረት በተወለደ በአርባኛው ቀን ወደ ቤተመቅደስ መምጣቱ፣ ሁለተኛ በሉቃ 2÷41-47 እንደምናገኘው ዐሥራ ሁለት ዓመት ሲሆነው ከዮሴፍና ከእመቤታችን ጋር ለበዓል ወደ ኢየሩሳሌም በሄዱ ጊዜ ከእነርሱ ተለይቶ በቤተመቅደስ በመቅረት የኦሪት ሊቃውንትን ሲጠይቃቸውና ሲሰማቸው የነበረበት አጋጣሚ ናቸው፡፡ በእነዚህ ጊዜያት ወደ ቤተ መቅደስ ሲመጣ አገልጋዮቹ በሥጋዊ ፍላጎታቸው ምክንያት በቤተመቅደሱ የማይገባ ሥራ እየሰሩ ቢያይም አምላክነቱን ገልጦ የሚያስተምርበት፣ የሚገስጽበት ጊዜ አልደረሰምና በዝምታ አልፏቸው ነበር፡፡
ከጥምቀቱ በኋላ ግን በሁለት አጋጣሚዎች ቤተ መቅደሱን አጽድቷል፡፡ ቀዳሚው በመጀመሪያው ፋሲካ አገልግሎቱን ሲጀምር ያደረገውና ከላይ በዮሐንስ ወንጌል የገለጽነው በምኩራብ ሣምንት የሚነበበው፣ የሚተረጎመው ነው፡፡ ጌታችን ለሁለተኛ ጊዜ ቤተመቅደሱን ሊያነፃ የሄደው ለመከራና ለሞት ተላልፎ ከመሰጠቱ አስቀድሞ በዕለተ ሆሳዕና፣ በማቴ 21÷12-17 የሚገኘው ነው፡፡ በዚህም ወቅት በተመሳሳይ ገዥዎችንና ለዋጮችን፣ እንዲሁም የቤተመቅደስ አለቆችን “ቤቴ የጸሎት ቤት ይባላል፣ እናንተ ግን የሌቦችና የወንበዴዎች፣ ቀማኞች ዋሻ አደረጋችኋት” በማለት የገሰጸበት ነው፡፡ ስለሆነም ትንቢተ ነቢያትን የፈጸመ ጌታ በአገልግሎቱ መጀመሪያና ፍፃሜ ላይ ወደ ቤተመቅደስ የመጣው ቤተመቅደሱን ለማንፃት ነበር፡፡
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ቤተመቅደስ ሲመጣ በቤተመቅደሱ እንስሳት የሚሸጡ የሚለውጡ ሰዎች እንደ ብሉይ ኪዳን ሥርዓት ለኃጢአት ማስተስረያ መስዋእትነት የሚቀርቡ ነበሩ፡፡ የካህናት አለቆችና ግብር አበሮቻቸውም በቤተመቅደሱ የሚሸጡትን እንስሳት ለመስዋእት ብቁ መሆናቸውን የሚያሳይ ማስረጃ በመስጠት በምትኩ ገንዘብ እየተቀበሉ አገልግሎቱ መልኩን ቀይሮ ንግድ ሆኖ ነበር፡፡ እንስሳቱን የሚሸጡት ሰዎችም ስለሚያገኙት ትርፍ እንጂ ስለ መስዋእቱ ንጽህና አይጠነቀቁም ነበር፤ ከጌታ የሚገኝ ሰማያዊ ጸጋን በመሸጥና በመለወጥ በሚያገኙት ትርፍ የቀየሩ ነበሩ፡፡
ታዲያ ወደ ቤተመቅደስ የመጣው ለፍርድ ሳይሆን ለማንፃት ነበርና ሻጮችና ለዋጮችን ሰዎች ሳይሆን የሚሸጡትንና የሚለወጡትን ርግቦችን፣ በጎችን፣ በሬዎችን፣ የሰዎቹን የሚለወጥ ገንዘብ ከቤተ መቅደስ አስወጣ፡፡ የቤተ መቅደሱ ባለቤት ዳግም ይመጣል፡፡ የሚመጣው ግን እንደቀደመው ለማንፃት ሳይሆን ለፍርድ ነውና በምግባር በሃይማኖት ጸንተን፣ በጸሎትና በምጽዋት ተግተን እንጠብቀው፡፡
ገዳማዊያን በዓለም ላለነው ለኛና ለቅድስት ቤተክርስቲያን ለሀገራችንም ይጸልያሉ፡፡ ገዳማቸውን በመርዳት፣ በዓታቸውን በማጽናት ከበረከታቸው እንሳተፍ፡፡
ድጋፍ ለማድረግ:- ሙትአንሳ ማር ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት ገዳም
ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391
ወይም
አቢሲኒያ ባንክ
141029444
የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444