Fetan Sport - ፈጣን ስፖርት


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic
Category: Education


ፈጣን ስፖርት የአውሮፓን ከፍተኛ የእግር ኳስ ሊጎች የሚሸፍን የኢትዮጵያ የዜና ቻናል ነው። ይዘቱም የቡድን ዜናዎችን፣ የጨዋታ ውጤቶችን፣ የተጫዋቾች ዝውውሮችን እና ሌሎች ብዙ ነገሮችን ያካትታል።

Related channels  |  Similar channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Category
Education
Statistics
Posts filter


🔵🔴 ሜሲ በባርሴሎና ዝግጅት ላይ ሊገኝ ነው!

የካታላኑ ክለብ ባርሴሎና ከሳምንት በኋላ 125ኛ አመት ክብረ በዓሉን ሊያከብር ነው። በታዋቂው ባርሴሎና ሊሴው ኦፔራ አዳራሽ በሚካሄደው ዝግጅት ላይ የክለቡ ታሪክ አይሽሬ ተጨዋች ሊዮኔል ሜሲ ይገኛል ተብሎ ይጠበቃል።

የክለቡ ልሳን የሆኑ መገናኛ ብዙሃን እንዳስነበቡት፣ አርጀንቲናዊው ኮከብ በዝግጅቱ ላይ ትልቁ እንግዳ ሆኖ ሊቀርብ ነው። 🐐🎭


⚽️ "ሜሲ የምንጊዜም ምርጡ ተጨዋች ነው" - ሮድሪ

ስፔናዊው የማንችስተር ሲቲ ተጨዋች ሮድሪ፣ ሊዮኔል ሜሲን "የምንጊዜም ምርጡ ተጨዃች" ሲል ገልጿል።

"ጥርጥር የለውም፣ አለማችን በእሱ ደረጃ ያለ ተጨዋች ተመልክታ አታውቅም። ከእሱ እግሮች ኳስን መንጠቅ እጅግ ከባድ ነው" ያለው ሮድሪ፣ በሁለቱ ታላላቅ ተጨዋቾች ያለውን ልዩነት እንዲህ ገልጿል:

"ከሮናልዶ ጋር ስትጫወት ሳጥን ውስጥ ኳሶችን እንዳያገኝ ትጥራለህ። ከሜሲ ጋር ግን የትም ቢሆን ኳሱ በጭራሽ እሱ እግር ላይ እንዳይደርስ ትሞክራለህ።" 🐐👑


🔵 ሲቲ ወሳኝ ተጨዋቾቹ ልምምድ ሰርተዋል!

እንግሊዛዊው የማንችስተር ሲቲ የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች ጆን ስቶንስ ከጉዳቱ በማገገም ወደ ልምምድ ተመልሷል።

ከሀገራት ጨዋታ በኋላ ወደ ሜዳ እንደሚመለስ የሚጠበቀው ኬቨን ዴብሮይን፣ እንዲሁም ጃክ ግሪሊሽ እና ማኑኤል አካንጂ የቡድን ልምምዳቸውን መስራት ችለዋል።

ሲቲ የፊታችን ቅዳሜ ምሽት 2:30 ከቶተንሀም ጋር ይጫወታል። 💪⚽️


🔵🔴 ላሚን ያማል በአምባሳደርነት ተሾሟል!

ስፔናዊው የባርሴሎና የፊት መስመር ተጨዋች ላሚን ያማል የዩኒሴፍ አምባሳደር በመሆን ተሾሟል።

"አሁን ዩኒሴፍን ተቀላቅያለሁ፣ በቀጣይ የህፃናትን መብት ለመጠበቅ አብረን የምንሰራ ይሆናል" ሲል በማህበራዊ ትስስር ገፁ አስታውቋል።

አለም አቀፍ የህፃናት ቀን በዛሬው እለት በመላው አለም እየተከበረ ይገኛል። 👶❤️


🔵 "ዋንጫ የማላሸንፍበት ክለብ መሄድ አልፈልግም" - ሌሮይ ሳኔ

ጀርመናዊው የፊት መስመር ተጨዋች ሌሮይ ሳኔ ውሉን ለማራዘም ከባየር ሙኒክ ጋር በጥሩ ድርድር ላይ መሆኑን ገልጿል።

"በባየር ሙኒክ ደስተኛ ነኝ፣ ምቾት ይሰማኛል" ያለው ሳኔ፣ ከአርሰናል እና ዩናይትድ ጋር ስሙ ስለመያያዙ ሲጠየቅ "እኔ መጫወት የምፈልገው የምሻሻልበት እና ዋንጫ ማሸነፍ የምችልበት ክለብ ውስጥ ነው" ሲል መልሷል።

ባየር ሙኒክ የሚፈልገው አይነት ክለብ መሆኑን ያረጋገጠው ተጨዋቹ ውሉን ማራዘም እንደሚፈልግ አክሏል። 🏆🇩🇪


⚪️🔴 አርሰናል አርዳ ጉለርን ሊያስፈርም ይችላል!

የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል በሚቀጥለው ጥር የተጨዋቾች የዝውውር መስኮት አርዳ ጉለርን ማስፈረም ስለሚችሉባቸው ሁኔታዎች እያጣሩ ነው።

በሪያል ማድሪድ ቤት ብዙም የመሰለፍ እድል ያላገኘው ቱርካዊው አማካይ የአርሰናል የመጀመሪያ ኢላማ ሊሆን እንደሚችል የስፔን ሚዲያዎች ዘግበዋል።

የክለቡ ሀላፊዎች በኦዴጋርድ ያደረጉትን ስኬታማ ዝውውር በጉለር ደግመው ማየት ይፈልጋሉ። 🇹🇷⚽️


🔴 ዩናይትድ በጥር ተጨዋች ያስፈርማል?

ማንችስተር ዩናይትድ በጥር የተጨዋቾች የዝውውር መስኮት አነስተኛ በጀት እንደሚኖራት ተገልጿል።

ቀያዮቹ ሴጣኖች የፋይናንሻል ፌር ፕሌይ ህግ ላለመጣስ መጠንቀቅ እንዳለባቸው እና ብዙ ገንዘብ ማውጣት እንደማይችሉ ተነግሯል። ተጨዋቾችን ሲሸጡ ብቻ አዳዲስ ዝውውሮችን ልናይ እንደምንችል ተጠቁሟል።

በአሞሪም የሚመራው ዩናይትድ በዝውውር ገበያው ትልቅ ተሳትፎ እንደማያደርግ ዘ አትሌቲክ ዘግቧል። 💰⚽️


🔵 ፔፕ ጋርዲዮላ ውሉን ለማራዘም ተስማማ!

ስፔናዊው አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ በማንችስተር ሲቲ ቤት ውሉን ለተጨማሪ አመት ለማራዘም ከስምምነት መድረሳቸውን ዘ አትሌቲክ ዘግቧል።

ለአንድ ተጨማሪ የውድድር አመት የመቆየት አማራጭ ያካተተ የአንድ አመት ውል ለመፈረም የተስማሙት አሰልጣኙ፣ በዚህም ሲቲን ከአስር አመታት በላይ የሚመሩ ይሆናል።

ክለቡ የውል ማራዘሚያውን በቅርቡ በይፋ ያስታውቃል። 👨‍💼🏆


⚪️🔴 "አርቴታ የጭንቅላት ጨዋታ ይወዳል" - ዚንቼንኮ

የአርሰናል የመስመር ተጨዋች አሌክሳንደር ዚንቼንኮ አሰልጣኝ አርቴታ ከተጋጣሚ ቡድን ጋር የጭንቅላት ጨዋታ እንደሚወዱ ገልጿል።

"አርቴታ ጉዳት ያጋጠማቸው ተጨዋቾች ቦርሳቸውን ይዘው ከቡድኑ ጋር እንዲጓዙ ሲነግራቸው ሰምቻለሁ" ያለው ዚንቼንኮ፣ የተጎዱ ተጨዋቾች ከሁሉም ጋር በመልበሻ ቤት እንዲቆዩ የሚያደርጉት የተጋጣሚ አሰልጣኝ ላይ ጫና ለማድረግ እንደሆነ አስረድቷል።

አርቴታ በዘንድሮው ዓመት ወሳኝ ተጨዋቾቻቸውን በጉዳት ማጣታቸው ይታወሳል። 🧠⚽️


⚪️ ኤደር ሚሊታኦ የቀዶ ጥገና ህክምና አደረገ!

ብራዚላዊው የሪያል ማድሪድ የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች ኤደር ሚሊታኦ ያጋጠመውን የ"ACL" ጉዳት ተከትሎ ስኬታማ የቀዶ ጥገና ህክምና አድርጓል።

ሪያል ማድሪድ በይፋዊ መግለጫው እንዳስታወቀው፣ ተጨዋቹ በሚቀጥሉት ቀናት የማገገሚያ ጊዜውን ይጀምራል።

ሚሊታኦ በዚህ ጉዳት ምክንያት ቢያንስ ለ9 ወራት ከሜዳ ይርቃል። 🏥🇧🇷


🔵 ስኮት ማክቶሚናይ ጉዳት አጋጥሞታል!

ስኮትላንዳዊው የናፖሊ የመሐል ሜዳ ተጨዋች ስኮት ማክቶሚናይ ትናንት ምሽት ሀገሩ ከፖላንድ ጋር ባደረገችው የኔሽንስ ሊግ ጨዋታ ጉዳት አስተናግዶ ከሜዳ ተቀይሮ ወጥቷል።

ተጨዋቹ በቀጣይ ስላጋጠመው የጉዳት መጠን ለማወቅ ወደ ክለቡ በመመለስ ተጨማሪ ምርመራዎች ይደረጉለታል።

በምሽቱ ጨዋታ ስኮትላንድ የፖላንድን ቡድን በማክጊን እና ሮበርትሰን ግቦች 2-1 አሸንፋለች። 🏴󠁧󠁢󠁳󠁣󠁴󠁿🤕


🔴 የአንቶኒ የማንችስተር ዩናይትድ ቆይታ?

ብራዚላዊው የማንችስተር ዩናይትድ የፊት መስመር ተጨዋች አንቶኒ የወደፊት ቆይታው ጥያቄ ውስጥ መግባቱን የእንግሊዝ ጋዜጦች ዘግበዋል።

ዴይሊ ስታር እንደዘገበው ዩናይትድ በጥር የዝውውር መስኮት አንቶኒን ሊሸጠው ይችላል። አሰልጣኝ አሞሪም በቦታው ላይ የ17 አመቱን ፖርቹጋላዊ የስፖርቲንግ ሊስበን ተጨዋች ጂኦቫኒ ኩዌንዳን በአማራጭነት እየተመለከቱ ነው።

ዩናይትድ አንቶኒን ከሁለት አመት በፊት ከአያክስ በ95 ሚሊዮን ዩሮ አስፈርሞ ነበር። 💰🇧🇷


⚽️ ኢንዞ ፈርናንዴዝ ለምን ቅጣት አልተጣለበትም?

የእንግሊዝ ኤፍኤ ቶተንሀሙን ሮድሪጎ ቤንታኩር በሰጠው ያልተገባ አስተያየት የ7 ጨዋታ እገዳ ቅጣት ሲጥልበት፣ በቅርቡ ክስ የቀረበበት ኢንዞ ፈርናንዴዝ ላይ ግን ቅጣት አልጣለም።

ኢንዞ ፈርናንዴዝ ድርጊቱን የፈጸመው በብሔራዊ ቡድን ግዴታ ላይ በመሆኑ ጉዳዩ የሚመለከተው ፊፋን ነው። ቤንታኩር ግን አስተያየቱን የሰጠው በትርፍ ጊዜው በመሆኑ ኤፍኤ ቅጣት መጣል ችሏል። ⚖️🏴󠁧󠁢󠁥󠁮󠁧󠁿


🇸🇩 ሱዳን ለአፍሪካ ዋንጫ አለፈች!

የሱዳን ብሔራዊ ቡድን ከአንጎላ ጋር ያደረገውን የማጣሪያ ጨዋታ በአቻ ውጤት በማጠናቀቅ ለአፍሪካ ዋንጫው ማለፉን አረጋግጧል።

በተመሳሳይ ምድብ ጋና ዛሬ ከኒጀር ጋር ባደረገችው ጨዋታ 2-1 ተሸንፋለች። በ6 ጨዋታዎች 3 ሽንፈት እና 3 አቻ በማስመዝገብ የምድቡን የመጨረሻ ደረጃ ይዛለች።

ናይጄሪያም ከሩዋንዳ ጋር ባደረገችው ጨዋታ 2-1 ተሸንፋለች። ከምድቡ ናይጄሪያን በመከተል ቤኒን ለአፍሪካ ዋንጫው አልፋለች። ⚽️🏆


⚡️ ሀላንድ የሊጉ ከፍተኛ ተከፋይ ሊሆን ይችላል!

ኖርዊያዊው ተጨዋች ኤርሊንግ ሀላንድ በማንችስተር ሲቲ ቤት ውሉን ለማራዘም ንግግር ማድረጉን ሚረር ፉትቦል ዘግቧል።

ከተጨዋቹ ወኪሎች እና ቤተሰቦች ጋር የተደረገው የመጀመሪያ ንግግር በጥሩ ሁኔታ ተጠናቋል። ውሉ እስከ 2029 ሲራዘም፣ ሳምንታዊ ክፍያውም ከ450,000 ወደ 600,000 ፓውንድ ከፍ እንደሚደረግ ተገልጿል።

በዚህም ከዴብሮይን በመብለጥ የፕሪምየር ሊጉ ከፍተኛ ተከፋይ ሲሆን፣ የውል ማፍረሻው ከ150 ሚሊዮን ወደ 200 ሚሊዮን ፓውንድ ይጨምራል። 💰👊


⚽️ "ሮናልዶ ዛሬ ባለመጫወቱ አዝኛለሁ" - ሞድሪች

ክሮሽያዊው የመሐል ሜዳ ተጨዋች ሉካ ሞድሪች፣ ሀገሩ ከፖርቹጋል ጋር በምታደርገው ጨዋታ ክርስቲያኖ ሮናልዶ የማይሳተፍ በመሆኑ ማዘኑን ገልጿል።

"ሁልጊዜም ከሮናልዶ ጋር መጫወት ያስደስታል። እሱ በዛሬው ጨዋታ ባለመሳተፉ አዝኛለሁ" ያለው ሞድሪች፣ "በቅርቡ እንደምገናኘው ተስፋ አደርጋለሁ። ከእሱ ጋር በምትገናኝበት ጊዜ ሁሉ አዲስ ነገር ትማራለህ" ብሏል።

ክሮሽያ ዛሬ ምሽት 4:45 በኔሽንስ ሊግ ከፖርቹጋል ጋር ትጫወታለች። 🇭🇷🇵🇹


⚽️ "ሳላህ በትልቅ ደረጃ የሚነሳ ተጨዋች አይደለም" - ትሮይ ዲኒ

የቀድሞው እንግሊዛዊ ተጨዋች ትሮይ ዲኒ መሐመድ ሳላህ በትልቅ ደረጃ የሚነሳ ተጨዋች አለመሆኑን ገልጿል።

"መሐመድ ሳላህ ምርጥ ተጨዋች ነው፣ ነገርግን በትልቅ ደረጃ የሚነሳ ተጨዋች ነው ብዬ አላስብም። ልጆቼ የአጥቂ ስፍራ ተጨዋች መሆን ከፈለጉ፣ ከሳላህ ይልቅ ቪኒሰስ ጂኒየር የሚያደርጋቸውን ነገሮች እንዲመለከቱ እመክራለሁ" ብሏል። 👀💭


🇫🇷 "ያለ ምባፔ ማሸነፍ እንችላለን" - ኮናቴ

ፈረንሳዊው የተከላካይ ስፍራ ተጨዋች ኢብራሂም ኮናቴ ብሔራዊ ቡድናቸው በኪልያን ምባፔ ላይ የተመሰረተ አለመሆኑን ገልጿል።

"ምባፔ አስደናቂ ተጨዋች ነው። ሁላችንም እንወደዋለን፣ እሱ ከዚህ ቀደም ለቡድኑ ያደረጋቸውን ነገሮች አንረሳም" ያለው ኮናቴ፣ "ሌሎች ጥሩ ተጨዋቾች አሉን፣ ያለ ምባፔም ጨዋታዎችን ማሸነፍ የሚችል ቡድን አለን" ብሏል።

ምባፔ ለተከታታይ ሁለተኛ ጊዜ ከብሔራዊ ቡድኑ ስብስብ ውጪ ሆኗል። ⚽️👊


🇪🇹 የ2017 የሶፊ ማልት ታላቁ ሩጫ ተካሂዷል!

የወንዶች 10 ኪሎ ሜትር ውድድሩን ቢኒያም መሀሪ 28:25.661 በሆነ ሰዓት በመግባት ለተከታታይ ሁለተኛ ጊዜ ዋንጫውን ይዟል።

የሴቶቹን ውድድር አትሌት አሳየች አይቸው 32:13.418 በሆነ ሰዓት በአንደኝነት አጠናቃለች።

የገንዘብ ሽልማቶች:
🥇 250,000 ብር
🥈 150,000 ብር
🥉 100,000 ብር 🏃‍♂️🏃‍♀️


🇪🇹 ዋልያዎቹ ለአፍሪካ ዋንጫው ሳያልፉ ቀርተዋል!

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ የምድብ አምስተኛ ጨዋታውን ከታንዛኒያ ጋር አድርጎ 2-0 ተሸንፏል። ምሱቫ እና ሳሉም የታንዛኒያን የማሸነፊያ ግቦች አስቆጥረዋል።

የመጀመርያ ጨዋታቸውን ያደረጉት አሰልጣኝ መሳይ ተፈሪ ሽንፈት ሲያስተናግዱ፣ ዋልያዎቹ በ2025 በሞሮኮ ከሚካሄደው የአፍሪካ ዋንጫ ውጪ መሆናቸውን አረጋግጠዋል።

የምድብ ደረጃ:
2⃣ ታንዛኒያ - 7 ነጥብ
4⃣ ኢትዮጵያ - 1 ነጥብ

የመጨረሻ ጨዋታ (ማክሰኞ):
- ዲሞክራቲክ ኮንጎ vs ኢትዮጵያ
- ታንዛኒያ vs ጊኒ 🦁💔

20 last posts shown.