Forward from: MARANATA✔
እስማኤል እንዳይወለድ
ከእግዚአብሔር የተወለድን ነገሮችን በራሳችን መንገድ ብቻ ማስተናገድ አንችልም!! ለእግዚአብሔር መተዉ ያለብን ነገር አለ!! በውስጣችን ባለው በመንፈሱ ሕይወታችን ወደሚመራበት ደረጃ #ማደግ አለብን!?
❝በእግዚአብሔር መንፈስ የሚመሩ ሁሉ እነዚህ የእግዚአብሔር ልጆች ናቸውና።❞ —ሮሜ 8፥14።
በመንፈሱ ያልተመራ፤ በጸጋው ያልታገዘ ሕይወት #እስማኤልን ይወልዳል!! እስማኤል ከእግዚአብሔር ፈቃድ ውጭ የተወለደ የአብርሃም ልጅ ነው!! (ዘፍጥረት 16)።
አብርሃም "ያለ ልጅ እሄዳለሁ፤ ኤሊዔዘር ይወርሰኛል" ብሎ ፈራ። እግዚአብሔር "ከጉልበትህ የሚወጣው ይወርስሃል፤ ዘርህ እንደ ሰማይ ከዋክብት ይበዛል" አለው። አብርሃም እግዚአብሔር የነገረውን አመነ። (ዘፍጥረት 15)።
የእግዚአብሔር የተስፋ ቃል በእርሱ አቆጣጠር ሲዘገይበት ሣራ ከአጋር እንዲወልድ ያቀረበችለትን አሳብ ተቀበለ። ወደ አጋር ገባ፤ እስማኤልም ተፀነሰ። እስማኤል ከተፀነሰ ጀምሮ የአብርሃም ቤት ተረበሸ። (ዘፍጥረት 16)። እግዚአብሔር በመንፈሱ እና በቃሉ ከሚነግረን ውጭ የምንከተላቸው አቋራጭ መንገዶች ዕረፍት ይነሳሉ።
የንጉሥ ልጆች ዛሬ መማር ያለብን ... እግዚአብሔር የገባልንን ተስፋ በራሳችን መንገድ እንዲፈጸም የማድረግ ፈተናን መቃወም ነው!! እስማኤል እንዳይወለድ!! በአብርሃም ቤት እስማኤል ተወለደ!!
እስማኤል፦
• እንደ ሥጋ የተወለደ፣
• ከባሪያይቱ የተወለደ፣
• ለባርነት የተወለደ፣
• አብሮ የማይወርስ እና
• በአባቱ ቤት የማይኖር የሥጋ ልጅ ነው!!
❝የባሪያይቱ ልጅ እንደ ሥጋ ተወልዶአል፥ የጨዋይቱ ግን በተስፋው ቃል ተወልዶአል።❞ —ገላትያ 4፥23።
ይስሐቅ እስኪወለድ መጠበቅ ሲያቅተን የሚወለድ ወይም የተወለደ ልጅ እስማኤል ይባላል!! ተስፋ ሲዘገይ ልብ ይዝላል፤ ያኔ ወደ ተነገረልን መራመድ ያቅተናል!! ከዚያ የእኛን መፍትሔ (እስማኤልን) እንፈልጋለን!!
ዘፍጥረት 21 ሲጀምር ❝እግዚአብሔርም እንደ ተናገረው ሣራን #አሰበ፤ እግዚአብሔርም እንደ ተናገረው ለሣራ #አደረገላት።❞ ይላል። እንዴት ደስ ይላል!! አንዴ ቆም ብለን እናስብ!? ከእግዚአብሔር ይልቅ ለራሳችን ደግ መሆን እንችላለን? እርሱ ቃሉን ያጥፍ ዘንድ ይችላልን? ወይስ እንደ ሰው ይረሳል? በጭራሽ እንዲህ አናውቀውም!!
ሣራ እንደ ተስፋው ቃል ይስሐቅን ለአብርሃም ወለደችለት!! እንዲህ ተጽፏል!! ❝ሣራም ፀነሰች፥ እግዚአብሔርም በተናገረው ወራት ለአብርሃም በእርጅናው ወንድ ልጅን ወለደችለት።❞ —ዘፍጥረት 21፥2። እግዚአብሔር በተናገረው ወራት የሚለውን አስምሩበት!! እርሱ ያለው አይቀርም!! ውጤት ያለው ቢመስልም እስማኤልን ለመውለድ የምናደርገውን ሙከራ እናቁም!! የእግዚአብሔርን ፈቃድ (Will) እና ነገሩ እንዲሆን የሚፈልግበትን ጊዜ (Timing) እንጠብቅ!!
ይስሐቅ በመወለዱ የአብርሃም ቤት ሳቅ ነግሶበታል። በእግዚአብሔር ጊዜ የሚሆንልን ነገር የውስጥ ሰላም አለው!! ከነገሩ መሆን በላይ የሚሰማን ጥልቀት ያለው ዕረፍት ይኖራል!! የታገሰ ወራሹን ይወልዳል!!
የእስማኤል እድሜ ይስሐቅ እስኪወለድ ነው!! ቀድሞ ቢወለድም አብሮ አይወርስም!! ❝አብርሃምንም፦ ይህችን ባሪያ ከነልጅዋ አሳድድ፤ የዚህች ባሪያ ልጅ ከልጄ ከይስሐቅ ጋር አይወርስምና አለችው።❞ —ዘፍጥረት 21፥10። እስማኤል ከነእናቱ መባረሩ ግዴታ ነው!!
ሣራ የእግዚአብሔር ጸጋ ምሳሌ ናት!! አብርሃም የአማኞች ምሳሌ ነው!! አጋር የሕግ ምሳሌ ናት!! እስማኤል የሥጋን ሥራ (የሰውን ጥረት) ያሳያል!! አማኞች መኖር (ማፍራት) ያለብን #በጸጋ ነው!! ከሕጉ ጋር [ከአጋር ጋር] ፍቺ ፈጽመናል!! (ሮሜ 7፥1-7)። ስለዚህ አጋርን ከነልጇ ከቤታችን አባረናል!! ከእግዚአብሔር መንፈስ እና ጸጋ ያልተፀነሰ ነገር እንዲወለድ አንፈልግምና!!