Ab_intra/ከ_ውስጥ


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic
Category: not specified


ይህ channel.
'where the mind goes,the man follows'.
በሚል ሀሳብ
ለአምሮ፣ለሀሳቦቻችን፣ለስሜታችንአና ለዕውቀታችን የሚጠቅም ምግብን የሚያዘጋጅ ነው።
የተለያዩ ሰዎች ጠቃሚ
#ንግግሮች.
#መፅሀፎችን
#መንፈሳዊ ና psyc.ትምህርቶችን or facts.
#ስዕሎችን
#መዝሙሮች/inst music ሁሉ ምናገኝበት ነው።
for more info,comment
@From_Inside_bot

Related channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Category
not specified
Statistics
Posts filter


ሁለቱ ከእጅህ ሊወጡ የማይገባቸው ነገሮች

በሕይወትህ ልታዳብራቸው ከሚገቡህ ጥበቦች መካከል ለሰዎች የሚሰጠውንና የማይሰጠውን ነገር የመለየት ጥበብ አንዱ ነው፡፡ የግል ሕይወትህን አስመልክቶ በሰዎች ውሳኔና ፍላጎት ስር እንዲወድቅ አሳልፈህ የምትሰጣቸውና እንደዚያም በማድረግህ የጠለቀ ችግር የማያመጡብህ ነገሮች አሉ፡፡ ምንም ሰጠህ ምንም ግን እነዚህን ሁለት ነገሮች ሰዎች እንዲወስኑልህ በፍጹም አሳልፈህ አትስጥ፡- 1) የውስጥህ ደስታ፤ 2) የማንነትህን ዋጋ፡፡

የውስጥህን ደስታ
በውስጥህ ደስተኛ የመሆንህንና ያለመሆንህን ጉዳይ ሰዎች ወይም የሰዎች ሁኔታ እንዲወስኑ የፈቀድክ ቀን የስሜትህ ውጣ-ውረድ ይጀምራል፡፡ የአንተ ደስታ የተመሰረተው ሰዎች በአንተ ላይ ባላቸው አመለካከት፣ ስለአንተ በሚያወሩት፣ በሚሰጡህና በሚከለክሉህ እና በመሳሰሉት ሁኔታዎች ላይ ሲሆን የውስጥህን ደስታ አሳልፈህ ሰጠህ ይባላል፡፡ እንደዚህ አይነት አዘቅት ውስጥ እንዳለህ ለማወቅ ከፈለክ በየእለቱ ደስታ ሲርቅህና ወይም ደስ ሲልህ እነዚህ ስሜቶች በምን ላይ እንደተመሰረቱ አጢናቸው፡፡

ሰዎች በአንተ ላይ ባላቸው አመለካከትና ለአንተና በአንተ ላይ በሚያደርጉት ላይ የተመሰረተ ከሆነ ደስተኛ የመሆንህንና ያለመሆንህን ሁኔታ ለሰዎች አሳልፈህ ሰጥተሃል ማለት ነው፡፡ ዛሬ ማን ምን ካደረገብህ ነገር የተነሳ ነው ያን የመሰለ ደስተኛነትህን የጣልከው?

የማንነትህን ዋጋ
ሰዎች ለሁሉም ነገር ዋጋ የማውጣት ልማድ አላቸው፡፡ ይህ ልማዳቸው ከቁሳቁስ አልፎ ለሰውም ዋጋ ወደማውጣት ቀጠና ውስጥ ይከታቸዋል፡፡ ከፈቀድክላቸውና የማንነትህን ዋጋ በእነሱ ተመን አውጪነት ላይ ከጣልከው ከፈጣሪህ የተቀበልከውን የማንነትህን ዋጋ ቀደው በመጣል የራሳቸውን ሰው-ሰራሽ ተመን ይለጥፉብሃል፡፡ የዚህ አይነቱ የሰው ልጅ ጠባብነት ሰለባ ለመሆን ራሰህን አሳልፈህ የሰጠህ ጊዜ ከዋጋህ በታች ራስህን በማውረድ ሰዎች ካስቀመጡበህ ተመን አንጻር ራስህን መሸጥ ትጀምራለህ፡፡

እውነታው ግን አንድና አንድ ነው፣ የሞያህ፣ የእውቀትህ፣ የልምምድህ የመሳሰሉት ከጊዜ በኋላ ያዳበርካቸውና ያጠራቀምካቸው ነገሮች ዋጋ ሊለዋወጥ ይችላል እንጂ የማንነትህ ዋጋ በፍጹም ሊለወጥ አይችልም፤ ሁል ጊዜ ተመን ሊሰጠው በማይችል መልኩ የከበረ ማንነት አለህ፡፡ ዛሬ ከየትኛው ነገርህ የተነሳ ነው በራስህ ላይ ጥሩ ስሜት እስከማይኖርህ ድረስ ሰዎች ዋጋህን የቀያየሩብህ?

ሰዎች የወሰዱትን ደስታህን እንደገና አስመልስ! ሰዎች ያዛቡትን የማንነትህን ዋጋ እንደገና አስተካክል!

https://www.facebook.com/Dr.mehretdebebe/


ያገዘፍከውና ያሳነስከው

የዛሬዋ ሕይወት በትናንትናውና በነገው መካከል እንደ ሳንዱዊች የተጣበቀች ሂደት ነች፡፡ እነዚህ ሁለቱ የሕይወት ገጽታዎች በዛሬው የሕይወትህ ሂደት ላይ ትልቅ ድርሻ አላቸው፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ከእነዚህ ሁለት ገጽታዎች መካከል ያገዘፈው ህይወትህን የማንቀሳቀስ አቅም አለው፡፡

የትናንትናውን ስታገዝፈው፣ የነገው ይደበዝዛል፤ የነገውን ስታገዝፈው ደግሞ የትናንትናው ይደበዝዛል፡፡ በእነዚህ ሁለት ምርጫዎች መካከል የመወሰን መብቱም አቅሙም አለህ፡፡ ብዙ የተሳካላቸው ሰዎች የትናንትናውን ልምምዳቸው “መልካምም” ሆነ “መጥፎ” ያንን ሳይክዱና ፈጽመው ሳይጥሉት ነገር ግን ከትናንትናው ይልቅ የነጋቸውን በማግዘፍ እንደሚያምኑ ይናገራሉ፡፡

የትናንትናውን በማግዘፍና የነገውን በማግዘፍ መካከል መምረጥ ማለት በመቃብር ውስጥ ባለውና በመሕጸን ውስጥ ባለው መካከል እንደመምረጥ ነው፡፡ የትናንትናህ መቃብር ውስጥ ነው - ሞቷል! በተቃራኒው፣ የነገህ ደግሞ በማህጸን ውስጥ ነው - ሊወለድ ተዘጋጅቷል! የትኛውን ትመርጣለህ? ለየጥኛው ትኖራለህ? የትናውን ስታሰላስል ታሳልፋለህ? ወደየትኛው አቅጣጫ መሄድ ትፈልጋለህ?

ያለፈው ታሪክ አስፈላጊነት እንደተጠበቀ ሆኖ፣ ካለፈው ታሪክ ይልቅ የነገው ራእይህ ሲገዝፍ ሕይወት ወደፊት ትሄዳለች፡፡ ከመጣህበት ይልቅ የምትሄድበት ሲገዝፍ! ካለፈው ስቃይ ይልቅ ከዚያ በመማር የያዝከው የመለወጥ ሂደት ሲልቅ! ካለፈው ስኬት ይልቅ የነገው የላቀ ደረጃ ሲተልቅ! አስገራሚ ሕይወት!!! አስገራሚ የወደፊት!!!
Make Ethiopia great again
@megaygra
@from_inside




🛎🛎🛎ዓለም ወዴት እየሄደች ነው🛎

1. መጽሐፍ ቅዱስን ማቃጠል በኡጋንዳ በይፋ ተረጋግጦአል
* በደቡብ አፍሪካ ውስጥ ፣ ወንድ ወይም ሴት በዝሙት ምክንያት ሌላውን የመክሰስ መብት የለውም
*በአሜሪካ እየታየ ያለው የወንድ ለወንድና የሴት ለሴት ጋብቻ
*ጀርመን ወንድም እህቱን ማግባት እንደሚችል ፣ አባት ልጁን:እናት ልጆአን የማግባት ፍቃድን መስጠቱ ፡፡
*የmiami ከተማ በመንገድ ላይ ፣ በቤተ ክርስቲያን ፣ በገቢያ ፣ በእግር ኳስ ሜዳ ወዘተ ውስጥ ወሲባዊ ግንኙነት በማንኛውም መንገድ ማግኘት እንዲችሉ መፍቀዶአ
.*ካናዳ ከእንስሳት ጋር የ sex ግንኙነትን መፍቀዶአ
* በስፔን ውስጥ-የወሲብ ፊልሞች በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች እና በዩኒቨርሲቲዎች መፈቀዱ *- ለአካለ መጠን ያልደረሱ ዝሙት አዳሪዎች ፈቃድ ማሪ ሉክ በህግ መፈቀዱ *በመጨረሻም ዩኤስ አሜሪካ የሰይጣንን ቤተ ክርስቲያን ከፍታለች ፡፡ በይፋ።
⚠️⚠️⚠️የተከበራችሁ ወንድሞች እና እህቶች ፣ መጨረሻው ተቃርቧል ፣ የኢትዮጵያ ትንሳኤ ደርስዋልና ንስሃ እንግባ ⚠️⚠️⚠️
ክርስትያኖች ትኩረታቸው እየተከፋፈሉ ሲሆን ዲያቢሎስ መለኮታዊውን ምህረት ለማስቆም ከፍተኛ ቁጥር ያላቸውን ነፍሳት ከእርሱ ጋር ሊወስድ ይፈልጋል ፡፡ ደቂቃ ካለዎት ... ይህንን መልእክት ያጋሩ ፡፡ ለምን በቤተክርስቲያን ውስጥ እንተኛለን ? ስለ እግዚአብሔር ማውራት ከባድ የሆነው ለምንድነው ሐሜት ለመናገር በጣም ቀላል የሆነው ለምንድነው? የእግዚአብሔርን መልእክት ችላ ማለት ለምን ቀላል ሆነ?
ይህን ነገር መቀየር የምትችለው
አንተ ነህ የተበላሸውን ነገር ለመቀየር ነው እዚህ ምድር ላይ ያለህው።

እግዚአብሔር ይባርኮት ኣሜን !!!
@from_ins1de
@from_ins1de


Yhen bememlket layenew vision enzerga bless u..




ለሰው ጊዜ አነሰው
ጊዜም ሰውን ረታው
በጊዜ ተቀጥሮ
ጊዜን በቀጠሮ
ከንፎ ሮጦ በርሮ
አባከነው ኑሮ!
ለሰው ቦታ አነሰው
ቦታም ሰውን ገዛው
የሰው ቤተ ሰሪ
በቦታ ታሳሪ
ላይኖር አኗኗሪ
ክብሩን አጣ ኗሪ!

ምህረት ደበበ/ነሃሴ 9-12
D/r mehret debebe Twitter page
Join now👇👇👇
@from_ins1de
@from_ins1de
@from_ins1de


#DRMIHRETDEBEBE
#ሕይወትን_በፍቅር

የፍቅርን ትክክለኛ ትርጉም ተማር፡፡ በሕይወትህ ውስጥም ዋናው ነገር ይህ ይሁን፡፡

እግዚአብሔርን አፍቅር፣ ራስህን ውደድ ሌሎችንም እንዲሁ፡፡ ይህንንም ግልጽ ባልሆነ መንገድ አታድርገው፡፡ ትህትና ይኑርህ፡፡ ከእያንዳንዱ ሕይወት ካለው ነገር የምትማረው የሆነ ነገር አለ፡፡

በሌሎች ሰዎች ደስተኛ ሁን፡፡ የሌሎችንም ሰሜት ተረዳ፡፡
ከሞከርክ ሁሉንም ሰው መውደድ ትችላለህ፡፡ ከምስጋና ጋር ቸር፣ ከትችት ጋር ጥንቁቅ፣ አገልግሎት ለመስጠትም የነቃህ ሁን፡፡ ብዙውን ድርሻ የሚወስደው እኛ ለሌሎች የምናደርገው ነው፡፡ ስለዚህ እንክብካቤህን ለሚሹ ከምትችለው ያነሰ አታድርግ፡፡ እውነተኛ ፍቅር ምድር ላይ ያለውን ሁሉ ቋንቋ ይናገራልና፡፡
ብርሃን ወረቀት ላይ በብርሃን እጅ የተጻፈ የብርሃን ቃል፣ ሥፍራን፣ ርቀትንና ጊዜን የሚደመስስ ኃይል ፍቅር ነው፡፡ ስለዚህ ትመሰገን ዘንድ አመስግን፣ ፍቅርን ትቀበል ዘንድ ፍቅርህን ስጥ፣ መልካም ስም የሚገዛው በፍቅር ነውና!
ፍቅር በሚያስደምምና ባልተለመደ መንገድ ይሠራል፡፡ በሕይወትም ውስጥ ፍቅር ሊለውጠው የማይችለው ምንም ነገር የለም፡፡ በጣም የተለመደውን ቦታ እንኳን ሳይቀር ወደ ተዋበ፣ ወደ አሸበረቀና ግርማን ወደ ተላበሰ መንደር ይቀይረዋል፡፡

ፍቅር፡-
1. ራስ ወዳድ ብቻ አይደለም፡- ይረዳል፣ ይራራልም፡፡ ሁሉን በስሜት ሳይሆን በልቡ ያያል፡፡
#DRMIHRETDEBEBE
2. እያንዳንዱ ሰው የሚፈልገው ምላሽ ነው ፡- ከጨቅላው ጀምሮ እስከ ትልቁ፣ እንስሳትን ጨምሮ የሁሉም ሕይወት የሚናገረው ቋንቋ ነው፡፡
3. የሚገዛ አይደለም፡- የዋጋ ተመን የሌለው ነጻ ነው፡፡ ልክ እንደ ንጹሕ ተአምር የሕይወት ጣፋጭ ምስጢር ነው፡፡ ስለዚህ ፍቅርን እንደ ትልቅ ሀብት ቁጠረው፡፡ በጥልቀትና በፍጹም ልብ ውደድ፡፡ ይህንንም በደስታ አድርገው፡፡ ምናልባት በሂደቱ ውስጥ ትጐዳ ይሆናል፡፡ ነገር ግን ሕይወትን ሙሉ ለሙሉ ለመኖር ብቸኛው መንገድ ነው፡፡ ምን ጊዜም ቢሆን ታላቅ ፍቅርና ታላቅ ስኬት ትልልቅ ፈተናዎች አሉበት፡፡ ስለዚህ ያለ ማቋረጥ ፍቅርን ለግስ፡፡ ወደ ሌሎች ያፈሰስከው ፍቅር መልሶ ወደ አንተ መፍሰሱ አይቀሬ ነው፡፡ ከመቀበል ይልቅ መስጠት የበዛ በረከት ስለሆነ በዚህ ውስጥ በመኖር ልዩ ደስታን ማግኘት እንችላለን፡፡
የማያስተውል ዓይን ብቻ በሰው ውስጥ የሉትን መልካምነቶች ማየት አይችልም እንጂ ፍቅር እውር አይደለም፡፡ እውነተኛ ፍቅርና ርኅራኄ ሁልጊዜም ደስታዎቹን ያጠራል፡፡ በትክክል ለማየት ይረዳል፣ ይፈውሳል፡፡ ክፉ ስሜት እንዲደበዝዝ፣ መልካሙ መንፈስ ደግሞ እንዲነቃ ያስችላል፡፡ በሰው ውስጥ ያለውን መጥፎውን ሳይሆን መልካሙን ነገር ያፋጥናል፡፡ ከብርሃን ይልቅ የሚያድስ፣ ከአበቦች ይልቅ መዓዛ ያለው፣ ከብዙ ዜማዎችም ይልቅ ጥዑም ነው፡፡
አስታውስ! ሕይወት የምትለካው ሌሎችን ሰዎች በመሰጥንባቸው ጊዜያቶች ሳይሆን እኛ በሕይወት በተመሰጥንባቸው ቅጽበቶች ነው፡፡ ሰው ሃይማኖቱን ሲወድ በሃይማኖቱ ሥር ያሉትን ያፈቅራል፡፡ ሰው እግዚአብሔርን ሲያፈቅር ግን የሰውን ዘር ሁሉ ይወዳል ፍቅር ኃይለኛ ልብን የማስታገስ፣ እንደ ድንጋይ የሆነውን ነገር የማለስለስ፣ ቋጠሮንም የመፍታት ለዛ አለው፡፡

↓↓ ቅን ከሆኑ ሼር አድርጉ ↓↓
$DRMIHRETDEBEBE
@from_ins1de
@from_ins1de


ሰላም እንዴት ናችሁ ባለፈው ስለ ፍቅር አንዳንድ ነገር ብያችሁ ነበር ፍቅር እንዲ ሲገለጵስ።


“You are not here to find love, nor to be greeted by happiness at every turn, nor to be showered with kindness, nor to be celebrated by all, to forever remain a child.

No. You came here to create love out of war.

Your soul willingly left its blissful place beyond all troubles to descend into a stifling frame of bone, blood and flesh. Why? Because only here can inner strength be forged by pain, can wisdom be nurtured by failure, can love be the reward of those who choose to give love. Your soul came here to struggle with the bitter things of life and squeeze out of them a syrup of sweet, inner joy.

And as there is no sweetness as succulent as bittersweet, so there is no river of love that runs as deep as the love forged through a battle of the heart, no strength as powerful as that wrestled from the hands of an enemy through stubborn, defiant resolve, no wisdom as the wisdom gained by stumbling in darkness, standing up again, stumbling and walking again, and again.

All that is good, all that has meaning, all is up to you alone."

Rabbi Tzvi Freeman
Join us 👇👇👇
@from_ins1de
@from_ins1de
@from_ins1de


አሸናፊነት አሸናፊነት የሚለካው በሌላ ሰው ላይ የበላይነት ማሳየት አይደለም፡፡ማሸነፍ የሚጀምረው ራሳችሁ ጋር ያለን ተግዳሮት ስትረቱ አለመብቃትን አስወግዳችሁ መብቃትን ስታኖሩ ወስጣችሁ የተቀመጠን ፍርሀት አሰወግዳችሁ ድፍረትን ሰታሰቀምጡ አንደሁም አለመቻልን በይቻላል መንፈስ ስትሞላ እናንተ ማለት አሽናፈነት ጀምራችኋል ፡፡አትሳሳቱ አሸናፊነት ማብቂያ የለውም ፡፡ ሁሌም ለማሸነፍ መኖር ጀምሩ እናንተ በሰውች ላይ ለመሰልጠን አትድከሙ ሀይላችሁን ትጨርሳላችሁ ፡፡ራሳችሁን አሸንፉ ህይወትን ድል እያደረጋችሁ ነው ፡፡ማሸነፍ ማለት ውሰጣችሁን ያለውን ብቃት የምትገልጡበት ሀይል እነጂ ሀይለኛ መሆን አይደለም ፡፡ተሸንፋለሁ ብላችሁ አታስቡ ማሸነፋችሁ ያለው እናተው እጅ ላይ ነው ፡፡ለመሸነፋችሁ ስበብ አትፈልጉ ከውጪ የሚጀምር አሸናፊነት የለም ዛሬም ራሳችሁን ተመልከቱ ማሸነፍ ትችላላችሁ።
@from_ins1de
@from_ins1de
@from_ins1de


ፍቅር

ፍቅር ማለት ምን ማለት ነው ተብለን ብንጠየቅ ሁላ ችንም በአማርኛ ይሄ ማለት ነው በግሪክ ደግሞ 5 አይነት ትርጉም አለው ወይም ሌላ ብዙ ትርጓሜ እንሰጠዋለን።

ልክ ነው የጌታ ፍቅር አጋፔ (unconditional love) ወይም ነገሮች ላይ ጥገኛ ያልሆነ ፍቅር ዝም ብሎ የሚያፈቅር ምክኒያታዊ ያልሆነ ነው።

አጋፔ በርግጥ የእግዚአብሔር ፍቅርን ይገልጻል?

እኔ ይገልጻል ብዬ አላስብም ምክንያቱም ጌታ ያለ ምክንያት ብቻ ሳይሆን እራሱ ጌታ ፍቅር ስለሆነ ጌታ ያፈቅራል ብሎ ለመግለጽ ይከብዳል።

እስቲ ይሄን ቃል እንይ:-

“ዓለም ሳይፈጠር፥ በፊቱ ቅዱሳንና ነውር የሌለን በፍቅር እንሆን ዘንድ በክርስቶስ መረጠን።”
— ኤፌሶን 1፥4

አለም ሳይፈጠር ካለ በሌላ አማርኛ ሀጥያት ወደ ምድር ሳይገባ አዳም እና ሄዋን ወደ ምድር ሳይመጡ ማለት ነው።
ስለዚህ አዳም ሄዋን እኛ ወደ ምድር ሳንመጣ ምን አይነት በሁኔታዎች የወሰን (unconditional ) ሊሆን ይችላል ? ምክንያቱም በዚያን ጊዜ ምንም አይነት ሁኔታ የለም ነበር::

ጌታ ያፈቀረን ነገሮች ሚባሉ ነገሮች ሳይፈጠሩ ነው።

የጌታ ፍቅር ከአጋፔ በላይ ነው!
የጌታ ፍቅር በአጋፔ አይለካም!

ጌታ ያፈቅራናል ብል ያንስብኛል! ሌላ ቃል ስሌለኝ ግን አንደሚያፈቅራቹ አትርሱ ልበላችሁ!

“በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና።”
— ዮሐንስ 3፥16
እንዲሁ ማለት ቅድመ ሁኔታ ሚባለው ነገር ሳይፈጠር ማለት ነው።
Greatly loved:-ያለ ቅጥ:- በጣም :-በክብር
Dearly prized:-በጣም ውድ
Via kaleb Isayas
@from-ins1de
@from-ins1de


ሰላም የዚህ channel ቤተሰቦች ላልተወሰነ ጊዜ ጠፍቼ ነበረ ነገር ግን አሁን በድጋሚ ወደናንተ ተመልሼአለው አብራችሁን ስላላችሁ አመሰግናለሁ።


Forward from: NAHOM ENDRIAS
#TRUTH_ZONE

ወዳጄ
ህይወት ተከታትለው የሚመጡ ተፈጥሮአዊ ድንገተኛ ለውጦች ድምር ናት፡፡ ለውጦችን ለመታገል አትጣሩ፡፡ በራሳችሁ ላይ ሀዘን ከመጥራት በቀር የምታተርፉት ነገር የለም እውነታ እውነታ ይሆን ዘንድ ተውት ነገሮች ሁሉ ተፈጥሮአዊ መንገዳቸውን ተከትለው እንደፈቀዱት እንዲፈሱ እድል ስጡዋቸው ሁሉም ነገር ባለበት ሁኔታ ደስ ይበላችሁ፡፡
ይህን ስትረዱ መኖር ይቀላችኋል፡፡

@TRUTHZONE @TRUTHZONE


It is comfort that creates tradition. It is discomfort that creates transformation. The average person doesn’t know what he or she is capable of until change affects him or her. In general, the human spirit thrives on finding solutions to chaotic conditions.



- Dr Myles Munroe
Join. And share

@from_ins1de
@from_ins1de
@from_ins1de


♨ህልምህ እንዳይሳካ የሚያደርግ አንድ መጥፎ ነገር አለ " አይሳካልኝም " የሚል ፍርሃት ።

♨ ስትሸነፍ አይደለም የተሸነፍከው በቃኝ ብለህ ስታቆም እንጂ !

♨ ሰዎች እንዲረዱህ ከመጠን በላይ አትድከም ሰዎች እንደሆኑ የሚሰሙት መስማት የሚፈልጉትን ብቻ ነውና ።

♨ አንድቀን ከእንቅልፍህ ስትነቃ ጊዜህ አልቆ ልታገኘው ትችላለህ ፤ ስለዚህ ልታደርገው የምትፈልገውን ነገር አሁኑኑ አድርገው ።

♨ስኬታማ ለመሆን ከፈለክ አንድ ሕግ አክብር ፈጽሞ ራስህን አትዋሽ ።

♨ የህይወት ምስጢሩ ሰባት ጊዜ ወድቆ ስምንት ጊዜ መነሳት ነው ።

♨ በዓለም ላይ ያለ ማንኛውም ሰው ሊገባው የሚችለው ቛንቛ አለ " ፍቅር " !

👉 ስትሸነፍ አይደለም የተሸነፍከው በቃኝ ብለህ ስታቆም እንጂ !

👉 አንድ ነገር አስታውስ ልብህ ያለበት ቦታ ሀብትህም ተቀምጧል ።

Share👇👇👇join
@from_ins1de
@from_ins1de
@from_ins1de


It's easy to blame God
But harder to fix things

NF
@from_ins1de


1. Winning is an attitude

2. winning is contagious

3. Winners have short memories

4. Winners are competitive with themselves and others

5. Winners rise to the occasion

6. Winners accept defeat gracefully and come back strong

7. Winners understand the law of averages and their average is high

8. Winners win wherever they go

9. Winners have charisma and can affect a whole culture

10. Winners attract winners
💥@from_ins1de
💥@from_ins1de
💥@from_ins1de




Forward from: MARANATA✔
እስማኤል እንዳይወለድ

ከእግዚአብሔር የተወለድን ነገሮችን በራሳችን መንገድ ብቻ ማስተናገድ አንችልም!! ለእግዚአብሔር መተዉ ያለብን ነገር አለ!! በውስጣችን ባለው በመንፈሱ ሕይወታችን ወደሚመራበት ደረጃ #ማደግ አለብን!?

❝በእግዚአብሔር መንፈስ የሚመሩ ሁሉ እነዚህ የእግዚአብሔር ልጆች ናቸውና።❞ —ሮሜ 8፥14።

በመንፈሱ ያልተመራ፤ በጸጋው ያልታገዘ ሕይወት #እስማኤልን ይወልዳል!! እስማኤል ከእግዚአብሔር ፈቃድ ውጭ የተወለደ የአብርሃም ልጅ ነው!! (ዘፍጥረት 16)።

አብርሃም "ያለ ልጅ እሄዳለሁ፤ ኤሊዔዘር ይወርሰኛል" ብሎ ፈራ። እግዚአብሔር "ከጉልበትህ የሚወጣው ይወርስሃል፤ ዘርህ እንደ ሰማይ ከዋክብት ይበዛል" አለው። አብርሃም እግዚአብሔር የነገረውን አመነ። (ዘፍጥረት 15)።

የእግዚአብሔር የተስፋ ቃል በእርሱ አቆጣጠር ሲዘገይበት ሣራ ከአጋር እንዲወልድ ያቀረበችለትን አሳብ ተቀበለ። ወደ አጋር ገባ፤ እስማኤልም ተፀነሰ። እስማኤል ከተፀነሰ ጀምሮ የአብርሃም ቤት ተረበሸ። (ዘፍጥረት 16)። እግዚአብሔር በመንፈሱ እና በቃሉ ከሚነግረን ውጭ የምንከተላቸው አቋራጭ መንገዶች ዕረፍት ይነሳሉ።

የንጉሥ ልጆች ዛሬ መማር ያለብን ... እግዚአብሔር የገባልንን ተስፋ በራሳችን መንገድ እንዲፈጸም የማድረግ ፈተናን መቃወም ነው!! እስማኤል እንዳይወለድ!! በአብርሃም ቤት እስማኤል ተወለደ!!

እስማኤል፦
• እንደ ሥጋ የተወለደ፣
• ከባሪያይቱ የተወለደ፣
• ለባርነት የተወለደ፣
• አብሮ የማይወርስ እና
• በአባቱ ቤት የማይኖር የሥጋ ልጅ ነው!!

❝የባሪያይቱ ልጅ እንደ ሥጋ ተወልዶአል፥ የጨዋይቱ ግን በተስፋው ቃል ተወልዶአል።❞ —ገላትያ 4፥23።

ይስሐቅ እስኪወለድ መጠበቅ ሲያቅተን የሚወለድ ወይም የተወለደ ልጅ እስማኤል ይባላል!! ተስፋ ሲዘገይ ልብ ይዝላል፤ ያኔ ወደ ተነገረልን መራመድ ያቅተናል!! ከዚያ የእኛን መፍትሔ (እስማኤልን) እንፈልጋለን!!

ዘፍጥረት 21 ሲጀምር ❝እግዚአብሔርም እንደ ተናገረው ሣራን #አሰበ፤ እግዚአብሔርም እንደ ተናገረው ለሣራ #አደረገላት።❞ ይላል። እንዴት ደስ ይላል!! አንዴ ቆም ብለን እናስብ!? ከእግዚአብሔር ይልቅ ለራሳችን ደግ መሆን እንችላለን? እርሱ ቃሉን ያጥፍ ዘንድ ይችላልን? ወይስ እንደ ሰው ይረሳል? በጭራሽ እንዲህ አናውቀውም!!

ሣራ እንደ ተስፋው ቃል ይስሐቅን ለአብርሃም ወለደችለት!! እንዲህ ተጽፏል!! ❝ሣራም ፀነሰች፥ እግዚአብሔርም በተናገረው ወራት ለአብርሃም በእርጅናው ወንድ ልጅን ወለደችለት።❞ —ዘፍጥረት 21፥2። እግዚአብሔር በተናገረው ወራት የሚለውን አስምሩበት!! እርሱ ያለው አይቀርም!! ውጤት ያለው ቢመስልም እስማኤልን ለመውለድ የምናደርገውን ሙከራ እናቁም!! የእግዚአብሔርን ፈቃድ (Will) እና ነገሩ እንዲሆን የሚፈልግበትን ጊዜ (Timing) እንጠብቅ!!

ይስሐቅ በመወለዱ የአብርሃም ቤት ሳቅ ነግሶበታል። በእግዚአብሔር ጊዜ የሚሆንልን ነገር የውስጥ ሰላም አለው!! ከነገሩ መሆን በላይ የሚሰማን ጥልቀት ያለው ዕረፍት ይኖራል!! የታገሰ ወራሹን ይወልዳል!!

የእስማኤል እድሜ ይስሐቅ እስኪወለድ ነው!! ቀድሞ ቢወለድም አብሮ አይወርስም!! ❝አብርሃምንም፦ ይህችን ባሪያ ከነልጅዋ አሳድድ፤ የዚህች ባሪያ ልጅ ከልጄ ከይስሐቅ ጋር አይወርስምና አለችው።❞ —ዘፍጥረት 21፥10። እስማኤል ከነእናቱ መባረሩ ግዴታ ነው!!

ሣራ የእግዚአብሔር ጸጋ ምሳሌ ናት!! አብርሃም የአማኞች ምሳሌ ነው!! አጋር የሕግ ምሳሌ ናት!! እስማኤል የሥጋን ሥራ (የሰውን ጥረት) ያሳያል!! አማኞች መኖር (ማፍራት) ያለብን #በጸጋ ነው!! ከሕጉ ጋር [ከአጋር ጋር] ፍቺ ፈጽመናል!! (ሮሜ 7፥1-7)። ስለዚህ አጋርን ከነልጇ ከቤታችን አባረናል!! ከእግዚአብሔር መንፈስ እና ጸጋ ያልተፀነሰ ነገር እንዲወለድ አንፈልግምና!!

20 last posts shown.

92

subscribers
Channel statistics