ሁለቱ ከእጅህ ሊወጡ የማይገባቸው ነገሮች
በሕይወትህ ልታዳብራቸው ከሚገቡህ ጥበቦች መካከል ለሰዎች የሚሰጠውንና የማይሰጠውን ነገር የመለየት ጥበብ አንዱ ነው፡፡ የግል ሕይወትህን አስመልክቶ በሰዎች ውሳኔና ፍላጎት ስር እንዲወድቅ አሳልፈህ የምትሰጣቸውና እንደዚያም በማድረግህ የጠለቀ ችግር የማያመጡብህ ነገሮች አሉ፡፡ ምንም ሰጠህ ምንም ግን እነዚህን ሁለት ነገሮች ሰዎች እንዲወስኑልህ በፍጹም አሳልፈህ አትስጥ፡- 1) የውስጥህ ደስታ፤ 2) የማንነትህን ዋጋ፡፡
የውስጥህን ደስታ
በውስጥህ ደስተኛ የመሆንህንና ያለመሆንህን ጉዳይ ሰዎች ወይም የሰዎች ሁኔታ እንዲወስኑ የፈቀድክ ቀን የስሜትህ ውጣ-ውረድ ይጀምራል፡፡ የአንተ ደስታ የተመሰረተው ሰዎች በአንተ ላይ ባላቸው አመለካከት፣ ስለአንተ በሚያወሩት፣ በሚሰጡህና በሚከለክሉህ እና በመሳሰሉት ሁኔታዎች ላይ ሲሆን የውስጥህን ደስታ አሳልፈህ ሰጠህ ይባላል፡፡ እንደዚህ አይነት አዘቅት ውስጥ እንዳለህ ለማወቅ ከፈለክ በየእለቱ ደስታ ሲርቅህና ወይም ደስ ሲልህ እነዚህ ስሜቶች በምን ላይ እንደተመሰረቱ አጢናቸው፡፡
ሰዎች በአንተ ላይ ባላቸው አመለካከትና ለአንተና በአንተ ላይ በሚያደርጉት ላይ የተመሰረተ ከሆነ ደስተኛ የመሆንህንና ያለመሆንህን ሁኔታ ለሰዎች አሳልፈህ ሰጥተሃል ማለት ነው፡፡ ዛሬ ማን ምን ካደረገብህ ነገር የተነሳ ነው ያን የመሰለ ደስተኛነትህን የጣልከው?
የማንነትህን ዋጋ
ሰዎች ለሁሉም ነገር ዋጋ የማውጣት ልማድ አላቸው፡፡ ይህ ልማዳቸው ከቁሳቁስ አልፎ ለሰውም ዋጋ ወደማውጣት ቀጠና ውስጥ ይከታቸዋል፡፡ ከፈቀድክላቸውና የማንነትህን ዋጋ በእነሱ ተመን አውጪነት ላይ ከጣልከው ከፈጣሪህ የተቀበልከውን የማንነትህን ዋጋ ቀደው በመጣል የራሳቸውን ሰው-ሰራሽ ተመን ይለጥፉብሃል፡፡ የዚህ አይነቱ የሰው ልጅ ጠባብነት ሰለባ ለመሆን ራሰህን አሳልፈህ የሰጠህ ጊዜ ከዋጋህ በታች ራስህን በማውረድ ሰዎች ካስቀመጡበህ ተመን አንጻር ራስህን መሸጥ ትጀምራለህ፡፡
እውነታው ግን አንድና አንድ ነው፣ የሞያህ፣ የእውቀትህ፣ የልምምድህ የመሳሰሉት ከጊዜ በኋላ ያዳበርካቸውና ያጠራቀምካቸው ነገሮች ዋጋ ሊለዋወጥ ይችላል እንጂ የማንነትህ ዋጋ በፍጹም ሊለወጥ አይችልም፤ ሁል ጊዜ ተመን ሊሰጠው በማይችል መልኩ የከበረ ማንነት አለህ፡፡ ዛሬ ከየትኛው ነገርህ የተነሳ ነው በራስህ ላይ ጥሩ ስሜት እስከማይኖርህ ድረስ ሰዎች ዋጋህን የቀያየሩብህ?
ሰዎች የወሰዱትን ደስታህን እንደገና አስመልስ! ሰዎች ያዛቡትን የማንነትህን ዋጋ እንደገና አስተካክል!
https://www.facebook.com/Dr.mehretdebebe/