በየሰፈሩ ሰፍረን
በየአጥሩ ተንጠልጠለን
አድዋን ያህል
አድባር ጥለን
ካምና ርቀን
ዛሬን ንቀን
ነገን ናፍቀን
መራመዱ እየጨነቀን
በየጥጉ ተናንቀን
ቀኑን ማሰብ እስኪያስፈራው
የታለ ባለፈረሱ?
የታለ ባለ ባንዴራው?
የታል የትውልድ አደራው?
አድዋን ያህል ትልቅ ጥለት
አድዋን ያህል ህብር ቀለም
ክብሩ ገብቶን
ፍሬው ታይቶን
ሳንደምቅበት ተያይዘን
ሳንኮራበት ታሪክ መዘን
በጊዜ ፊት እንዲህ ፈዘን
ያከበረን ያስከበረን
ኩራት ሆኖ ያዘለቀን
አድዋ ያህል ዘ ላ ለ ም ቀን
ስሙን መጥራት
ድሉን ማሰብ ተናነቀን?!
By Thomas lemma
@getem
@getem
@paappii
በየአጥሩ ተንጠልጠለን
አድዋን ያህል
አድባር ጥለን
ካምና ርቀን
ዛሬን ንቀን
ነገን ናፍቀን
መራመዱ እየጨነቀን
በየጥጉ ተናንቀን
ቀኑን ማሰብ እስኪያስፈራው
የታለ ባለፈረሱ?
የታለ ባለ ባንዴራው?
የታል የትውልድ አደራው?
አድዋን ያህል ትልቅ ጥለት
አድዋን ያህል ህብር ቀለም
ክብሩ ገብቶን
ፍሬው ታይቶን
ሳንደምቅበት ተያይዘን
ሳንኮራበት ታሪክ መዘን
በጊዜ ፊት እንዲህ ፈዘን
ያከበረን ያስከበረን
ኩራት ሆኖ ያዘለቀን
አድዋ ያህል ዘ ላ ለ ም ቀን
ስሙን መጥራት
ድሉን ማሰብ ተናነቀን?!
By Thomas lemma
@getem
@getem
@paappii