"ድንቄም ቆራጭ"😁😁😁
"""""""""""""""""""""
ከልብ ተሠርንቆ ልውጣ አልውጣ እያለ፤
ያስገባንው ነገር ከአቅም ካየ"ለ።
ይውጣ ምናባቱ ልብን ከበሽተ ካላረገን ደህና፤
አንቅሮ መትፋት ነው ከሚያሳጣን ጤና።
ሰውም እንደዚህ ነው፥
የልባችን እሳት የልባችን ንዳድ ለሱ ከበረደው፤
የፍቅራችን ሙቀት ቀዝቅዞ ከታየው።
ምን ሊያረግ ይቀመጥ ሊሆነን ፈተና፤
ከተመቸው ይሂድ
መንገዱ ያውና።
የልባችን መሻት መሻቱ ካልሆነ፤
የመውደድ ፍላቱ ከሱው ከተነነ።
ልቡ የሸፈተን አስረን ላናስቀረው፤
መንገዱ ያውና ይሂድ ከተመቸው።
ብዬ እፎክርና ዝቼ በሃሳቤ፤
አስሮ ያስቀመጠው ይሸነፋል ልቤ።
አድሮ ልመና...ተው ፍታኝ
የቃልህ እስረኛ ነኝ🥹
ምን ላርግ ከእኔ ዘንድ አልሰራም
✍ጦቢያ
ቀን 21
የካቲት፦2017-አርብ
@getem@getem@getem