የ #አሜሪካው የቢትኮይን ኩባንያ በ #ኢትዮጵያ የመጀመሪያውን የማስፋፍያ ምዕራፍ ማጠናቀቁን አስታወቀ
የአሜሪካው የቢትኮይን ኩባንያ "ቢአይቲ ማይኒን" በኢትዮጵያ የመጀመሪያውን የማስፋፍያ ምዕራፍ ማጠናቀቁን አስታውቋል።
ኩባንያው 14.2 ሚሊዮን ዶላር መዋዕለ ንዋይ በማፍሰስ የቢትኮይን ማቀነባበሪያ ቁሳቁሶችን እና የመረጃ ማዕከሎችን መግዛቱን በትናንትናው ዕለት ይፋ አድርጓል።
የመጀመሪያው ምዕራፍ 35 ሜጋዋት የመረጃ ማዕከልና 17,869 ቢትኮይን ማይኒንግ ማሽኖችን 2.2 ሚሊዮን ዶላር ጥሬ ገንዘብ እንዲሁም 369,031,800 'ኤ ክላስ' ድርሻዎችን በማጣመር መግኘት ያካተተ ነው ተብሏል።
ኩባንያው እ.ኤ.አ በ2025 መጀመሪያ ይጠናቀቃል ተብሎ ለሚጠበቀው ለሁለተኛው ምዕራፍ የማስፋፍያ ፕሮጀክት ተጨማሪ የመረጃ ማዕከላት ግዢዎችን በመፈጸም 51 ሜጋዋት የሚጠቀም ማዕከል ባለቤት ለመሆን ማቀዱ ተጠቁሟል።
የማስፋፍያ ፕሮጀክቱን ለማጠናቀቅም 45 ሚሊዮን 278 ሺህ የአክሲዮን ድርሻዎችን ለመሸጥ ማሰቡን ክሪፕቶ ኒውስ ዘግቧል።