በሶማሊያ ስለሚሰፍረው የግብጽ ጦር ዙሪያ ሁለቱ ሀገራት በቀጣይ ሳምንት እንደሚመክሩ ተገለጸ
ግብጽ በአፍሪካ ህብረት ልዩ ተልዕኮ ተሰጥቶት በሶማሊያ በሚሰማራው የጦር ሰራዊቷ ዙሪያ በቀጣይ ሳምንት ከሶማሊያ መንግስት ባለስልጣናት ጋር እንደምትመክር ተገለጸ።
በሁለቱ ሀገራት መካከል ውይይቱ የሚካሄደው ከጥር 7 እስከ 9 ቀን 2017 ዓ.ም መሆኑን የሶማሊያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አሊ ባርካድ እንደነገሩት ብሉንበርግ አስነብቧል።
ግብጽ አትሚስን በሚተካው በአዲሱ በሶማሊያ የአፍሪካ ህብረት የድጋፍ ተልዕኮ (AUSSOM) ውስጥ እንደምትሳተፍ የሀገሪቱ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ባድር አብዳላቲ ማረጋገጣቸውን መዘገባችን ይታወሳል።
በሶማሊያ አዲስ ተልዕኮ ተሰጥቶት በሚሰፍረው የአፍሪካ ህብረት የሰላም አስከባሪ ጦር AUSSOM ግብጽ ወታደሮቿን የምታዋጣው ከሶማሊያ በኩል በቀረበላት ጥሪ መሰረት ነው ሲል ብሉንበርግ በዘገባው አመላክቷል።
የሶማሊያ መንግሥት #የኢትዮጵያ ወታደሮች በአፍሪካ ኅብረት ልዑክ ውስጥ መካተታቸውን በተመለከተ “መልሶ ለማጤን” ዝግጁ መኾኑን ማስታወቁን መዘገባችን ይታወሳል።
ብሉንበርግ ባስነበበው ዘገባው የሶማሊያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ኢትዮጵያ የአውሶም ጦር ውስጥ ምን ያክል ቁጥር ያለው ሰራዊት እንድታሰማራ እንደተፈቀደላት የታወቀ ነገር አለመኖሩን እንደነገሩት ጠቁሟል።
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤት ከቀናት በፊት ታህሳስ 18 ቀን 2017 ዓ.ም ባካሄደው ስብሰባ በሶማሊያ በሰላም ማስከበር ተግባር ተሰማርቶ በቆየው አትሚስ አተካክ ረቂቅ ውሳኔ ላይ ውሳኔ ማሳለፉን መዘገባችን ይታወሳል።
አትሚስን በመተካት ልዩ ተልዕኮ ተሰጥቶ ለሚሰፍረው የሰላም አስከባሪ ጦር ይሁንታ መስጠቱን፤ የቆይታ ግዜውም 12 ወራት እንዲሆን መፍቀዱን በዘገባው ተካቷል።