ሩሲያ በአንድ ዓመት ዉስጥ ከ427 ሺ በላይ ወታደሮቿ ተገድለዋል አልያም ቆስለዋል ስትል ዩክሬን አስታወቀች
እ.ኤ.አ እስከ ታህሳስ 30 ቀን 2024 ድረስ የዩክሬን ጦር ዋና አዛዥ ኮሎኔል ጄኔራል ኦሌክሳንደር ሲርስኪ እንደተናገሩት በአንድ ዓመት ዉስጥ 427,000 የሩስያ ወታደሮች ሞተዋል ወይም ቆስለዋል ብለዋል።ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ባለው ቁጥራዊ መረጃ መሰረት በ 2024 የሩስያ ኪሳራ በአማካይ 1,180 ወታደሮች በቀን እንደሚገደሉ አልያም እንደሚቆስሉ ያሳያል፡፡ከፍተኛው የሩሲያ ወታደርች የተመዘገበዉ በህዳር ወር 45,720 እና በታህሳስ ወር 48,670 ኪሳራ መድረሱን የዩክሬን የመከላከያ ሚኒስቴር አስታውቋል።
ከእነዚህ የሩስያ ወታደሮች ውስጥ ምን ያህሉ እንደተገደሉ እና ምን ያህል እንደተጎዱ እንዲሁም ከጦር ሜዳ እንደተወገዱ ግን ግልጽ አይደለም፡፡ሚድያዞና የተባለው የራሺያ ገለልተኛ ድረ-ገጽ እንደዘገበው ከጥር 1 ቀን 2024 እስከ ታህሳስ 17 ቀን 2024 ባሉት ወራት ቢያንስ 31 ሺ 4 መቶ 81 የሩስያ ወታደሮች መሞታቸው ተረጋግጧል ብሏል።ሚዲያዞና የተገደሉትን የሩሲያ ወታደሮች ስም ለማጠናቀር የይፋዊ ምንጭ ምርምርን ይጠቀማል ፣መረጃውን በሟች ታሪኮች ፣በዘመዶቻቸዉ፣ከአካባቢ ባለስልጣናት መግለጫዎች እና ሌሎች የህዝብ ሪፖርቶችን ዋቢ ያደርጋል።
ጦርነቱ በጀመረበት ሶስት አመት ገደማ ጦሩ ወደ ዩክሬን እየገሰገሰ ሲሆን ሩሲያ በምስራቃዊ ዩክሬን የምትገኝ የኩራክሆቭን በሀብት የበለፀገች ከተማን መያዙን በዚህ ሳምንት አስታዉቃለች።ምንም እንኳን ዩክሬን በሩሲያ ኩርስክ ውስጥ አዲስ ጥቃትን ብትጀምርም የሞስኮ ኃይሎች በምስራቃዊ ዩክሬን ውስጥ ግስጋሴያቸዉን ቀጥለዋል፡፡በዋሽንግተን ዲሲ መቀመጫዉን ባደረገው የጦርነት ጥናት ተቋም (አይ ኤስ ደብሊው) በተሰበሰበው የጂኦግራፊያዊ መረጃ መሰረት የሩስያ ኃይሎች በ2024 ዓመት 4,168 ካሬ ኪሎ ሜትር የዩክሬን ግዛትን ተቆጣጥረዋል።
@ዳጉ ጆርናል