ቻይና በበሽታ ስጋት ከታንዛኒያ፣ ሶማሊያና ሌሎች በርካታ ሀገራት የሚገቡ የእንስሳት ምርቶችን አገደች
ቻይና በተለይም በጎች ወደ አገር ውስጥ እንዳይገቡ ከልክላለች። ከዚህ በተጨማሪ ቻይና ፍየል፣ዶሮና ሌሎች የእንስሳት ተዋፅኦም ከአፍሪካ፣እስያ እና አውሮፓ ወደ ሀገሯ እንዳይገቡ ከልክላለች።
ክልከላው ሊጣል የቻለዉ ከበግና ከፍየሎች የሚነሳ የእግርና የአፍ በሽታ መታየት መጀመሩን ተከትሎ ነው። እግዱ በህይወት ያሉ እንስሳት ብሎም የተቀነባበረ የስጋ ውጤት የሚያጠቃልል ሲሆን ቻይና እዚህ ውሳኔ ላይ ልትደርስ የቻለችውም የዓለም የእንስሳት ጤና ድርጅት በተለያዩ ሀገራት የእንስሳት በሽታ በወረርሺኝ መልኩ እየታየ ነው ማለቱን ተከትሎ ነው።
ከዓለማችን ግዙፍ የእንስሳት ስጋ ተቀባይ በሆነችዉ ቻይና የተወሰነው ውሳኔ እንደ ጋና፣ ሶማሊያ፣ ኳታር፣ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ፣ ናይጄርያ፣ ታንዛንያ፣ ቡልጋርያና ኤርትራ የመሳሰሉ ሀገራት ላይ ተፅእኖ ያሳድራል ተብሏል።
ከነዚህ ሀገራት በተጨማሪ ቻይና ከፍልስጤም፣ አፍጋኒስታን፣ ኔፓልና ባንግላዲሽ የሚመጡ የእንስሳት ተዋፅኦ ላይ እገዳ የጣለች ሲሆን ሙሉ በሙሉ ባይሆንም ከጀርመን ወደ ቻይና የሚላኩ የተወሰኑ የስጋ ምርቶች ላይም እገዳ ጥላለች።