በትግራይ በ14 ወረዳዎች 266 ትምህርት ቤቶች እድሳት ሊደረግላቸው ነዉ
የዓለም ባንክ በትግራይ በተካሄደው ጦርነት ሳቢያ የወደሙ ትምህርት ቤቶችን፣ የጤና ተቋማትን እና የውሃ አቅርቦት ተቋማት የእድሳት ግንባታ ለማድረግ የሚያስችል 3 ነጥብ 52 ቢሊየን ብር ድጋፍ ማድረጉ ተገለጸ። ከዓለም ባንክ በተገኘው ድጋፍ በ14 ወረዳዎች 266 ትምህርት ቤቶች እድሳት በተጨማሪ 84 የጤና ተቋማት እና 844 የውሃ አቅርቦት የሚሰጡ ጉድጓዶች ላይ የእድሳት ግንባታ እንደሚካሄድ ተጠቁሟል።
ይህ የተገለጸው በውቅሮ ከተማ በዓለም ባንክ ድጋፍ የእድሳት ሥራ በሚደረግላቸው ፕሮጀክቶች ዙሪያ በተዘጋጀ የምክክር መድረክ ላይ ሲኾን በመድረኩ ላይ የክልል እንዲሁም የወረዳዎች አመራሮች እና ተወካዮች እየተሳተፉ ይገኛሉ። የትግራይ ተሐድሶና መልሶ ማቋቋም ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ቴድሮስ ገ/እግዚአብሔር እንደተናገሩት በትግራይ ጦርነት ያስከተለው ውድመትና ጉዳት ከፍተኛ በመኾኑ በሁሉም የትግራይ አካባቢዎች የመልሶ ግንባታና የመልሶ ማቋቋም ሥራ እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል። የእድሳት ግንባታ የሚካሄድባቸው ወረዳዎችም ዋጅራት፣ ሰሓርቲ፣ ሓሓይለ፣ ዓዴት፣ ጉለመከዳ፣ ብዘት፣ እገላ፣ ፅምብላ፣ እምባስነይቲ፣ ዛና፣ ማእከል ኣድያቦ፣ ራያ ዓዘቦ፣ ነቅሰገና ኣላጀ መኾናቸው ተጠቁሟል።