የሆስፒታሉ የቀዶ ጥገና ዋርድ በቅርቡ በተገደለው ዶ/ር አንዱአለም ስም እንዲሰየምና ሓውልት እንዲቆምለት ዩኒቨርሲቲው ወሰነ
የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ሴኔት፤ የጥበበ ግዮን ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የቀዶ ጥገና ዋርድ በቅርቡ በተገደለው ዶ/ር አንዱ አለም ስም እንዲሰየምና በሆስፒታሉ ግቢ ሓውልት እንዲቆምለት ወሰነ። በግድያው ላይም ጥልቅ ምርመራ እንዲደረግ እና እጃቸው ያለበት አካላት በአፋጣኝ ለህግ እንዲቀርቡ እንዲደረግ ጠይቋል።
ዩኒቨርቲው ዛሬ ባወጣው መግለጫ፤ የ37 አመቱ ዶ/ር አንዱአለም የቀረቡለትን በርካታ ዓለምአቀፍ የስራ ቅጥር ግብዣዎች ባለመቀበል ወገኑን ለማገልገል ቆርጦ የነበረ ባለሙያ መሆኑን ገልጿል።
ዶ/ር እንዱአለም በጥበበ ግዮን ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ታሪክ “የመጀመሪያውን ቀዶ ጥገና ስራ መስራቱን” የገለጸው ዩኒቨርሲቲው እስከ ህልፈቱ ድረስ ሆስፒታሉ ደረጃውን በጠበቀ መልኩ ለማሳደግ ከፍተኛ ጥረት ሲያደርግ እንደነበርም አስረድቷል።