ስምንተኛው የአፍሪካ ቢዝነስ ፎረም ከአፍሪካ ህብረት ጉባኤ ጎን ለጎን እንደሚካሄድ ተገለጸ
ስምንተኛው የአፍሪካ ቢዝነስ ፎረም ከ38ተኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች መደበኛ ስብስባ ጎን ለጎን በመጪዉ የካቲት 10 በአዲስ አበባ ይካሄዳል ተብሏል።
ፎረሙ " ከአቅም ወደ ብልፅግና ፤ የአፍሪካን ክልላዊ የእሴት ሰንሰለቶች ማንቀሳቀስ"
በሚል መሪ ቃል አዲስ አበባ በሚገኘው የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን አዳራሽ (ኢሲኤ) ውስጥ ይደረጋል።
ፎረሙን የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን፣ የአፍሪካ ፋይናንስ ኮርፖሬሽን እና የአረብ ባንክ ለአፍሪካ የኢኮኖሚ ልማት በትብብር በትብብር ያዘጋጁታል።
ከመንግስት እና ከግል ኢንተርፕራይዞች፣ ከልማት አጋሮች ፣ የሀገር ውስጥ እና አለም አቀፍ አልሚዎች፣ የፋይናንስ ተቋማት እና የማህበረሰብ ድርጅት ተወካዩች በፎረሙ እንደሚሳተፉ የመንግስት ሚዲያ ዘግቧል።