በአዲስ አበባ አንዳንድ የመንግስት አገልግሎቶችን በ3ተኛ ወገን ለማሰራት የሚያስችል ደንብ ፀደቀ
በሶሶተኛ ወገን ለማሰራት የታሰቡት የመንግስት ስራዎች የትኞቹ እንደሆኑ አልተገለፀም።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ 4ተኛ ዓመት 7ተኛ መደበኛ ስብሰባው በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል።
ወሳኔ ከተላለፈባቸው መካከል አንዳንድ የመንግስት አገልግሎቶችን በውል ለ3ተኛ ወገን ለማስራት የወጣውን ረቂቅ ደንብ ካቢኔዉ ያፅደቀበት ይገኝበታል።
በከተማዉ አስተዳደር በጀት ተመድቦላቸዉ የተገነቡ እና በመጠናቀቅ ያሉትን አዳዲስ ሆስፒታሎችን ዘመኑን በዋጀ ህክምና መሳሪያ ለማሟላት እና አለም አቀፍ ደረጃን የሚያሟላ አገልግሎት መስጠት ያስችላቸው ዘንድ በዘርፉ ትልቅ ልምድ ካከበቱ የግል ሴክተር ጋር በአጋርነት ለመስራት ዉሳኔ አሳልፏል።
የተለያዩ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ ላላቸው እና ተኪ ምርቶችን ለሚያመርቱ ኢንዱስትሪዎች ባቀረቡት የማስፋፊያ ቦታ ጥያቄዎች በሙሉ ድምፅ ፅድቋል።
ካቢኔው የኮሪደር ልማት ውጤት ከሆኑት ሥራዎች አንዱ የብዙሀን ትራንስፖርት መሠረተ ልማት ችግሮች የሚያቃልል እና የትራፊክ ፍስቱን የሚያሻሽለው የብስክሌት መጋራት አገልግሎት እና የብስክሌት መስመር አጠቃቀም ደንብንም አፅድቋል።