👉"ከእኛ ክፋት የተነሳ ነው መከራ እየመጣብን ነው በዚህም በሀጥያታችን ፈጣሪያችንን አስቆጥተናል" አቡነ ማቲያስ
👉"ከእኩይ ስራችን መመለስ አለብን ከቃል ባለፈ የሰው ልጅ በሰራው ነው ለሰላም በተግባር ዘብ መቆም ይገባናል"ሐጅ ኢብራሂም
👉"ሰላም ትልቁ ጸጋ ነው " ብፁዕ ካርዲናል
👉"የምንሰብከው ወንጌል የሰላም ነው"ቄስ ደረጀ
በኢትዮጵያ የሲቪል እና የሙያ ማኅበራት ም/ቤት(ኮንግረስ) አዘጋጅነት ልዩ የጸሎት እና የሰላም ጥሪ አገራዊ ጉባኤ የተደረገ ሲሆን በየአቅጣጫው የሚታየው ግጭት እንዲቆም "ሰላም ለሀገራችን፤ ሰላም ለህዝባችን!!" ይሆን ዘንድ የየሃይማኖቱ አባቶች ለኢትዮጵያ ህዝብ የሰላም ጥሪ እና መልእክት በዛሬው እለት አስተላልፈዋል።
📌በመድረኩም ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ፓትርያርክ ሊቀጳጳሳት ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለሀይማኖት ፤ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን በመወከል ባስተላለፉት መልዕክት " ከእኛ ክፋት የተነሳ ነው መከራ እየመጣብን ነው በዚህም በሀጥያታችን ፈጣሪያችንን አስቆጥተናል ያሉ ሲሆን በዚህም እግዚአብሔርን በማሳዘናችን በቀጣይ የካቲት 3 እስከ 5 ድረስ በሚቆየው ጾመ ነነዌ በንሰሀ በመመለስ ከልብ ይቅርታ በመጠየቅ እና ከክፉ ተግባር መታቀብ" እንደሚያሻ መልዕክት አስተላልፈዋል።
📌የክብር ዶክተር ሸይክ ሐጂ ኢብራም ቱፋ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት እና የዑለማዎች ምክር ቤት ሰብሳቢ፤ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት በመወከል ባስተላለፉት መልዕክት " ከእኩይ ስራችን መመለስ አለብን ከቃል ባለፈ የሰው ልጅ በሰራው ነው ለሰላም በተግባር ዘብ መቆም ይገባናል ብለዋል።
📌ብፁዕ ካርዲናል ብርሃነ እየሱስ ሊቀጳጳሳት ዘካቶሊካውያን የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን የጳጳሳት ጉባኤ ፕሬዝዳንት በበኩላቸው ባስተላለፉት መልዕክት
ሰላም ትልቁ ጸጋ ነው የክርስትና እምነት የገባው በሰላም ነው የሚል መልዕክት አስተላልፈዋል።
📌ቄስ ደረጀ ጀምበሩ የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲናት ካውንስል ጠቅላይ ጸሀፊ የምንሰብከው ወንጌል የሰላም ነው ስለዚህ ሰላምን አብዝተን ልንፈልግ እና ልንከታተል ይገባል ብለዋል።
የሀይማኖት አባቶቹ ከሰላም ጥሪ ባለፈ እንደየ እምነታቸው ለፈጣሪያችን ስለ ሰላም በጸሎታቸው ተማጽነዋል።