ምሽቱ ነው ቀኔ
ባይኔ ህሊናዬ ሳይህ በጨለማ፣
ስላለም ባይገባኝ ደረቀ ወይ ለማ፥
ጭንቀቴን ሃዘኔን አዚያ አራግፌ፣
ልቤ ተረጋግቶ ተንፍሼ አርፌ፣
እንደፈራ ሰው ወይ እንደተለከፈ፣
እዚያ በደረትህ እዚያ ተለጥፌ፤
ከሁሉ በተሻለው ከወርቅ ሆነ ከብር፣
ድምፄ ሳይሰማ በድምፄ ስዘምር፣
ቁሳዊው እቅዴ ብሰምር ባይሰምር፣
ያለኑሮ ሂሳብ ያለ ወጪ ድምር፣
ምሽቱ ነው ቀኔ ከቀናት የሚያምር።
ትናፍቀኛለህ ውዴ❤
✍Alazer T.
@gitim_alem
ባይኔ ህሊናዬ ሳይህ በጨለማ፣
ስላለም ባይገባኝ ደረቀ ወይ ለማ፥
ጭንቀቴን ሃዘኔን አዚያ አራግፌ፣
ልቤ ተረጋግቶ ተንፍሼ አርፌ፣
እንደፈራ ሰው ወይ እንደተለከፈ፣
እዚያ በደረትህ እዚያ ተለጥፌ፤
ከሁሉ በተሻለው ከወርቅ ሆነ ከብር፣
ድምፄ ሳይሰማ በድምፄ ስዘምር፣
ቁሳዊው እቅዴ ብሰምር ባይሰምር፣
ያለኑሮ ሂሳብ ያለ ወጪ ድምር፣
ምሽቱ ነው ቀኔ ከቀናት የሚያምር።
ትናፍቀኛለህ ውዴ❤
✍Alazer T.
@gitim_alem