እጣፋንታዬ ላያልፈኝ፣
ከተጻፈልኝ ላልጨምር
እግዜሩ ያዘዘው እንጂ፣
እልቁ ምኞቴ ላይሰምር
አላዛርን ሳይ ላልደኸይ፣
ነዌን ሳስታውስ ላልከብር
ዳዊትን ስሻ ላልነግስ
አሮንን ሳስብ ላልቀድስ
በእሳቱ ሰረገላ ላይ ላልጠልቅ እንደ ኤልያስ
ቅይድ የጠፋው ምኞቴን፣እንደ እንዝርት ጥጥ ባዞረው
ሕይወትን መከተል እንጂ፣ ኑረትን መቼ ልመራው!
ያው እድል ከሸለመችኝ፣
በበትሬ ውሀ እከፍላለሁ
ስምረቴ የዘመመእንደሁ፣
ባህር ውስጥ እቀበራለሁ።
አለምን እገዛም እንደሁ
ለሰልፍም እታደል እንደሁ
በእስክንድር ፈረስ ልቀመጥ
ሰይፈ ጌድዮን ልጨብጥ
ወይ ሰለሞንን ላስንቀው
ወይ ተዋናይን ልልቀው
የአሳቤን አክናፍ ሰብሬ፣
ዛሬ ዛሬን እየኖርሁ
ነገን ለነገው እየተውሁ
የአርባ ቀን ስውር ጽዋየን፣ ልጎነጭ እጠብቃለሁ
አምላክ እንዳሻው ሊያኖረኝ ፣በኔ ጭንቅ ምን አተርፋለሁ?
(ታደሰ ደምሴ)
📱ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!📱
ግጥሜን ለኢየሱስ
💙እወዳቸዋለ💙
---------------------------------------------------------
SHARE
@gitim_alem @gitim_alem
--------------------------------------------------------
SHARE
Contact me @abu_ND8