( ያልጸደቀው ጻድቅ)
ከመስቀሉ ጀርባ
እልፍ አእላፍ ወከባ
ይታየኛል
በጣር ትግል መስቀል ኋላ የሚታትር
የሚታደም ህይወት ከፍሎ ከትያትር
ባልከፈለው ዋጋ ድነት ተከናንቦ
ጀነትን በስራ የሚል ትግል ስቦ
ይታየኛል
ወረድ ብሎ ከዳገቱ
ከጎልጎታ መስቀል ጀርባ
በህግጋት የሚሳፈር
ብኩን ተጓዢ ባለጀልባ
ላይደርስበት መሬት የብሱን
የሚቀዝፍ ውቅያኖሱን።
ይታየኛል
በፈራራሽ በሽክላ ገል
ከብረት ጋር የሚታገል።
ጀርባ ሰጥተው ለመስቀሉ
ለመፅደቄ ደሜ ይፍሰስ ብለው ያሉ
ይታዩኛል ያልገረጡ ወይ ያልሰቡ
ከፅድቅ ደጅ እምነት ይዘው ያልቀረቡ።
ለመኖር ያልኖሩ የታገሉ ለሞት
ከህይወት ሚዛን ላይ አይጭሩም አግራሞት
ክርስቶስን ትቶ ፅድቅ የለም በጥረት
ከመስቀሉ ጀርባ በሚታየው ትርኢት
የፅድቅ መቋጫ የፅድቅ መባቻ
መፍትሔው እምነት ብቻ።
(እንግዳዬሁ ዘሪቱ)
ግጥሜን ለኢየሱስ
💙እወዳቸዋለ💙
---------------------------------------------------------
SHARE
@gitim_alem @gitim_alem
--------------------------------------------------------
SHARE
Contact me @abu_ND8
ከመስቀሉ ጀርባ
እልፍ አእላፍ ወከባ
ይታየኛል
በጣር ትግል መስቀል ኋላ የሚታትር
የሚታደም ህይወት ከፍሎ ከትያትር
ባልከፈለው ዋጋ ድነት ተከናንቦ
ጀነትን በስራ የሚል ትግል ስቦ
ይታየኛል
ወረድ ብሎ ከዳገቱ
ከጎልጎታ መስቀል ጀርባ
በህግጋት የሚሳፈር
ብኩን ተጓዢ ባለጀልባ
ላይደርስበት መሬት የብሱን
የሚቀዝፍ ውቅያኖሱን።
ይታየኛል
በፈራራሽ በሽክላ ገል
ከብረት ጋር የሚታገል።
ጀርባ ሰጥተው ለመስቀሉ
ለመፅደቄ ደሜ ይፍሰስ ብለው ያሉ
ይታዩኛል ያልገረጡ ወይ ያልሰቡ
ከፅድቅ ደጅ እምነት ይዘው ያልቀረቡ።
ለመኖር ያልኖሩ የታገሉ ለሞት
ከህይወት ሚዛን ላይ አይጭሩም አግራሞት
ክርስቶስን ትቶ ፅድቅ የለም በጥረት
ከመስቀሉ ጀርባ በሚታየው ትርኢት
የፅድቅ መቋጫ የፅድቅ መባቻ
መፍትሔው እምነት ብቻ።
(እንግዳዬሁ ዘሪቱ)
ግጥሜን ለኢየሱስ
💙እወዳቸዋለ💙
---------------------------------------------------------
SHARE
@gitim_alem @gitim_alem
--------------------------------------------------------
SHARE
Contact me @abu_ND8