የወንጌል አርበኛው አባባ ዋንዳሮ
ወንጌላዊ ዋንዳሮ ዳባሮ (አባባ ዋንዳሮንታ) ....
ስለ አባባ ዋንዳሮ ታሪክ ከብዙ በጥቅቱ ለማስፈር ሞክርያለሁና ብታነቡትት የወንጌል ሀይል የመንፈስ ቅዱስ እሳት ያገኛችኃል ።
አባባ ዋንዳሮ ከወላይታ ሶዶ ወደ ደቡብ አቅጣጫ 20km ርቀት ያላት ሁምቦ በሚትባል ወረዳ በ1906 ዓ.ም ተወደዋል ።
እንደ አባቱም ጭሰኛ ገበሬ እና ሽማኔ ሥራን ይሰራ ነበር ።
በወጣትነቱም ለሐይማኖታዊ ነገሮች ንቁ ስለነበር ከ 1915-1920 ዓ.ም ደረስም "የነብዩን" እሳ ላሌን ትምህርት ለመተግበር ይሞክር ነበር ። የ"ነብዩም" ትምህርትም "ለሰይጣን የሚያደርጉትን አምልኮ ትተው ለእውነተኛው አምላክ አምልኮን ቢያቀርቡ በደስታ እና ተድላ እርስ በርስ እንደሚኖሩ ያስተምር ነበር።"
ይኼንንም ትምህርት አባባ ዋንዳሮ በልቡ "ለእንጨት ማምለክ እና እንስሳትን መሰዋዕት ማቅረብ ለሰይጣን ስለሆነ መተው አለብኝ" ብሎ አሰበ ።
አንድ ቀን አባባ ዋንዳሮ ወደ ሁምቦ ሲመለስ በግፍ ፊታውራሪ ዶግሶ በሬውን ቀምቶ ነበር ፤ ስለ በሬውም ፊታውራሪውን በሁምቦ ፍርድ ቤት ከሶ'ት ነበርና ነገር ግን ፍትሕ በዛም ተጣመመና አባባ ዋንዳሮም እንዲህም አሉ " እኔ ወደ እግዚአብሔር ብቻ አለቅሳለሁ እኔስ ምንም ማድረግ አልችልም።" ብሎ ተወው። በኋላም ደጀዝማች መኮንን በ1932 ለወላይታ ተሾመ ። አባባ ዋንዳሮም ከአባ ጮራሞም ደጃዝማች መኮንን በእውነት እንደሚፈርድ ሰማ ፤ ከፊታውራሪ በቀለም አረጋገጠ ፤ ነገር ግን አባባ ዋንዶሮ ወደ ሶዶ ሲመጣ ደጃዝማች መኮንን ለአማራ ጦርነት ዘምቶ ነበርና በቦታው ማንም አልነበረም ። አባባ ዋንዳሮ በሐዘኔታ ለእረፍት ወደ ቤታቸው ተመለሱ ።
አባባ ዋንዳሮም ያለውን ብቸኛ ንብረቱን ከማጣቱ የተነሳ ለእርዳታ በኦቶና ያሉ ሚሽኔሪዎችን ፈለገ እና ወዳሉበት ሄደ ፤ ሄዶም ቀያይ ፊቶችንም አይቶ " በርግጥም በነዚህ ሰዎች ውስጥ እግዚአብሔር አለ ፍትህም ይኖራል" አለ ።
አባባ ዋንዳሮም ከጥቅት ሳምንታትን በኋላ እንደገና ተመልሶ ከሁምቦ ወደ ሚኔሪዎች ጣቢያ መጣ ፤ በዛም ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ጠያቃቸው በወቅቱ እነዚህ የአሜሪካ ሚሽኔሪዎች አላማ እርዳታ ብቻ ሳይሆን ወንጌልን ለፍጥረታት መስበክ ነበርና አንድ ጠይቆ የሚሰማ ሰው ማግኘታቸው ደስም አላቸው ። Earl Lewis የሚባል ሚሽኔሪ የወላይታን ባሕላዊ የደም መሰዋዕት ባሕልን በደንብ ስለሚያውቅ "ኢየሱስ ብቻ የዓለምን ኃጢአት የሚያስወግድ የእግዚአብሔር በግ" መሆኑንና ይህ ኢየሱስ ከዚህ ጭንቀት መከራ ሲቃይ እርግማን ጭንጋፋ በነፃ እንደሚያድን በደንብ አድርጎ መሰከረለት አባባ ዋንዳሮም ለሶስተኛ ጊዜ ወንጌልን ስለሚሰማ አመነበት ።
በቀጣይ ሳምንት እሁድ ግን አባባ ዋንዳሮ ወደ ሚሽኔሪዎች ጣቢያ ሲመጣ ከ20 የሚበልጡ ሰዎችን ይዞ መጣ ፤ (ያኔ ኢየሱስ ክርስቶስን አምኖ ወደ ሁምቦ ሲመለስ የ2:00 ሰዓት መንገድ ወንጌልን ስመሰክር 3 ቀን ነበር የፈጀበት ) በጭንጋፋ እና በረሃብ በስቃይና በርግማን የሚሰቃዩ የተገለሉ ወገኖች ልክ እንደሱ በደል የደረሰባቸው ይህንን የሚያሳርፍ ኢየሱስን ለመቀበልና በሱ ምክንያት የሚመጣውን መከራ ለመጋፈጥ ምንም አላመነቱም ።
በጨንቻ ከተማ ያለችሁ የSIM nurse የነበረችሁ ሩት ብረይ እንደ አዲስ በተከፈተው ክሊኒክ ስለኢየሱስ ስትመሰክር ሰዎቹ " ይኼን ሁሉ እኛ እዛ በሁምቦ ገበያ ሰምተናል " ይሏት ነበር፤ ለካ እዛ በገበያ ቦታ የሰበከው አባባ ዋንዳሮ ነበር ። ከጥቅት ወራትም በ ኋላ በኦቶና [ ኦቶና ማለት ሚሽኔሪዎች በወቅቱ ለህክምና እና ለወንጌል አገልግሎት የመሰረቱት ትልቁ ሆስፕታል ነው ከሁሉም ኢትዮጵያ ሰዎች ይጎርፉ ነበር ] በሚደረገው ስብሰባ ከመቶ በላይ ሰዎች እንደተሳተፉ የወቅቱ የSIM ዳይረክተር የሆኑት ዶክተር ቶማስ ላ ምቤ መስክረዋል ።
አባባ ዋንዳሮ በሁምቦ የመኖርያ ቀበሌአቸው የሠሩትን የፕሮቴስታንት ተከታዮች ጎጆ የጸሎት ቤት ከኢትዮጵያ መንግሥታዊና ከኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ጥንታዊ ሐይማኖት ውጭ የሆነውን የሚቃረነውን አዲሰን መጤ እና ጴንጤ እምነት ተከታዮች ጸሎት ቤት ነው የሚባለውን አሠርተዋል ።
ይህንንም እምነት አጋግሎ እያራመደ ነው፤ አባሎቻችንን ሰብኮ ከአንገታቸው ክር እያስበጠሰ አጥምቆ ወደ መጤና ጴንጤ ሃይማኖት እያስገባብን ነው በተዋሕዶ ሐይማኖታችን ላይም ደባ እየፈጸመ ነው፤ ይህ ደበኛ ይቀጣልን፤ ጸሎት ቤት ነው ብሎ የሰራውንም ያፍርስልን ሲሉ በጊዜው በሙሉ ሥልጣን ለነበሩት ፊታውራሪ መጠሎ ዶግሶ አመለከቱ።
ፊታውራሪ ዶግሶም አባባ ዋንዳሮን አስጠርተው አንተና ጭፍሮችህ የምታደርጉትን ደባ ሰምችያለሁ። ከጭፍሮችህ ጋር አብረህ በቤተክርስቲያንነት የሰራኸውን ጎጆ ቤተን በአስቸኳይ አሁኑኑ ጭፍሮችህን ሰብስበህ አፍርሱትና ያፈረሳችሁትን ይዛችሁ ሶዶ ወስዳችሁ ለኦርቶዶክሱ የግዮርጊስ ቤተክርስቲያን የዙርያ አጥር ሥራ እዚያ ለሚገኙት ቀሳውስት አስረክቡ ብለው አዘዙአቸው።
አባባ ዋንዳሮም "እሽ የእግዚአብሔር ፈቃድ ይሁን" ብለው የጸሎት ቤቱን አፍርሰው የቤተክርስቲያኒቱ አባላት ሁሉም ራሳቸው ተሸክመው የሚገርም መዝሙር እየዘመሩ ("ኢ ያና! ዛሩዋካ ኢማና"= እሱ[ኢየሱስ] ይመጣል መልስንም ይሰጣል) የሚለውን መዝሙር እየዘመሩ ከሁምቦ ዶግሶ ወንገላ ከሚባለው ቦታ እስከ ሶዶ ኦርቶዶክስ ግዮርጊስ ቤተክርስቲያን ድረስ ወስደው ለቀሳውስቱ አስረክበው ተመለሱ በደስታ አሁን እየዘመሩ እየፀለዩ እየመሰከሩ ተመለሱ ።
ከዚያም በኋላ አማኞች በግለሰብ ቤት እና በየእንጨት ጥላ ሥር እየተደበቁ እግዚአብሔርን ያመልኩ ነበር። ይኼንንም አቶ ጠቀሮ የተባለ ሰው ለፊታውራሪው ጠቆመ። ፊታውራሪውም አባባ ዋንዳሮን የመጨረሻ ከፍተኛ ቅጣት ለመቅጣት ለአርብ ቀጠረ። ይኼም ቀጠሮ ለአባባ ዋንዳሮ ደረሰው፤ አባባ ዋንዳሮም እንዲህ አሉ ለመልዕክተኛው"ከአርብና ከዶግሶ መኻል እግዚአብሔር አለ!"
አርበም ሲደርስ አባባ ዋንዳሮ በቀጠሮ ቦታ ለመገኘት ስወጡ ብዙ አማኞችም ተከተሉት፤ አባባ ዋንዳሮም አማኞችን እንዲህ አላቸው"የጌታዬን የኢየሱስን አካል ከመቃብር ያስነሳውን ያንን ታላቅ ኃይል ተጠራጥራችሁ ነው ልትከተሉኝ የመጣችሁት?" አሏቸው።( አማኞቹም ምናልባት በሞት ከተቀጣ አስክሬናቸውን ለማምጣት ነው ተመካክረው ነው የተከተሉአቸው።)አማኞችም "አንጠራጠረውም" ብለው መለሱለት።
አባባ ዋንዳሮም "ኢ ያና " "ዶግሶ ከምድር ሲመጣ አምላኬ ከላይ በአየር ቀድሞት ይደርስልኛል" እያሉ ጉዟቸውን ቀጠሉ።