ወደ ቦታውም ሲደርሱ ፊታውራሪ ዶግሶም ገና መድረሳቸውም ነበረና (አባባ ዋንዳሮ ጢሙን ተላጭቶ በሆድና በጀርባው አርባ አርባ እንዲገረፍ ወስነው ነበር) ፊታውራሪውም በሉ ያንን ደበኛ ያዙት ብለው ወደ ዋንዳሮ በርቀት እያመላከቱ ሳለ ይቀመጡበት ዘንድ ባርጩማ አቀረቡላቸውና ወፍረምም ሰው ስለነበሩ ገና ከወገባቸው ዝቅ ሲያደርጉ ሆዳቸው ፈንድቶ አንጀታቸው ተዘርግፎ እዚያው ሞቱ። እቀጣለሁ ያለው በእግዚአብሔር እጅ ተቀጣ። አባባ ዋንዳሮን ሊያስገርፉት የቆሙ ፊታውራሪ ዶግሶ የራሳቸው ቀብር ተፈጸመ።
በጣሊያን ወረራ ወቅት ከወንጌል ስብከት ጋር በተያያዘ ከወላይታ አከባቢ ከተለቃቀሙ ወንጌላዊያን ጋር አባባ ዋንዳሮም በሶዶ ሸክላ ወኅኒ ቤት ታስረው ነበር ።በዛም ቦታ ሁሉም በአንድ ቦታ መሰብሰባቸው ለጋራ መዝሙርና ጸሎት ተመቻቸው። አባባ ዋንዳሮንም ይኼን ሁሉ የሚታደርገው አንተ ነህ ብለው ለይተው ጢማቸውን እየነጩት አርፌህ ትቀመጣለህ ወይስ ትገደላለህ? ይሉት ነበር ።
አባባ ዋንዳሮም ስቃያቸው በበዛበት ደቂቃ ላይ ያመንሁበት ጌታዬ ኢየሱስ አሁን ይመጣልኛል ብለው ሲያበቁ ፍም የሚመስል እሳት ከሰማይ እየታየ መጥቶ በወህኒ ቤት አናት ላይ ወረደ። በዚያው ላይ ሀይለኛ አውሎ ነፋስን ተቀላቅሎ ይመጣበትና የሸክላው ወህኒ ቤት በእሳት ተቀጣጠለ። ድብልቅልቅ ወጥቶ መነዋወጥ ሆነና የዚህ ሰውዬ ጦስ ያስፈጀናልኮ ብለው ፈተው ለቀቁት።
አንድ ቅዳሜም ከታላቅ ሴት ልጃቸው(ሞልሴ) ጋር በአንድ ቤተክርስቲያን የጌታ እራትን ለመስጠት ሲሄዱ መንገድ ላይ መሸባቸው፤ ነገር ግን የግድ እዛው ቤተክርስቲያን ደርሰው ለነገው የጌታ እራት መጸለይ ነበረባቸው። በመሃል ግን በጨለማው እየተረመዱ ከሁለት እግረቸው መሃል መብራት በራና መንገዱን ያሳያቸው ጀመረ ። እየሄዱ እያሉም ሽፍታዎች ከፊት ለፊታቸው ሲመጡ ከመንገዱ ገሸሽ ብለው ወደ ዛፍ ውስጥ ገቡ ያንጊዜ መብራቱ ጠፋ፤ ሽፍታዎቹ ካለፉ በኋላ መንገዳቸውን ሲቀጥሉ መብራቱ እንደገና በራ እና እስከ ቤተክርስቲያን ግቢ ድረስም ሸኛቸው።
አባባ ዋንዳሮ በብዙ ፕሮግራሞች ላይ ደም እየፈሰሰባቸው ያገለገሉ እንደነበር ታርካቸው ያወራል።
ዕብራውያን 12 (Hebrews)
1-2፤ እንግዲህ እነዚህን የሚያህሉ ምስክሮች እንደ ደመና በዙሪያችን ካሉልን፥ እኛ ደግሞ ሸክምን ሁሉ ቶሎም የሚከበንን ኃጢአት አስወግደን፥ የእምነታችንንም ራስና ፈጻሚውን ኢየሱስን ተመልክተን፥ በፊታችን ያለውን ሩጫ በትዕግሥት እንሩጥ፤ እርሱ ነውርን ንቆ በፊቱም ስላለው ደስታ በመስቀል ታግሦ በእግዚአብሔር ዙፋን ቀኝ ተቀምጦአልና።
ይህ የወንጌል አርበኛው የአባባ ወንዳሮ ታርክ ነው
ተወዳችኋል🥰
---------------------------------------------------------
SHARE
| @GITIM_ALEM |
| @GITIM_ALEM |
--------------------------------------------------------
SHARE
Contact me @abu_ND8