ተከታታይ መንፈሳዊ ልብወለድ
#ሁለት_ሰይፍ
ክፍል አራት (ሜርሲ✍️)
ናትናኤል የእራሴ የሚላቸውን ዕቃዎች በስርአት ከሰደረ በኋላ ከበሩ ጋር ሆኖ ቤቱን ይመለከታል::
"ናትናኤል::" ወደ ውጭ ይወጣል::ሳራ ሙሉ ቱታ ለብሳ በእጇ የመኪና ቁልፍ አንጠልጥላ ከእሱ እራቅ ብላ ቆማለች::
"ቤቱ አማረልህ?"
ፈገግ ብሎ:-
"ቀድሞም ያማረ ቤት ላይ እኮ ነው የገባሁት::"
እሷም ፈገግ ትል እና:-
"ቆንጆ ቆይታ እንዲኖርህ ነው የምመኘው::እምም... የሚያስቸግርህ ወይም የምትፈልገው ነገር ካለ ደውልልኝ::ማክቤልን ከክላስ የማመጣበት ሰዓት ደርሷል::"
"እሺ.." ፊቷን አዙራ ወደ በሩ ትሄዳለች::
"ሳራ.."
ቆም ብላ ትዞራለች::
"ስልክሽን አልሰጠሽኝም::"
"ኦውው.. ያ... ያዘው::"
ቁጥሯን ተቀብሏት ስትወጣ በዓይኑ ሸኝቷት ወደ ቤቱ ሲገባ እጁ ላይ የያዘው ስልክ ይጠራል::አቤነዘር መሆኑን ሲያይ ተቻኩሎ በማንሳት ወደ ጆሮው ያደርጋል::
"እንዴት ነው አዲሱ ቤትህ... እየተለመደ ነው::"
"ይለመዳል ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ::" ከሶፋው ተቀምጦ ከአጠገቡ ሪሞቱን በማንሳት ከፊቱ ስታንዱ ላይ ያለውን ቲቪ ይከፍታል::
"ምን አሉህ?... ቅድም እኮ አልተደማመጥንም::"
"እምም... እንግዶችህ ጋር ነበርክ::እንደጠበቅኩት ነው::አላሳመንኳቸውም::"
"የምር.."
"ይሃ.... አባዬ በተለይ..."
"አንድ ልጃቸው እኮ ነህ::"
"ይገባኛል አቤኒ::ግን አንዳንዴ ውስጥህ የሚነግርህን ማዳመጥ አለብህ::"
"ልክ ነህ::ለልብህ የሚነግርህን መንፈስ ቅዱስ ማዳመጥ አለብህ::"
"መንፈስ ቅዱስ..."
"አዎ.. ምነው..."
"አይ ምንም...."
"ዛሬ የወጣቶች ፕሮግራም አለ::አስራ አንድ ሰዓት ለምን ብቅ አትልም::"
"ኦውው.. አቤኒ... በዛ ሰዓት ኦንላይን የምሰራው ሥራ አለኝ::በኋላ እንደዋወል በቃ::"
እያቅማማ:-"እሺ እንዳልክ::ደሕና ሁን::"
"ባይ.."ስልኩን ዘግቶ ከጎኖ በማስቀመጥ ወደ ቲቪው እየተመለከተ በእረጅሙ ተነፈሰ::
"ግራ የገባሽ ዓለም..."
* * *
ሳራ መገናኛ ከሚገኘው ከሰፊው ዳቦ እና ኬክ መጋገሪያ እና መሸጫቸው ላይ ተሰይማ ከውስጥ ከሚሰራው ጀምሮ እስከ መሸጫው ድረስ ጥራታቸውን ሁኔታውን ካየች በኋላ ማኔጀሩ የቀን የሽያጭ ሁኔታውን ካብራራላላት በኋላ የሚያደርገውን አዛው ከእሱ ከተለያየች በኋላ ተሰናብታቸው በመውጣት ከመኪናዋ በመግባት ሰሚት ወዳለው ሌላኛው ቅርንጫፍ ታመራለች::
* * *
ናትናኤል ከበሩ ሲወጣ ማክቤል ከበረንዳው ጫፍ ላይ ተቀምጦ ኳሱን በእጁ እያመላለሰ ከበሩ ላይ ዓይኑን ተክሎ ሲያገኘው እሱም የዓይኑን አቅጣጫ ተከትሎ ወደ በሩ ይመለከታል::
ምንም የሚታይ ነገር ሲያጣ ዓይኑን ወደ ማክቤል ይመልሳል::
"ደሕና ነህ ማክቤል... ማክቤል.."
ማክቤል ደንገጥ ብሎ ይመለከተዋል::
"ደሕና ነህ..."
"አዎ..."
"እምም... ኳስ አብረን መጫወት እንችላለን::"
የማክቤል ፊት ይፈካል::
"እንዴ ትጫወታለህ::" ኳሱን እንደያዘ ይነሳል::
ናትናኤል ወደ መሃል እየሄደ:-
"ኩመካ ላይ እንዴት ነህ?"
"ማንም አይችለኝም::"
ናትናኤል እየሳቀ:-
"ታዲያ እኔ ልሞክርሃ::" እየተጫወቱ እያለ ሳራ ስትገባ ማክቤል የመታው ኳስ ከፊቷ ሲያርፍ ፊቷን ይዛ ዝቅ ትላለች::ማክቤል እና ናትናኤል በድንጋጤ ይመለከቷታል::
"ሳ... ደሕና ነሽ.." ቀና ብላ ትመለከተዋለች::
"ማክ አሁን ግባ::" ትላለች በተቆጣ ድምፀት::ማክቤል ፊቱን አዙሮ ወደ ውስጥ ይገባል::
"ደሕና ነሽ.."
"አዎ... አስቸገረህ አይደል?" ጉንቿን እያሻሸች::
"አይ እኔ ነኝ እንጫወት ያልኩት::"
ፊቷን አዙራ ትልቁን በር በመክፈት ከውጭ የቆመውን መኪናዋን ወደ ግቢ ታስገባ እና መልሳ ስትቆልፍ ወደ በሩ ጋር ይመለከታታል::ከመኪናው ነጭ ኬክ እና ዳቦ የያዘ ሁለት ፔስታል ይዛ በመውረድ ወደ እሱ ቀረብ ብላ አንዱን ፔስታል እያቃበለችው:-
"እስኪ ይሄን ቅመሰው::"
እየተቀበላት:-
"ኦውው... አመሰግናለሁ::"
"እናቴ እያለች ተከራዮችዋን የመጀመሪያ ቀን ቡና አፍልታ ኦልሞስት ደግሳ ነበር የምትቀበለው::ትንሽ ቢዚ ሆንኩኝ::"
"ዚ ስምን ኤሎት::አመሰግናለሁ በጣም::"
"ደሕና እደር::"
"ደሕና እደሪ::"
ገብቶ በሩን ከኋላው በመዝጋት አንድ ሶፍት ያወጣ እና ከፔስታሉ ውስጥ አንድ ተቆራሽ አንስቶ አንዴ ሲገምጠው አይኑ ይፈካል::
"ኦ ማይ ጋድ.. ይሄ ይለያል::" ድጋሚ ይገምጠዋል::
* * *
ስልኩ ሲጠራ ብድግ ይላል::ላፕቶፑ እንደተከፈተ ከጠረጴዛው ላይ ተቀምጧል::
"አምላኬ::መቼ ነው እንቅልፍ የወሰደኝ::"ቀና ብሎ የግድጊዳውን ሰዓት ሲመለከት ለሰባት ይቆጥራል::
"ማነው በዚህ ለሊት.." እግሩን ከሶፋው ላይ በማውረድ ስልኩን ከጠረጴዛው ላይ አንስቶ ደዋዩን ሲመለከት ደንገጥ ይላል ካቅማማ በኋላ አንስቶ ጆሮው ላይ ያደርጋል::
"ሱዚያና..."
"ይቅርታ የኔ ውድ ከመሸ ደወልኩብህ.... የሆነ ነገር ተፈጥሮ::"
"እባክሽን..."
"ይገባኛል... ብዙ እንደተጎዳህ... ግን አንዴ ብቻ ስማኝ.."
በእረጅሙ ይተነፍስና:-
"ምንድነው እሺ..."
Like🥰 Comment📩 Share💫
ቀጣዩ እንድለቀቅ
ይቀጥላል...
ግጥሜን ለኢየሱስ
💙እወዳችኋለሁ 💙
---------------------------------------------------------
SHARE
| @GITIM_ALEM |
| @GITIM_ALEM |
--------------------------------------------------------
SHARE
Contact me @abu_ND8