እንዳልገኝ ተኝቼ
የመምጣትህን ዳግመኛ ተስፋ
እየጠበቅኩኝ ይሄው ቀናቱ ተገፋ
ልቤም ተዘናግቶ ይሄው እየከፋ
ቃልህን እረስቶ ስምህን አክፋፋ
ጠብቅ ባልከኝ ቦታ ድካሜ በዛና
በመጠበቂያዬ ሆኜ ረክሼ አለሁና
የማንቂያውን ደወል የመምጣትህን ወሬ
በእንቅልፌ ሲሰማ እንዳልቀር ከስሬ
በትጋት ነው እንጅ አንተን መጠበቁ
ከድካምና እንቅልፍ ዘወትር እየነቁ
ጠላትን ሊዋጉ ለጽድቅ ሲታጠቁ
ዳግም ምጻትህን ለተ'ቀን እያወቁ
እኔ ደካማ ነኝ በእጅጉ ሰነፍ
የተናገርከኝን ቃሎችን የማጥፍ
መጠበቅያዬ ቦታን የማደርግ ለእንቅልፍ
ሲበዛ ደካማ ለጽድቅ የማልሰለፍ
አደራ ጌታ ሆይ ይህን ቃሌን አደራ
ከቤት ውስጥ ሆኜ እንዳልሆን ክስራ
አንተ በምትመጣበት ቀን ፊትህን ፈርቼ
ከውጭ እንዳልቀር እንዳልገኝ ተኝቼ
ጠብቅ ካልከኝ ቦታ
እርቄ የማታ የማታ
ዳግም ስትመጣ
ስዖል አይሆን የኔ እጣ
Guys እንንቃ የምር🥰
✍️Amanuel Negash(abu)
ግጥሜን ለኢየሱስ
💙እወዳችኋለሁ 💙
---------------------------------------------------------
SHARE
| @GITIM_ALEM |
| @GITIM_ALEM |
--------------------------------------------------------
SHARE
Contact me @abu_ND8
የመምጣትህን ዳግመኛ ተስፋ
እየጠበቅኩኝ ይሄው ቀናቱ ተገፋ
ልቤም ተዘናግቶ ይሄው እየከፋ
ቃልህን እረስቶ ስምህን አክፋፋ
ጠብቅ ባልከኝ ቦታ ድካሜ በዛና
በመጠበቂያዬ ሆኜ ረክሼ አለሁና
የማንቂያውን ደወል የመምጣትህን ወሬ
በእንቅልፌ ሲሰማ እንዳልቀር ከስሬ
በትጋት ነው እንጅ አንተን መጠበቁ
ከድካምና እንቅልፍ ዘወትር እየነቁ
ጠላትን ሊዋጉ ለጽድቅ ሲታጠቁ
ዳግም ምጻትህን ለተ'ቀን እያወቁ
እኔ ደካማ ነኝ በእጅጉ ሰነፍ
የተናገርከኝን ቃሎችን የማጥፍ
መጠበቅያዬ ቦታን የማደርግ ለእንቅልፍ
ሲበዛ ደካማ ለጽድቅ የማልሰለፍ
አደራ ጌታ ሆይ ይህን ቃሌን አደራ
ከቤት ውስጥ ሆኜ እንዳልሆን ክስራ
አንተ በምትመጣበት ቀን ፊትህን ፈርቼ
ከውጭ እንዳልቀር እንዳልገኝ ተኝቼ
ጠብቅ ካልከኝ ቦታ
እርቄ የማታ የማታ
ዳግም ስትመጣ
ስዖል አይሆን የኔ እጣ
Guys እንንቃ የምር🥰
✍️Amanuel Negash(abu)
ግጥሜን ለኢየሱስ
💙እወዳችኋለሁ 💙
---------------------------------------------------------
SHARE
| @GITIM_ALEM |
| @GITIM_ALEM |
--------------------------------------------------------
SHARE
Contact me @abu_ND8