ከሙሴ መና ትበልጣለህ
አባቶቻችን በልተው መናን ምድረ በዳ
አንተን ሳያገኙ ካንተ እንደ እዳ
አንተ የሌለህበትን መብልና ሙሃ
ሁሉም ሰው በላና ቀረ በበረሃ
መቼ ግን ገባቸው አንተ እንደምትበልጥ
ከሰጠሃቸው ነገር ከመብል እና መጠጥ
መብሉን ተውና እሱን ግን እውቁ
ብሎ ብመክራቸውም ባርያህን ግን ናቁ
ለ'ተቀን ህልማቸው መብሉ ሆነና
አንተን ግን ቀየሩ ባበላሃቸው መና
የሚረዱት አንተን በምግቡ ሆነና
ሁሉም እዛዉ ቀረ በተስፋው ገዳና
የኔም ሲጋት ያለው እዚህ ጋር ነው ኣባ
እንዳልሆን ደካማ ፍቅርህ የማይገባ
እንደበሉት በመና አንተን እንዳጠበቡ
እነም እንዳልለካህ በቁስ እጄ በምገቡ
አንተ መች ትለካለህ ለኔ በምትሰጠው
በሀብትና ገንዘብ ከቤቴ ውስጥ ካለው
ከፍትፍትህ ፊትህን እንዳውቅ አስቀድሜ
እርዳኝ እልሃለሁ አልችልም በአቅሜ
✍️Amanuel Negash(abu)
ግጥሜን ለኢየሱስ
💙እወዳችኋለሁ 💙
---------------------------------------------------------
SHARE
| @GITIM_ALEM |
| @GITIM_ALEM |
--------------------------------------------------------
SHARE
Contact me @abu_ND8