የወደድከኝ ሰሞን!
፡
ከቤቴ ደጃፍ ላይ
ሲመላለስ አይተው የታዘቡት ሁሉ
'የፍቅር ደብዳቤ
በልጁ አስይዞ ልኮ ነበር አሉ'
፡
እርሱ ግን!
ዘወትር ተመላልሶ ፥ ባያገኘኝ ላፍታ
ተስፈኛዋ ልቡ ፥ አጥታኝ ብትሄድ ለፍታ
፡
ሰነባብቼ ግን
ከበሬ በስተ ሥር ፥ የታየኝ ወረቀት
እኔን ለማፍቀርህ ፥ የሄድክበት 'ርቀት
ምን ያህል እንደሆን ፥ በቅጡ ያስረዳል
የእውነት መውደድህ ፥ እንዲሁ ይወደዳል፤
፡
እንዲህ ተገረምኩኝ!
በደም የከተብከው ፥ የመዳፍህ ጽሕፈት
እርማት ማያሻው ፥ ያልታየበት ግድፈት
የተጠቀምከው ቃል ፥ ብዛት ያላወቀው
አንድ እሱኑ ነው ፥ ይህ ነው ሚደንቀው
፡
እናልህ ወዳጄ...
'ላስብበት' ብዬህ ፥ እንዳትቆም ከደጄ
እንደ ትላንትናው ፥ ላላመላልስህ
አንድ እድል ብትሰጠኝ ፥ እንዴት ልከልስህ ?
:
የእኔንስ ደብዳቤ ፥ በማን ልላክልህ
ማነው አንተን ደራሽ ፥ የሚያካልልህ ?
ግጥሜን ለኢየሱስ
💙እወዳችኋለሁ 💙
---------------------------------------------------------
SHARE
| @GITIM_ALEM |
| @GITIM_ALEM |
--------------------------------------------------------
SHARE
Contact me @abu_ND8
፡
ከቤቴ ደጃፍ ላይ
ሲመላለስ አይተው የታዘቡት ሁሉ
'የፍቅር ደብዳቤ
በልጁ አስይዞ ልኮ ነበር አሉ'
፡
እርሱ ግን!
ዘወትር ተመላልሶ ፥ ባያገኘኝ ላፍታ
ተስፈኛዋ ልቡ ፥ አጥታኝ ብትሄድ ለፍታ
፡
ሰነባብቼ ግን
ከበሬ በስተ ሥር ፥ የታየኝ ወረቀት
እኔን ለማፍቀርህ ፥ የሄድክበት 'ርቀት
ምን ያህል እንደሆን ፥ በቅጡ ያስረዳል
የእውነት መውደድህ ፥ እንዲሁ ይወደዳል፤
፡
እንዲህ ተገረምኩኝ!
በደም የከተብከው ፥ የመዳፍህ ጽሕፈት
እርማት ማያሻው ፥ ያልታየበት ግድፈት
የተጠቀምከው ቃል ፥ ብዛት ያላወቀው
አንድ እሱኑ ነው ፥ ይህ ነው ሚደንቀው
፡
እናልህ ወዳጄ...
'ላስብበት' ብዬህ ፥ እንዳትቆም ከደጄ
እንደ ትላንትናው ፥ ላላመላልስህ
አንድ እድል ብትሰጠኝ ፥ እንዴት ልከልስህ ?
:
የእኔንስ ደብዳቤ ፥ በማን ልላክልህ
ማነው አንተን ደራሽ ፥ የሚያካልልህ ?
ግጥሜን ለኢየሱስ
💙እወዳችኋለሁ 💙
---------------------------------------------------------
SHARE
| @GITIM_ALEM |
| @GITIM_ALEM |
--------------------------------------------------------
SHARE
Contact me @abu_ND8