◾️
ደም በነካው ልብስ መስገድ〰〰〰〰〰〰〰〰〰〰
➡️
ኢብኑ ባዝ አላህ ይዘንላቸውና ልብሱ ላይ ትንሽ ደም እያለበት የሚሰግድ ሰው ሶላቱ ይበላሻልን? ተብለው ተጠይቀው እንዲህ ብለው መለሱ።✅ ደሙ ትንሽ ከሆነ (ችግር የለውም) ይቅር ይባላል። ነገር ግን ደሙ በተለምዶ ብዙ ነው የሚበል አይነት ከሆነ ይህ ይቅር አይባልም። በልብሱ ወይም በሰውነት አካሉ ብዙ ደሞ እንዳለ እያወቀ የሰገደ ሰው ሶላቱ ትክክል አይሆንም። ነገር ግን ደሙ ጥቂት ከሆነ ይቅር ይባላል። አንድ ሰው ብዙ ደም እንዳለበት ቢረሳ ወይም ሳያውቅ ቢሰግድና ከጨረሰ በኋላ ቢያውቅ ወይም ቢያስታውስ ሶላቱ ችግር የለውም ትክክል ነው። ክል እንደዚሁ አንድ ሰው ሽንት ይመስል የሆነ ነጃሳ በልብሱ ወይም በከፊል የሰውነት አካሉ ላይ እያለ ቢሰግድና ከሰገደ በኋላ ቢያስታውስ ሶላቱ ትክክል ነው።
http://www.binbaz.org.sa/noor/5715