✍
መሃከለኛው ከፍታ……… "አል_አዕራፍ"
ስለ አዕራፍ ምን አሳወቀህ??!!
በጥልቅ ምኞት እና በአስጨናቂ ስጋት መሃል ሰፋሪዎች መንፈሳቸው የሚወጠርበት መሃከለኛው ከፍታ ቦታ ነው።
"አዕራፍ" ይባላል፦
በጀነት እና በጀሃነም መሃል የሚገኝ ከፍታ ቦታ ነው። እዚህ ቦታ ላይ የሚሆን ሰው በቦታው ከፍታ ምክንያት የጀነት ሰዎች ያሉበት ፀጋም ይሁን የጀሀነም ሰዎች ያሉበት ስቃይ ያላንዳች መቸጋገር አንገቱን በማዟዟር ብቻ መመልከት ይችላል።
በመሆኑም………
ወደ ጀነት ሰዎች በተመለከተ ጊዜ ልቡ ጥልቅ በሆነ ምኞት ሲዋልል: ወደ ጀሀነም ሰዎች በሚመለከት ጊዜ ሁለመናው አስጨናቂ በሆነ ስጋት ይናወጣል።
አዕራፍ ላይ የሚቀመጡ ሰዎች እነማን ናቸው??………
ለዚህ ጥያቄ መልስ ለመስጠት የዲን ምሁራኖች እና የቁርኣን ተንታኞች ብዙ ዐይነት ነጥቦች የጠቀሱ ቢሆንም: ግልፅ ከሆነው የቁርኣን አንቀፅ እና ከሰሓባዎች ገለፃ ጋ የሚገጥመው;
እነዚህ ሰዎች ዱንያ ላይ የሰሩት መልካም ስራ እና የተዳፈሩት ወንጀል እኩኩል ሆኖ: ወደ ጀነትም ይሁን ወደ ጀሀነም መግባት ያልቻሉ ሰዎች ናቸው።
ጀነት እንዳይገቡ የሰበሰቡት ወንጀላቸው ሲያግዳቸው፤ ወደ ጀሀነም እንዳይወረወሩ ያስቀደሙት መልካም ስራቸው ይከላከልላቸዋል።
የቁርኣን ተርጓሚ እና ከሊቅ ሰሓባዎች ውስጥ አንዱ የሆነው ዐብዱላህ ኢብኑ መስዑድ ስለ አዕራፍ ሰዎች ሲናገር፦
"መልካም ስራው እና መጥፎ ስራው እኩኩል የሆነበት ሰው ከአዕራፍ ሰዎች ጋ ይሆናል። መሃል ላይ ይቆሙና የጀነት ሰዎች ሁኔታ እና የጀሀነም ሰዎች ሁኔታ ይመለከታሉ። ወደ ጀነት ሰዎች በተመለከቱ ጊዜ "የአላህ ሰላም በእናንተ ላይ ይሁን" ብለው ይጣሯቸዋል፤ ፊታቸው ወደ ጀሀነም ሰዎች ባዞሩ ጊዜ ደግሞ "ጌታችን ሆይ ከበደለኛ ሰዎች ጋ አታድርገን" ብለው ይፀልያሉ።
የመልካም ስራ ባለቤቶች ከፊት_ለፊታቸው እና ከበስተ_ኃላቸው የሚያበራላቸው ብርኃን ይሰጣቸዋል። በዚህ ቀን ለሁሉም ሰው የየራሱ ብርኃን ይሰጠዋል። ልክ ወደ ሲራጥ እንደ ደረሱ አላህ ከሙናፊቆች ላይ ብርኃናቸው ያጠፋባቸዋል: የጀነት ሰዎች ለሙናፊቆች የገጠማቸውን በተመለከቱ ጊዜ "ጌታችን ሆይ ብርኃናችን አዝልቅልን" ብለው ይለምናሉ።
የአዕራፍ ሰዎች ግን ብርኃናቸው አይወሰድባቸውም: ባይሆን እጃቸው ላይ ያለውን ብርኃን እንዲዘልቅላቸው ከጅለው ይቆያሉ፤ በመጨረሻም የጀነት ሰዎች ጀነትን ገብተው ከጨረሱ በኋላ እነዚህ የአዕራፍ ሰዎችም አላህ ጀነት ያስገባቸዋል።"
አላህ በተከበረው ቃሉ የእነዚህ ሰዎች ሁኔታ በማላቅ በቦታው ስም የተሰየመ አንድ ትልቅ የቁርኣን ምዕራፍ ካወረደ በኋላ: የጀነት ሰዎች ፀጋ እና የጀሀነም ሰዎች መከራ በከፊሉ ይጠቅስና: በሁለቱ መሃል ስለ ሚደረገው የጀሀነም ሰዎች የሚያስቆጭ ቃለ ምልልስ ይነግረንና ስለነዚህ ሰዎች ጠቅለል ባለ መልኩ እንደ ሚከተለው ያወሳልናል፦
📖{وَبَيْنَهُمَا حِجَابٌ وَعَلَى الْأَعْرَافِ رِجَالٌ يَعْرِفُونَ كُلًّا بِسِيمَاهُمْ وَنَادَوْا أَصْحَابَ الْجَنَّةِ أَن سَلَامٌ عَلَيْكُمْ لَمْ يَدْخُلُوهَا وَهُمْ يَطْمَعُونَ}
{በመካከላቸውም ግርዶሽ አለ፡ በአዕራፍም ላይ ሁሉንም በምልክታቸው የሚያውቋቸው ሰዎች አሉ፡፡ የጀነትንም ሰዎች ሰላም ለእናንተ ይሁን በማለት ይጣራሉ፡፡ እነርሱም (የአዕራፍ ሰዎች) የሚከጅሉ ሲሆኑ ገና አልገቧትም፡፡} [⁴⁶]
{وَإِذَا صُرِفَتْ أَبْصَٰرُهُمْ تِلْقَآءَ أَصْحَٰبِ ٱلنَّارِ قَالُوا۟ رَبَّنَا لَا تَجْعَلْنَا مَعَ ٱلْقَوْمِ ٱلظَّٰلِمِينَ}
{ዐይኖቻቸው ወደ እሳት ሰዎች አቅጣጫ በተዞሩ ጊዜ; "ጌታችን ሆይ! ከበደለኞች ጋር አታድርገን" ይላሉ፡፡} [⁴⁷]
{وَنَادَىٰٓ أَصْحَٰبُ ٱلْأَعْرَافِ رِجَالًۭا يَعْرِفُونَهُم بِسِيمَىٰهُمْ قَالُوا۟ مَآ أَغْنَىٰ عَنكُمْ جَمْعُكُمْ وَمَا كُنتُمْ تَسْتَكْبِرُونَ}
{የአዕራፍ ሰዎችም በምልክታቸው የሚያውቋቸውን ሰዎች ይጣራሉ፡፡ "ስብስባችሁና በብዛታችሁ የምትኮሩ መሆናችሁ ከእናንተ ምንም አልጠቀማችሁ" ይሏቸዋል፡፡} [⁴⁸]
{أَهَٰٓؤُلَآءِ ٱلَّذِينَ أَقْسَمْتُمْ لَا يَنَالُهُمُ ٱللَّهُ بِرَحْمَةٍ ۚ ٱدْخُلُوا۟ ٱلْجَنَّةَ لَا خَوْفٌ عَلَيْكُمْ وَلَآ أَنتُمْ تَحْزَنُونَ}
{እነዚያ አላህ በችሮታው አያገኛቸውም ብላችሁ የማላችሁት (ደካሞች) እነዚህ ናቸውን? "ጀነትን ግቡ ፍርሃት የለባችሁም እናንተም አታዝኑም" (ተባሉ ይሏቸዋል)፡፡} [49]
የጀነት ሰዎች ጀነት, የእሳት ሰዎች ጀሀነም ከገቡ በኋላ መሃላቸው ላይ ግርዶሽ ይደረጋል። የግርዶሹ በጀሀነም በኩል ያለው ስቃይ ሲሆን በጀነት በኩል ያለው ፀጋ እና ደስታ ነው። ከዚህ ግርዶሽ ከፍታ ቦታው ላይ "አዕራፍ" ተብሎ በተሰየመው ቦታ ላይ ነው እነዚህ አጅራቸው እና ወንጀላቸው እኩል የሆነባቸው ሰዎች የሚቀመጡት። ወደ ጀሀነም ሲያየዩ ፈርተው በአላህ እየተጠበቁ፤ ወደ ጀነት በሚዞሩ ጊዜ ደግሞ ከጅለው አላህን ሲማፀኑ ይቆዩና በመጨረሻም በአላህ ቱሩፋት ማረፊያቸው ጀነት ትሆናለች።
ከዚህ ዳሰሳ ሁለት ዋና ዋና ትምህርቶች እናገኛለን:
1ኛው, ከወንጀል መራቅ ካልተቻለም መቀነስ!!
እነዚህ ሰዎች የሰበሰቡት ወንጀል ካስቀደሙት መልካም ስራ ጋ እኩል በሆነ ጊዜ ጀሀነም ከመግባት ተርፈው ቢያንስ መሃል ላይ ለመስፈር በቁ። እንደው ከሰሩት ወንጀል ላይ ሌላ ተጨማሪ አንዲት ወንጀል ብቻ ጨምረው የሰሩ ቢሆን ኖሮ የወንጀል ሚዛናቸው ከብዶ ወደ እሳት ከመወርወር የሚያስጥላቸው አልነበረም።
ስለሆነም…………
ይህንን የተገነዘበ ሁሉ በተቻለው ልክ ከወንጀል ሊርቅ ግድ ይለዋል።
2ኛው, መልካም ስራን ማብዛት እና አሳንሶ አለማየት!!
አዕራፍ ላይ መሃል ሰፍረው የሚቆዩ ሰዎች ወደ ጀነት ለመግባት የሚቀራቸው አንዲት መልካም ስራ ብቻ ነበረች። ከኢስቲግፋር፣ ከሰደቃ፣ ከሰላት፣ ከቁርኣን፣ ከዱዓ፣፣፣፣ አንዲት ብቻ ተጨማሪ መልካም ስራ የሰሩ (የጨመሩ) ቢሆን ኖሮ ወደ ጀነት ገብተው ደስታቸውን ሀሴት ሊያደርጉ እንጂ ጀነትን ከቅርብ ርቀት እያዯት መግባት ተስኗቸው አይቁለጨለጩም ነበር።
ስለሆነም……………
አላህ በየትኛው ስራህ ሚዛንህ ደፍቶልህ ጀነት እንደሚለግስህ አታውቅምና ባገኘኸው አጋጣሚ: በቻልከው ልክ መልካም ስራ ለመስራት ለማብዛት ታገል እንጂ በፍፁም "እቺ ምን አላት?" ብለህ እንዳታሳልፍ።
🖊አቡ ሙSሊM ሐምዱ ቋንጤ
ከፋርቃን ሰማይ ስር!!
https://t.me/hamdquante