✍
ድብርት, ደስታ እና አዘኔታ ተፈራረቁብኝ!!
ወፍራም ድምፅ ባለው ስፒከር የተከፈተው ሙዚቃ አጠገብህ ካለው ሰው ጋ እንኳ መደማመጥ አያስችልም፤ የምሽቱ አየር እና የመንገድ ክፍት መሆኑ ተመችቶት ታክሲው እያሽከረከረ ሳይሆን እያዘለለ የሚነዳው ነው የሚመስለው። መጨረሻችን ለመድረስ ቢያንስ ከጉዞው አንድ ሦሥተኛው ያህል ሲቀረን ጋቢና ተቀምጠው ከነበሩት አንደኛው መውረጃው ደርሶ ወረደ።
ወደ ታክሲው የገባው የመጨረሻው ሰው እኔ ነበርኩኝ፤ መቀመጫዎቹ ሁሉ ሞልተው ስለ ነበር ለትርፍ በተዘጋጀው ጣውላ ጫፍ ላይ ነበር የተቀመጥኩት። ስለነበርም ጋቢና የነበረው ተሳፋሪ ሲወርድ ረዳቱ ጋቢና እንድገባ ጋበዘኝ።
ጋቢና ገብቼ የመሀለኛው ወንበር ላይ ተቀመጥኩኝ። እዚህጋ ነው ክስተቱ………
ሹፌሩ ወዴትም መጠጋት ላይችል ነገር ክብሩን ለመግለፅ በሚመስል መልኩ ተጠጋልኝና "አሰላሙ ዐለይኩም" አለኝ።
የዘፈኑ ጩኸት፣ የፀጉሩ አፈራረዝ፣ ከለበሰው የጂንስ ቁምጣ ጋ ተዳምሮ በተለምዶ "የዱርዬ" የሚባለው ገፅታ ያሟላ ነበር። ያቀረበልኝ ሰላምታ ከመለስኩለት በኋላ: "የምር ሙስሊም ሆኖ ነው እንዲህ የሆነው?" የሚል ጥያቄ ተፈጠረብኝና ቀና ብዬ የመኪናው ዳሽቦርድ ስመለከት በተለያዩ ኢስላማዊ ጥቅሶች ተጨናንቋል።
"ሙስሊም ሆኖ እንዲት እንዲህ ይበላሻል?" የሚል ድብርት ያዘኝ፤
"እንዲህ ለብሶ, እንዲህ እያዘፈነም እስልምናውን አይረሳም? ለሙስሊም ወንድሙ ፍቅር ያሳያል?" የሚል ደስታም በውስጤ ያቃጭላል፤
በመጨረሻም………
"ዘመናዊነት" በሚል ክፉ መንፈስ የሙስሊም ወጣቶች መበላሸት እና ኢስላማዊ ባህል ማጣት ውስጤ ተረብሾ ለእኔም ለእሱም አዘንኩኝ።
🤲አላህ ወደ እሱ ያማረ የሆነ መመለስ ይመልሰን🤲
🖊ሐምዱ ቋንጤ ከፉርቃን ሰማይ ስር!!
https://t.me/hamdquante