ኢትዮጵያ የሌዊን ክህነት ከመልከጸዴቅ ክህነት ጋር አስተባብራ የያዘች ነች።
በዓለም ልዩ ከሚያደርጓት ነገሮችም አንዱ ይህ ነው።
በጥንት ዘመን በነበረው የክህነት ስርአት ካህን የሚሆኑት ከአስራ ሁለቱ የእስራኤል ነገዶች ውስጥ የሌዊ ነገዶች ብቻ ነበሩ። ይህም ስርአት ለሺዎች ዓመታት በእስራኤል ዘንድ ቆይቷል።
ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም የዘለዓለም ካህን መሆኑን ሲያጠይቅ ከሌዊ ነገድ ተወልዷል። ምክንያቱም እናቱ እመቤታችን ድንግል ማርያም ከካህኑ አሮን ወገን ማለትም ከሌዊ ነገድ የምትወለድ ስለሆነች። በሌላኛው ወገን ደግሞ ከይሁዳ ነገድ ከንጉስ ዳዊት ወገን ስለምትወለድ ልጇም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በእስራኤል ህግና ስርአት ንጉስም ካህንም መሆኑን አስረግጧል።
ታዲያ የጌታችን ክህነት እንደ ሌዊው ክህነት ብቻ አልነበረም። ሌዋውያን ካህናት የህዝቡን ኃጢአት ለማስተሰረይ የእንስሳውን ደም መስዋእት ያደርጉ ነበር። እርሱ ግን የራሱን ሥጋ መስዋእት አድርጎ አቀረበ። በዚህም የሌዋውያን ካህናትን ስርአት ፈጸመ። ነገር ግን የርሱ ክህነት ከዛም ያለፈ ነበር። ንጉስ ዳዊት በመዝሙሩ እንደተናገረው "እንደ መልከጼዴቅ ስርአት አንተ የዘለዓለም ካህን ነህ" ያለውም ይፈጸም ዘንድ ጌታችን ያንኑ የክህነት ስርአት አጽንቷል።
እርሱንም ስርአት በሀዲስ ኪዳን ዘመን በማስፋት፣ በወይንና በስንዴ የሚካሄደው የመልከጼዴቅ መስዋእት ስርአት በዓለም ሁሉ እንዲዳረስ አድርጓል። ምክንያቱም በሀዲስ ኪዳን አህዛብ ሁሉ ወደ ክርስትና መጥተዋልና፤ ለነርሱም ክህነት ይሰጥ ዘንድ ግድ ነውና። ነገር ግን የሌዊ ክህነት ለአህዛብ መሰጠት አይችልም፣ ግልጽ በሆነ ምክንያት። ስለዚህም አህዛብ ሁሉ በመልከጼዴቅ ክህነት ማገልገል ቀጠሉ።
በኋላም አይሁድ በሮም ግዛት ላይ ባመጹ ጊዜ የሮሙ ንጉስም ወረራቸው፣ የሰሎሞንም ቤተመቅደስ ድጋሜ አፈረሰው፣ ሀገራቸውንም አጠፋ እነርሱም በዓለም ላይ ተበተኑ። በዚህም ምክንያት የሌዊው ክህነት ስርአትም አብሮ ጠፋ። ከዚያም የተነሳ አሁን ያሉ አይሁዶች ወጥ የሆነ የእምነት መሪም ሆነ የስልጣን ተዋረድ ያለው ስርአት መገንባት ሳይችሉ ቀርተዋል።
ኢትዮጵያ ግን ትለያለች። እስከዛሬም ድረስ በዓለም የጠፋው የሌዊ ስርአት በኛ ዘንድ አልጠፋም። እግዚአብሔር ኢትዮጵያን የመልካም ነገሮች ሁሉ ጠባቂ ግምጃ ቤት አድርጎ አስቀምጧታል። በዓለም የጠፋው ሁሉ በርሷ ዘንድ ተጠብቆ ይገኛል... ግማደ መስቀሉ፣ ታቦተ ጽዮን፣ መጽሐፈ ሄኖክ፣ መጽሐፈ አክሲማሮስ፣ ውዳሴ ማርያም ... ሌሎችም ሌሎችም።
ታዲያ የሌዊ ክህነት እንዴት ወደ ኢትዮጵያ መጣ? ስንል ወደ ኋላ ወደ ንጉስ ሰሎሞን ዘመን ይወስደናል። የሰሎሞንና የማክዳ ልጅ ምኒልክ ለአቅመ አዳም በደረሰ ጊዜ አባቱን ለመጠየቅ ወደ እስራኤል ይሄዳል። በዚያም ቆይቶ ሲመለስ አባቱ ሰሎሞን ከመኳንንቱ ሁሉ ጋር ተማክሮ ህዝቡንም አሳምኖ ከአስራ ሁለቱም ነገዶች ወንዶችም ሴቶችም አድርጎ ይመርጥና ከልጁ ጋር ወደ ኢትዮጵያ ይልከዋል። ከነዚህም ውስጥ የሊቀካህኑ የአዛርያስ ልጅ ሳዶቅ ይገኝበታል።
ምኒልክም አብረውት የመጡት እስራኤላውያን በኢትዮጵያ መንግስትና እምነት ስርአት ውስጥ በመግባት የመሪውን ቦታ ይይዛሉ። የልጅ ልጆቻቸውንም በመተካት ዘራቸው ይቀጥላል። እንደ ገድለ ተክለሃይማኖት ያሉ መጻሕፍት ላይም ስንመለከት የአክሱም ነገስታትና ካህናት በሙሉ የዘር ሀረጋቸው የሚመዘዘው ከንጉሱ ምኒልክ እና ካህኑ ሳዶቅ ነው። የነዚህም ሳይቋረጥ ቀጥሎ ነበር።
ከዚያ የዘር ሀረግም እንደ አቡነ ተክለሃይማኖት፣ አቡነ ዜና ማርቆስ፣ አቡነ አኖሬዎስ ሌሎችም ታላላቅ የኢትዮጵያ ቅዱሳን ተገኝተዋል።
ዛሬም ድረስ በኢትዮጵያ የሚነሱ ካህናት ዘራቸው ወደኋላ ቢቆጠር የሌዊ ካህናት ዘር ይገኝበታል። እስራኤላውያንም በኢትዮጵያ ውስጥ ያልተቀላቀሉት ነገድ ወይም "ብሔር" የለምና በመላው ሀገሪቱ ባሉ ህዝቦች ቢቆጠሩ የዚህ የካህናት ዘር ይኖርበታል።
በሀዲስ ኪዳን በተቀበልነው ስርአት ደግሞ የመልከጼድቅን ክህነትም አጣምረን የያዝን ሆነናል። በርግጥ ያ ስርአት የሌዊው ክህነት ከመምጣቱም በፊት እኛ ጋር እንደነበረ የሚጠቁሙ ነገሮች ቢኖሩም ማለት ነው።
በዚህም እግዚአብሔር በኢትዮጵያ ፈቃዱን እየፈጸመ በሺዎች ዓመታት የዘለቀ ስርአቱን ያስቀጥልበታል።